Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

መውሊድን ማክበር ለምን ይከለከላል?????????


መውሊድን ማክበር ለምን ይከለከላል?????????
1 መውሊድን ማክበር የረሱል( صلى الله عليه وسلم) እና የባልደረቦቻቸው ፈለግ ስላልነበረ።መውሊድ ሙሉ በሙሉ አዲስ ፈጠራ ነው ምክንያቱም ረሱል صلى الله عليه وسلم) የሰቸውን እና ከሰቸው በኳለ በቅን የተመሩትን በልደረበዎቻቸውን እንድንከተል እና ፈለጋቸውንም አጥብቀን እንድንይዝ አዘውናል ቀጥለውም አዲስ ፈጠራን እንድንጠነቀቅ እና አዲስ ፈጠራ ሁሉ ጥመት እንደሆነ ጥመት ወደ እሳት እንደሚመራ እንድ ቀን ጸሓይ ግልጽ በሆነው ንግግራቸው ነግረውናል።አብዛኛው መውሊድን የሚያከብሩ አካለት ለምን ታከብራላቹህ ተብለው ሲጠየቁ እኛ ረሱልን( صلى الله عليه) ስለምንወድ ነው ይሉሓል በተቃራኒው እናንተ(መውሊድን የሚቃረኑትን አካላት) የረሱል(( صلى الله عليه) ጠላቶች ናቹ ይሉናል፡እኛም የምንላቸው እውነተኛ ውዴታ በተግበር እንጂ መሰረት በሌለው ወረት አይገለጽም እውንውተኛ ወዳጆች ከሆናቹ ፈለጋቸውን በመከተል እንጂ አዲስ ፈጠራን በመከተል አይገለጽም እንላቸዋለን። ረሱልም() صلى الله عليه) በመጾም እንጂ በመጨፈር እና ኹራፋት ተግባር ውስጥ ተዘፍቀው አላሳለፉም፡ አላህ እኛንም እናንተንም የሚያዘን እንድንከተል ብቻ እንጂ በመጤ ፈጠራዎች እንድንዋልል አላዘዘንም እንግዲያውስ እውነታው ከተገለጸ በሗለ ሐቅን የመከተል ያለመከተል ምርጫ በእጃቹ ነው እንላቸዋለን ፥ ለሚገሰጹት ከቁርኣን ብዙ መገሰጫዎች አሉ
قُلْ إِن كُنتُمْ تُحِبُّونَ اللَّهَ فَاتَّبِعُونِي يُحْبِبْكُمُ اللَّهُ وَيَغْفِرْ لَكُمْ ذُنُوبَكُمْ ۗ وَاللَّهُ غَفُورٌ رَّحِيمٌ [٣:٣١]
በላቸው፡- «አላህን የምትወዱ እንደኾናችሁ ተከተሉኝ፤ አላህ ይወዳችኋልና፡፡ ኀጢኣቶቻችሁንም ለናንተ ይምራልና፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡» እስቲ ንገሩን እውነት አላህን ና መልክተኛውን ትወዳላቹሁን? አዎ ከሆነ መልሳቹህ እንግዲያውስ ተከተሉ አዲስ ፈጠራን አትፍጠሩ።

اتَّبِعُوا مَا أُنزِلَ إِلَيْكُم مِّن رَّبِّكُمْ وَلَا تَتَّبِعُوا مِن دُونِهِ أَوْلِيَاءَ ۗ قَلِيلًا مَّا تَذَكَّرُونَ [٧:٣]
ከጌታችሁ ወደእናንተ የተወረደውን ተከተሉ(ቁርኣን እና ሱንና)፡፡ ከአላህም ሌላ ረዳቶችን አትከተሉ፡፡ ጥቂትን ብቻ ትገሰጻላችሁ፡፡

وَأَنَّ هَٰذَا صِرَاطِي مُسْتَقِيمًا فَاتَّبِعُوهُ ۖ وَلَا تَتَّبِعُوا السُّبُلَ فَتَفَرَّقَ بِكُمْ عَن سَبِيلِهِ ۚ ذَٰلِكُمْ وَصَّاكُم بِهِ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ [٦:١٥٣]
«ይህም ቀጥተኛ ሲኾን መንገዴ ነው፤ ተከተሉትም፡፡ (የጥመት) መንገዶችንም አትከተሉ፡፡ ከ(ቀጥተኛው) መንገዱ እናንተን ይለያዩዋችኋልና፡፡እነሆ ትጠነቀቁ ዘንድ በርሱ አዘዛችሁ፡፡» በመቀጠልም እንደሚታወቀው መውሊድ መከበር የተጀመረው ከ3-4 መቶ አመታት በኳለ በግብጽ ሓገር (1232) እንደሆነ የተሪክ መዛግብት ያመላክታሉ። ይህን መሰል(መውሊድን) ና ሌሎችንም ረሱል( صلى الله عليه) እና የሳቸው ባልደረባዎች የልሰሩትን ኢባዳ ወደ አላህ ዘንድ ያቃርበነል ብሎ መስራት ረሱል( صلى الله عليه) ለዚህ ሕብረተሰብ አድርሱ የተባሉትን መልእክት በኣግባቡ አለደረሱም ብሎ መሞገት እና አላህ ሱብሃነሁ ወተኣላ ዲናችንን ሙሉ እንዳደረገው የገለጸልንን ነገር በተዘዋዋሪ ማጣጠል መሆኑን ልንዘነጋው አይገባም። ዲናችን ምንም የሚጎድለው ነገር እንደሌለ በግልጽ ቁርኣን ላይ ሰፍሮ ይገኛል
الْيَوْمَ أَكْمَلْتُ لَكُمْ دِينَكُمْ وَأَتْمَمْتُ عَلَيْكُمْ نِعْمَتِي وَرَضِيتُ لَكُمُ الْإِسْلَامَ دِينًا ۚ [٥:٣]
ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለናንተ ሞላሁላችሁ፡፡ ጸጋዬንም በናንተ ላይ ፈጸምኩ፡፡ ለእናንተም ኢስላምን ከሃይማኖት በኩል ወደድኩ፡፡
2 መውሊድን ማክበር ከካፊር ጋር መመሳሰል ነው ምክንያቱም እናሱ የኢሳን(አለይሂ ሰላም) ልደት ያከብራሉና፡ ፈለጉም የተያዘው ከማን አንሰን በሚል አስተሳሰብ እንደሆና ይታወቀል(ያለ አዋቂ ሰሚ ንፍጥ ያለቀልቃል አለ ያገሬ ሰው)። ከፊሮችን መመሳሰል እጅግ በጣም የተከለከል ነገር ነው። ረሱል( صلى الله عليه) እንዲህ ብለዋል እነሱን የሚመሳሰል ከነሱ ነው። በተለይ ነገሩ የከፋ የሚሆነው ሐይማኖታዊ በሆነ ጉደይ ነው ይህ( ልደትን ማክበር) ደግሞ ግልጽ ጉዳይ ነው።
3 መውሊድን መክበር ቢድኣ እና ከኩፋሮች መመሳሰል ከመሆኑም ባሻገር በረሱል( صلى الله عليه) ላይ በመውደድ እና በማላቅ ስም ድንበር እንዲታለፍ በርን ይከፍታል ። እንደሚታወቀው እና እንደሚተገበረውም መውሊድን ሳቢያ በማድረግ በ ረሱል( صلى الله عليه) ለይ ከባባድ ድንበር ማለፎች ይከናወናሉ ለምሳሌ እርዳታን ከሳቸው መፈለግ ፣ ዱኣን ለሳቸው ማድረግ፣ ድረሱልኝ ማለት፣ ሞተው ሳለ በህይወት እንዳሉ አድርጎ መጣራት -----------። ረሱል( صلى الله عليه) በሳቸው ላይ ድንበር እንዳይታለፍ እጅግ በጣም አስጠንቅቀዋል ምን ኣሉ? “ የመሪየምን ልጅ ኢሳን(አለይሂ ሰላም) ክርስቲያኖች ከፍ ከፍ እንዳደረጉት ከፍ ከፍ አታድርጉኝ። እኔ የአላህ ባሪያ ነኝ የአላህም ባሪያ እና መልክተኛ ብላቹህ ጥሩኝ።”
4 የረሱል( صلى الله عليه) መውሊድ ብሎ ማክበር ለብዙ አዳድስ ፈጠራዎች በር ይከፍታል ሁላችንም እንድምናውቀው በተለይ በተለይ በገጠር አካባቢ የሼህ ኤከሌ መውሊድ እየተበለ በየ አመቱ ለሰዎች ቀብር ሲሰገድ እና ሙታን ሲለመኑ ማየት እዲስ ነገር አይደለም። ለምሳሌ በስልጤ እና በጉራጌ ለይ ከሚገኙት አልከሶ፣ አብሬት፣ ሶርጋን ፣ሸውባድር፣ቀጥባሬ------- እነኚህን የቀብር ባልትተቤቶች ረደት፣ ተንከባካቢ፣ መቃረቢያ እና ጠባቂ አድርገው እንደሚይዙዋቸው የተወቀ ነገር ነው። እነዚህ ተግባራትት የጃሂሊያዎች ተግባራት ነበሩ ግና ቢድኣ የማየስከትለው ጥፋት ዬለም እና ያለንበትንም መሕበረሰብ የቀደምት ጀሒሊያዎቹ ይፈጽሙት የነበረውን ተግባራት እንዲፈጽሙ በር ከፈተላቸው። ግን አላህ ይህንን ተግባር በግልጽ ይቃወመዋል
وَيَعْبُدُونَ مِن دُونِ اللَّهِ مَا لَا يَضُرُّهُمْ وَلَا يَنفَعُهُمْ وَيَقُولُونَ هَٰؤُلَاءِ شُفَعَاؤُنَا عِندَ اللَّهِ ۚ قُلْ أَتُنَبِّئُونَ اللَّهَ بِمَا لَا يَعْلَمُ فِي السَّمَاوَاتِ وَلَا فِي الْأَرْضِ ۚ سُبْحَانَهُ وَتَعَالَىٰ عَمَّا يُشْرِكُونَ [١٠:١٨]
ከአላህም ሌላ የማይጎዳቸውን የማይጠቅማቸውንም ይግገዛሉ፡፡ «እነዚህም አላህ ዘንድ አማላጆቻችን ናቸው» ይላሉ፡፡ «አላህን በሰማያትና በምድር ውስጥ የማያውቀው ነገር ኖሮ ትነግሩታላችሁን» በላቸው፡፡ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ፤ ላቀም፡፡ በሌላ አያ ላይ አላህ እንዲህ ይለናል
أَلَا لِلَّهِ الدِّينُ الْخَالِصُ ۚ وَالَّذِينَ اتَّخَذُوا مِن دُونِهِ أَوْلِيَاءَ مَا نَعْبُدُهُمْ إِلَّا لِيُقَرِّبُونَا إِلَى اللَّهِ زُلْفَىٰ إِنَّ اللَّهَ يَحْكُمُ بَيْنَهُمْ فِي مَا هُمْ فِيهِ يَخْتَلِفُونَ ۗ إِنَّ اللَّهَ لَا يَهْدِي مَنْ هُوَ كَاذِبٌ كَفَّارٌ [٣٩:٣]
ንቁ! ፍጹም ጥሩ የኾነው ሃይማኖት የአላህ ብቻ ነው፡፡ እነዚያም ከእርሱ ሌላ (ጣዖታትን) ረዳቶች የያዙት «ወደ አላህ ማቃረብን እንዲያቀርቡን እንጅ ለሌላ አንገዛቸውም» (ይላሉ)፡፡ አላህ በዚያ እነርሱ በእርሱ በሚለያዩበት ነገር በመካከላቸው ይፈርዳል፡፡ አላህ እርሱ ውሸታም ከሓዲ የኾነን ሰው አያቀናም፡፡ የአላህ ከእንዲህ አይነት ጥመት በአንተው እጠበቃለሁ። እንሻኣላህ በቀጣይ መውሊድ አክባሪዎች ለማክበራቸው የሚያቀርቡትን ተልካሻ ምክንያቶች ከነ ምላሻቸው ለማቅረብ እጥራለሁ

Post a Comment

0 Comments