Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ለቃጥባሬ አካባቢ ነዋሪዋች

Kheyredin Adem
ለቃጥባሬ አካባቢ ነዋሪዋች ==========
በየአመቱ አሏህና መልክተኛዉ ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም የሚታመፅበት የሼህ ኢሳ ሀምዛ የልደት በአል (መዉሊድ)
አስመልክቶ አዉቀንም ይሁን ሳናዉቅ ለዚህ ባጢል ድርጊት ድጋፍ የምንሰጥ ሰዎች አሏህን እንፍራ። በተለይ በወልቂጤ፤ በጉብርየ፤
በአገና፤ አበሽጌ፤ ጎሮ፤ ዘናበነር፤ ሀዋርያት ፣ እንዲሁም በቸሀ፣ በቀቤና፣ በእዣ ወረዳዎች የምትገኙ ሙስሊም ወገኖቻችን ለቦታዉ
ካላቹ ቅርበት የተነስ የምግብ፤ የቁሳቁስ፣ የመጓጓዣ፤ የሀይል አቅርቦት ድጋፍ የምታደርጉ አሁንም አሏህን ፍሩ እላለሁ። ለዱንያ
ጥቅም ብለን ተዉሂድን በሚያጠፋ ድርጊት አንተባበር። በቦታዉአሏህ ይታመፃል፣ ለቀብር ኢስቲጋሳ ይደረጋል፣ በመንዙማ
ይጨፈራል፣ በሼህ ኢሳ ይማላል ከዚህ አልፎ ሱንዮችን የሚቃወሙበትን በአል ላይ የንግድ እቃዎቻችን እያጓጓዝን ለበአሉ ድምቀት አንሁን ። ቦታዉም መሄድ ካለብን ካሉበት ጥመት ለማስጠንቀቅ ና ተዉሂድን ለመስበክ ካልሆነ መሄድ የለብንም።
አሏህ ሆይ እዘንልን ተዉሂድ አሳዉቀን በዛም ላይ ግደለን። አሜን።