ሶስት ምክሮች
1ኛ‐ ትክክለኛውን ጎዳና ለሳቱ
አላህ እንዲህ ይላል፦
﴿قُلْ إِنَّمَا أَعِظُكُم بِوَاحِدَةٍ ۖ أَن تَقُومُوا لِلَّهِ مَثْنَىٰ وَفُرَادَىٰ ثُمَّ تَتَفَكَّرُوا﴾ [سبأ: ٤٦]
«“የምገስጻችሁ በአንዲት ነገር ብቻ ነው!” በላቸው! ለአላህ ብላችሁ ሁለት ሁለት ሆናችሁና ለየብቻ ተነስታችሁ ከዚያ እንድታስተውሉ!…»[ሰበእ 46]
ያስተዋሉ! ተጨባጩ ዓለም እንደሚመሰክረው ብዙ ሰዎች በተሰበሰቡበት አጋጣሚ እውነታን አጣርቶ የሚያሳይ ውይይት መፈፀም እጅግ አስቸጋሪ ነው በተለይ በእምነት ጉዳይ ላይ! ምክንያቱም በአብዛኛው ንፁህ እሳቤን የሚያደፈርሱና ጭፍን ወገንተኝነትን የሚቀሰቅሱ ሁኔታዎች መንፀባረቃቸው አይቀርምና! በአንቀፁ ላይ እንደተመለከተው ሁለት ሆነው አንዱ የደረሰበትን እውነታ ለሌላው በማቅረብ በቅንነት መወያየት ለአስተውሎት አመቺ ሁኔታን ይፈጥራል! ለብቻው የሆነም ሰው ባልተረበሸ ልቦና መረጃዎችን የማገናዘብ እድል ይኖረዋል
ከዚህ ጋር አላህ ቀጥተኛውን መንገድ እንዲመራን መማፀን ሊዘነጋ የሚችል ጉዳይ አይደለም!
2ኛ‐ ጥርጣሬን ለሚያስተናግዱ
መሠረቱ የተጠናከረ ርዕሰ‐ጉዳይ ላይ ለሚነሱ አላፊ ውዥንብሮች ትክክለኛ ምላሽን አለማወቅህ/ሽ በጉዳዩ ላይ ጥርጣሬን አያጭርም! ምክንያቱም መሠረታዊ እርግጠኝነት በቅርንጫፋዊ ጥያቄ ሊናወጥ አይገባምና! በዚህ ላይ ደግሞ አንተ ልትፈታው ያልቻልከውን የጥርጣሬ ቋጠሮ ሌላ አዋቂ በአላህ ፍቃድ ይፈታዋል!
«ልቦናህን ለአላፊ ሃሳቦችና ውዥንብሮች እንደ እስፖንጅ አታድርገው! እነሱን መጥጦ ከነሱ ሌላ የሚተፋው አይኖረውምና! ነገር ግን እንደ ጠንካራ መስታወት አድርገው፦ ውዥንብሩ ከላይ በኩል ያልፋል፤ ወደ ውስጥ ግን አይዘልቅም! በጥራቱ አሳልፎ ያያቸዋል፤ በጥንካሬውም ይቋቋማቸዋል! የሚያጋጥምህን ውዥንብር ሁሉ ለልብህ የምታግተው ከሆነ ግን የውዥንብር መጠራቀሚያ ይሆናል!»
ከሸይኹ´ል‐ኢስላም ኢብኑ ተይሚይ‐ያህ ወርቃማ ምክሮች አንዱ ነው። “ሚፍታሑ ዳሪ´ስ‐ሰዓዳህ” ሊ´ብኒ´ል‐ቀይ‐ዪም (1/140) ይመልከቱ።
3ኛ‐ እውነቱን ለተረዱ
እውነትን ለማወቅ አላህ የረዳው ሰው እርሱን ሊያመሰግንና በዚያ ላይ እንዲያፀናው ሊማፀነው ይገባል። ሌሎችን በንቀት አይን ከማየትም ራሱን ሊጠብቅ የግድ ይላል።
በተረፈ እውነታውን ለማመላከት የምናደርገው ጥሪ ሁልጊዜ በጥበብና በእውቀት ላይ የተማከለ ይሁን! የተረዳ ሁሉ ሌላን ሊያስረዳ እንደማይችልም አይዘንጉ! ከፍሬ‐ቢስ ክርክር መራቅም አንድ ብልሃት ነው! ከሁሉ በላይ ውድ ንብረታችን እምነታችን ነውና እንዳይበከል፤ እንጠብቀው እንንከባከበው
አላህ ሁላችንንም ወደ ቀጥተኛው ጎዳና ይምራን!
[ከኡስታዝ ኤልያስ አህመድ ሐፊዘሁላህ “የአማኞች ጋሻ” መፅሀፍ ከገፅ 234‐236 የተወሰደ]