Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

መውሊድ እንዴት ተጀመረ???

መውሊድን በተመለከተ

① የመውሊድ እንዴት ተጀመረ???

☞ መውሊድን ዲነል ኢስላም ዳግም በነብዩ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም አማካኝነት ካንሠራራ በት ቀን አንስቶ ለረጅም ዘመናት የማያውቀው አዲስ እንግዳ ነገር እንደሆነ ማንም ሣያመነታ የሚቀበለው ነገር ነው እናም ይህ መጤ ነገር የተወሠደው ከእስልምና ውጪ ካሉ እምነት ተከታዩቾ ነው ነሣራዎች የኢሳ አለይሂ ሠላት ወሠላምን የልደት አመት ሢያከብሩ የተመለከቱ ሠዎች የነብዩን ሠለላሁ አለይሒ ወሠለምን የልደት አመት ማክበር ጀመሩ

☞ ይህ ተሸቡህ (መመሣሠል) ነብዩ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም ገና ሣይከሠት የተናገሩት ትንቢት ነው

(ﻟﺘﺘﺒﻌﻦ ﺳﻨﻦ ﻣﻦ ﻛﺎﻥ ﻗﺒﻠﻜﻢ ﺷﺒﺮﺍً ﺑﺸﺒﺮ ﻭﺫﺭﺍﻋﺎ ﺑﺬﺭﺍﻉ ﺣﺘﻰ ﻭﻟﻮ ﺩﺧﻠﻮﺍ ﺟﺤﺮ ﺿﺐ ﺗﺒﻌﺘﻤﻮﻫﻢ)

"ከናንተ በፊት የነበሩ ሠዎችን መንገድ የወከሎ ጉድጓድ እስኪገቡ ድረስ እርምጃ በእርምጃ ትከተሏቹሀላቹ ትገባላችሁ "

☞ ነሣራዎች እና ሌሎች ከኢስላም ውጪ ያሉ እምነቶች ጋር ለመመሣሠል ተብሎ የተሠራ ስህተት ነው መውሊድ እንዲጀመር የረዳው!!!

② ለመጀመርያ ግዜ መውሊድ የተከበረው መቼ ነው???

☞ መውሊድ ቢድአ (መጤ) መሆኑን አስረግጠው የሚያስረዱ ኡለሞች ነብዩ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም ፣ ሡሀቦች ፣ ታብእዬች ፣ አትበአ ታብእዬችም ባጠቃላይ በጥሩነታቸው ከነብዩ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም አንደበት የተመሠከረላቸው የሦስቱ ክፍለ ዘመን ምርጥ ሠዎች መካከል አንድም ሠው አላከበረም እንዲከበርም አላዘዘም እንደውም መውሊድ የሚባለው ነገር እነሡ ዘንድ አይታወቅም

ታድያ መቼ ተጀመረ???

☞ በታሪክ እንደሚታወቀው ለመጀመርያ ግዜ የነብዩ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም የልደት ቀን ተብሎ የተከበረው የአራተኛው ክፍለ ዘመን ማብቂያ ላይ ግብፅ ውስጥ በፋጢምያዎች ነው

③ በመውሊድ ሠበብ …???

☞ መውሊድን ማክበር ቢድአ መሆኑ ሣይበቃ መውሊድ ስም ቁጥር ስፍር የሌላቸው ሽርክያት እና ሁራፋት የበዛባቸው እንቅስቃሴዎች እና ንግግሮች ይገኙበታል ከነሡ ውስጥ

⇏ በነብዩ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም ላይ ድንበር ማለፍ ፦

☞ አለም ላይ ለመጀመርያ ግዜ በአላህ ሡብሀነሁ ወተአላ ላይ የተጋራው (ሽርክ የተሠራው) መልካም ሠዎችን ከልክ በላይ በማወደስ (ድንበር በማለፍ ነው) በመውሊድም ስም ነብዩን እናወዴሣለን ብለው ለሣቸው የማይገባቸውን የአላህ መብት አሣልፈው ይሠጧቸዋል ይህንንም በሚያከብሩበት ቀን ከሚሏቸው መንዙማዎች ላይ እያየነው ያለ ነገር ነው ሆኖም ይህ ነገር ከመከሠቱ በፊት መለኮታዊው ነብይ አንድ ወሣኝ ነገር ጥለውልን አልፈዋል

"ﻻ ﺗﻄﺮﻭﻧﻲ ﻛﻤﺎ ﺃﻃﺮﺕ ﺍﻟﻨﺼﺎﺭﻯ ﺍﺑﻦ ﻣﺮﻳﻢ ﻭﺇﻧﻤﺎ ﺃﻧﺎ ﻋﺒﺪ ﻓﻘﻮﻟﻮﺍ: ﻋﺒﺪ ﺍﻟﻠﻪ ﻭﺭﺳﻮﻟﻪ"
"ነሣራዎች የመርየምን ልጅ ከፍ ከፍ እንዳደረጉት ከፍ ከፍ ከፍ አታድርጉኝ እኔ የአላህ ባርያ ነኝ የአላህ ባርያ እና መልዕክተኛው በሉኝ "

⇏ በዚህች ቀን ደኢፍ በሆነ ሀዲስ ላይ ተመርኩዘው ነብዩ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም ከብርሀን እንደተፈጠሩ ሢዘፍኑ ይውላሉ ነገር ግን አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ ምን አይነት ነብይ እንደላከልን ነግሮናል ስለ ላከው እና ስለፈጠረው ነገር ደግሞ ከእርሡ በላይ አውቃለው ማለት ሞኝነት ነው

( ﻟَﻘَﺪْ ﺟَﺎﺀَﻛُﻢْ ﺭَﺳُﻮﻝٌ ﻣِﻦْ ﺃَﻧﻔُﺴِﻜُﻢْ ﻋَﺰِﻳﺰٌ ﻋَﻠَﻴْﻪِ ﻣَﺎ ﻋَﻨِﺘُّﻢْ ﺣَﺮِﻳﺺٌ ﻋَﻠَﻴْﻜُﻢْ ﺑِﺎﻟْﻤُﺆْﻣِﻨِﻴﻦَ ﺭَﺀُﻭﻑٌ ﺭَﺣِﻴﻢٌ)
"ልክ እንደናንተ የሆነ መልእክተኛ መጣላችሁ እናንተ ያላችሁበት ችግር የሚበረታበት የሆነ ፣ መልካም ነገር እንድታገኙ የሚጓጓ ፣ በምእመናን ላይ ሩህሩህ እና አዛኝ የሆነ "

☞ "ልክ እንደናንተ የሆነ…" ማለት
① እንደናንተው ሠው የሆነ
② ከአረቦች የሆነ እንደ ሁለቱም ትክክል ነው

☞ ይህን ካልን ነብዩ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም ሠው ናቸው የሠው ልጅ ደግሞ የተፈጠረው ከአፈር እንጂ ከብርሀን አይደለም!!!

⇏ ቀኗን በዘፈን እና በዳንስ ማሣለፍ ፦ ሠለዋት ነው በሚል ሽፋን መሣጂዶች ዳንስ ቤት እስኪመስሉ ድረስ መዝፈን እና መደነስ

⇏ የመስጂድን ክብር የሚያጎድፋ ነገሮች ወደ መስጂድ ይዞ መግባት እንደ ጫት እና መሠሎቹን

⇏ ሤቶች ተኳኩለው እና ተገላልጠው ከወንዶች ጋር መሠባሠብ መዝፈን እና መደነስ

☞ እና ሌሎችም ተዘርዝረው የማያልቁ እንከኖች መውሊድ እናክብር በሚል ስም ይተገብራሉ

ተመልሼ እመጣለው

Post a Comment

0 Comments