Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

መውሊድ

መውሊድ
ከአላህ እና ከመልክተኛው (ሰላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይሁን) ውጭ ሸሪዓን መደንገግ የሚችል አለን? አላሁ (ሱብሀነሁ ወተዓላ) ሃይማኖቱን ሞልቶታል፡፡ ይህ ታላቅ እውነታ ሊረሳ አይገባውም፡፡ በእስልምና ሀይማኖት የአላህ መልክተኛ በተግባር ሰርተው ያሳዩት እና ያዘዙበት ሁለቱን ኢዶች ብቻ ነው፡፡ የአላህ መልክተኛ ከመልክታቸው የደበቁት ነገር አለን? አላህን ከመልክተኛው ቀጥሎ አላህ ላይ ያመኑ፤ የወደዱት፤ ሀብት ንብረታቸውን ለአላህ ዲን የሰጡት ሰሃባዎች፤ ከማናችንም በላይ የአላህን መልክተኛ ይወዱ ነበር፡፡ የታዘዙትንም ይፈፅሙ ነበር፡፡ ይህንን የሚጠራጠር አለን?
አላህም ሙሃጂርና አንሳርን የተከተለን ሰው እንደሚወድ ተናግራል፡፡ የሚከተሉትን ጥያቄዎች እንመልስ
ነብያችን ሰርተውበታልን? እንዲሰራ አዘዋልን?
አቡበክር አሲዲቅ ሰርቶታልን? እንዲሰራ አዘዋልን?
ኡመር ሰርቶታልን? እንዲሰራ አዘዋልን?
ኡስማን ሰርቶታልን? እንዲሰራ አዘዋልን?
አልይ ሰርቶታልን? እንዲሰራ አዘዋልን?
ሙሃጂሮችና አንሳሮች ሰርተውታልን?
ታቢእዮች፤ አትባ ታቢኢን፤ አቡ ሀኒፋ፤ ኢማሙ ማሊክ፤ ኢማሙ ሻፊእ፤ ኢማሙ አህመድ፤፤፤፤፤ ሰርተውታልን?
መውሊድ ከዚህ ሁሉ አመታት በሃላ ዲን ላይ መጨመሩ ብቻ የጥፋት መንገድ ለመሆኑ በቂ ማስረጃ አይሆንምን?
አላህ መውሊድ በመስራቴ ይቀጣኛልን? ብሎ አንድ ሰው ቢጠይቅ፡፡ የሰይድ ሙሰየብ ንግግር መልስ ይሆናል፡፡ አንድ ሰው ከሱቢህ በሃላ ደጋግሞ ሰላት ሲሰግድ አዩት፤ ከዛም እሳቸው ተው ሲሉት እሱም እንዲህ አለ ‹‹አላህ ሰላት በመስገዴ ይቀጣኛልን?›› እሳቸውም እንዲህ ብለው መለሱለት ‹‹ሰላት በመስገድህ ሳይሆን መልክተኛውን በመቃረንህ ነው››
ይህ ከሆነ እውነታ፡፡ መውሊድን ለማክበር ችግር የለውም የሚሉ ሰዎች የአላህን ቅጣት አይፈሩምን?
የአላህ ባርያዎች ሆይ! መውሊድ እንደማይቻል መናገር አንዳንድ ሰዎች እንደሚሉት የሙስሊሙን አንድነት የሚበታትን አይደለም፤ እንዲያውም እውነተኛ ወንድማማችነትን፤ ታማኝ መካሪነትን የሚያሳይ ነው፡፡ በአላህ ስም ወንድምና እህቶቼን የምመክረው አላህና መላክተኛው ያዘዙንን በአቅማችን እንስራ፤ ከዛ በተረፈ ያልታዘዝነውን ከመስራት አላህን እንፍራ፡፡ አንድነት ይበታተናል እየተባለ ቢድዓ ዝም ማለት የአላህ ቅጣት ሲመጣ ሁላችንን ነው የሚነካን፡፡ አላህ የሃቅን መንገድ ሁላችንንም ይምራን፡፡ አሚን፡፡

Post a Comment

0 Comments