በሱረቱል ፋቲሃህ ጥላ ስር
ሙስሊሞች ሆይ ቁርአንን በጥሞና ብናስተውለው በሚገባ ብንመረምረው ለዓቂዳ ከፍተኛ ትኩረት የቸረ ሆኖ እናገኘዋለን ። በተለይም መካ ላይ የወረዱ (መክይ) የቁርአን አንቀፆችና ምዕራፎች ዐይነተኛ ሚናቸው ኢስላማዊ ዐቂዳን ማስተማርና እርሱን ተቃርኖ ለሚገኝ እምነት ወይም አመለካከት ተገቢውን ምላሽ መስጠት ነው ። መካ ላይ ከወረዱት ምዕራፎች አንዷ የሆነችው አል-ፋቲሐህ ለዚህ ጥሩ ማስረጃ እና ምሳሌ ናት።
ኢማሙ ኢብኑል ቀይም እንዲህ ሲሉ ፅፈዋል ፡-
ይህች ምዕራፍ አል-ፋቲሐህ እጅግ ጠቃሚ ቁም ነገሮችን አጠቃላ ይዛለች አላህን በሦስይ አበይትና የሌሎች የአላህ ባህሪያትና ስሞች ምንጭ ሊሆን በሚችሉ ባህሪያት አስተዋውቃለች እነርሱም << ረብ ጌታ እና ረህማን እጅግ በጣም ሩህሩህ የሚሉት ናቸው ።
የአላህን ብቸኛ አምላክነት ኡሉሂያ የበላይ ገዢነት ሩቡብያህ እና አዛኝነት ረህማህ በሚገባ ገልጻለች ። << አንተን ብቻ እናመልካለን የሚለው የምዕራፏ ክፍል የአላህን ብቸኛ አምላክነት ኢላህያን የሚያመለክት ሲሆን እገዛ የምንጠይቀው አንተን ብቻ ነው የሚለው ክፍል የበላይ ገዢነት ሩቡብያህ ያሳያል ቅኑን መንገድ ይመራን ዘንድ አላህን የምንጠይቅበት ክፍል ደግሞ የእርሱን አዛኝነት ረህማህ ያመለክታል።
የምዕራፏ መወጠኛ የሆነው መወወስጋና ሐምድ ሦስት ነገሮችን ይጠቁማል አላህ በአምላክነቱ በበላይ ገዢነቱ እና በኣዛኝነቱ ሊመሰገን እንደሚገባው ምስጋና ውዳሴ የልዕልና መገለጫዎች ናቸው ምዕራፏ የሰው ዘርን መጨረሻ እጣ ፈንታ ጠቁማለች ለመልካም ወይም ክፋ ስራዎች ተገቢውን ዋጋ እንደሚያገኙ ትገማለች። በመዒውም ዓለም በሚሰጠው ብይን ብቸኛ ዳኛው አላህ ነው። በፍትህ ይዳኛል ይህ ሁሉ የተገለፀው <<የፍርዱ ቀን ንጉስ>> በሚለው ህብረ ቃል ነው።
ምዕራፏ የነቢያትን መኖር አስፈላጊነት በብዙ መልኩ አሳይታለች
ኢብኑል ቀይም ማብራሪያቸውን በመቀጠል እንዲህ ይላሉ፡-
<<ቁርአን ሙሉ በሙሉ የሚያተኩረው የተውሂድን፣ ሀቅን ና የሚያሳየውን የላቀ ምንዳ እንዲሁም ሽርክን ሙሽሪኮችን የመጨረሻ እጣ ፈንታቸውን በማብራራት ላይ ነው። >>
<<ምስጋና ለአላህ ለዓለማት ጌታ>> የሚለው ክፍል ተውሒድ ነው። <<እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ>> የሚለው ተውሒድ ነው።
<<ቀጥተኛውን መንገድ ምራን ፣ የእነዚያን አያሌ ፀጋዎችን የለገስካቸውን>> የሚለው ክፍልም ተውሒድ ነው። ወደ ተውሒድ ሰዎች ጎዳና ለመመራት አላህን መማፀን ያስተምራል ። <<ያልተቆጣህባቸውንና መንገድ ያልሳሳቱትን ጎዳና ጠቁመን።>>
እንዲህ ሲሉም ፅፈዋል፡-
<< አብዛኛዎቹ የቁርአን ምዕራፎች ስለ ተውሒድ የሚሉት ነገር አላቸው ቁርአን ስለ አላህ ስሞችና ባህሪያት ያስተማረው ተውሒድን ነው። እርሱን ብቻ በብቸኝነት ስለማምለክና ከርሱ ውጪ ሌሎች ኃይሎችን ከማምለክ ስለመቆጠብ ያስተምራል።ይህም ተውሒድ ነው። አንድ ነገር ያዛል። አንዳች ነገር ይከለክላል። አላህን ብቻ በብቸኝነቶ የማምለክ ተገቢነት ይገልፃል። እነኚህ የተውሒድ ሐቆች ናቸው። የተውሒድ ሰዎችን ልዕልናና በዚህች ዓለም አላህ ምን እንደፈፀመላቸው በመጭው ዓለምም የሚጠብቃቸውን ታላቅ እድል ይዘክራል። ይህም የተውሒድ መልካም ምንዳ ነው። የሽርክ ሰዎችን በዚህ ዓለም የገጠማቸውን ውርደትና በመጪው ዓለም የሚጠብቃቸውን ቅጣት ያወሳል።ይህ ከተውሒድ ያፈነገጡ ሰዎች የሚገጥማቸውን ውርደት የሚጠቁም ነው።>>
ቁርዓን ለዓቂዳ ከፍተኛ ትኩረት ይሰጣል ። አብዛኛዎቹ ቁርአንን የሚያነቡ ሰዎች ግን ስለ ዓቂዳ ትክክለኛ ግንዛቤ የላቸውም ። ነገሮች ሲምታታባቸው ይስተዋላል። የሚከተሉት ከአያት ቅድመ አያቶቻቸው የወረሱትን እምነት በመሆኑ በጥሞና አይመረምሩትም ላሃውላ ወላቁወተ ኢላቢላህ!