Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

መውሊድን የማናከብርበት ምክንያቶች

④ መውሊድን የማናከብርበት ምክንያቶች
☞ ነብዩ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም ከነብይነት በፊት 40 አመት ከነብይነት ቡሀላ 23 አመት በድምሩ 63 አመት የኖሩ ሢሆን አንድም ቀን የተወለድኩበት አመት ብለው አክብረው አያውቁም! ለ63 አመት ያክል በጓደኝነት አብሯቸው የነበረው አቡበከር ሲዲቅ በህይወትም እያሉ ሞተውም አንድም ቀን የተወለዱበትን ቀን አክብሮላቸው አያውቅም ፣ እነዛ ነብዩን ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም ባሉበት ሆነው እሾህ እንዳይወጋቸው የሚጨነኩ ብርቅዬ ሡሀቦች አንድም ቀን አከበሩ የሚል ወሬ አልተነገረም ፣ በነብዩ አንደበት ምርጥ በመባል ከተመሠከረላቸው የሦስቱ ክፍለ ዘመን ብርቅዬዎች መካከል አንድ ሠው አክብሯል የሚል የተፃፈ ታሪክ የለም
⇉ ይህንን ያመነ ሠው መውሊድን ሊያከብር አይገባውም አሻፈረኝ ካለ ግን የሚከተለው የቁርአን አያ እሡን ይመለከተዋል
(ﻭﻣﻦ ﻳﺸﺎﻗﻖ ﺍﻟﺮﺳﻮﻝ ﻣﻦ ﺑﻌﺪ ﻣﺎ ﺗﺒﻴﻦ ﻟﻪ ﺍﻟﻬﺪﻱ ﻭﻳﺘﺒﻊ ﻏﻴﺮ ﺳﺒﻴﻞ ﺍﻟﻤﺆﻣﻨﻴﻦ ﻧﻮﻟﻪ ﻣﺎ ﺗﻮﻟﻰ ﻭﻧﺼﻠﻪ ﺟﻬﻨﻢ ﻭﺳﺎﺀﺕ ﻣﺼﻴﺮﺍ)
"የቅናቻው መንገድ ከተብራራለት ቡሀላ መልዕክተኛውን የሚጨቃጨቅ ፣ ከምዕመናን መንገድ ውጪ ያለን መንገድ የሚከተል በዞረበት (ጥመት ላይ) እናዞረዋለን መመለሻነቷ የከፋ የሆነ ጀሀነምንም እንስገባዋለን "
⇉ አያው ላይ " ከምዕመናን መንገድ ውጪ ያለን መንገድ የሚከተል" ይላል የምእመናን መንገድ ማለት የሡቦች ፣ የታብዕዬች ፣ እያለ ይቀጥላል መውሊድ ደግሞ ከነዚህ ቡድኖች ውጪ ነው
☞ መውሊድ ቢድአ ወይም መጤ ነገር ነው በዲን ላይ መጤ ነገር አይሠራም ነብዩ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም እንዲህ ይላሉ
" ﺇﻳﺎﻛﻢ ﻭﻣﺤﺪﺛﺎﺕ ﺍﻷﻣﻮﺭ… "
"አደራችሁን መጤ ከሆኑ ነገሮች "
⇉ ይህን ስል መውሊድ ጥሩ ጭማሪ ነው የሚል እንደማይጠፋ እርግጥ ነው ሆኖም ነብዩ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም የዚህን ጥያቄ ምላሽ ሢነግሩ እንዲህ ይላሉ
"…ﻓﺈﻥ ﻛﻞ ﻣﺤﺪﺛﺔ ﺑﺪﻋﺔ ﻭﻛﻞ ﺑﺪﻋﺔ ﺿﻼﻟﺔ"
"በዲን ላይ ጭማሪ ነገር በአጠቃላይ ቢድአ ነው እያንዳንዱ ቢድአ ደግሞ ጥመት ነው "
(ﻭﻛﻞ ﺿﻼﻟﺔ ﻓﻲ ﺍﻟﻨﺎﺭ)
"ጥመት ደግሞ ለሣት ይዳርጋል "
ሌሎችም ምክንያቶች አሉን ኢንሸአላህ ይጠቀሣሉ

Post a Comment

0 Comments