Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሰፍን ለማስተካከል የምንመረኮዝበት ቁርጭምጭሚት ነው እንጂ የእግር ጣትን አይደለም


ሰፍን ለማስተካከል የምንመረኮዝበት ቁርጭምጭሚት ነው እንጂ የእግር ጣትን አይደለም፡፡ ቁርጭምጭሚቶች መስመራቸውን እንዲጠብቁ አድርጎ መቆም ነው፡፡ ረጅም እና አጭር እግር እንዳለ ሁሉ ጣቶችም እንደ የሰው እግር ይበላለጣሉ፡፡ ስለዚህ የሰፍን ቀጥተኛነትና መስተካከል ያለ ቁርጭምጭሚት ማረጋገጥ ያስቸግራል፡፡ ቁርጭምጭሚትን አጠገብ ካለው ሰው ቁርጭምጭሚት ጋር ማጋጠምን በተመለከተ ሰሃቦች ያደርጉት እንደ ነበር ጥርጥር የለውም፡፡ ሰፋቸውን ያስተካክሉ የነበሩት ቁርጭምጭሚቶቻቸውን በማገጣጠም ነው፡፡ ሰፉ ቀጥ ብሎ እንዲስተካከል እያንዳንዱ ሰው ቁርጭምጭሚቱን አጠገቡ ካለው ሰው ቁርጭምጭሚት ጋር ያጋጥም ነበር፡፡ ስለዚህ እያንዳንዱ ሰው ይህንን ማድረግ አለበት፡ ነገር ግን ይህ ማለት ቁርጭምጭሚቶች እስከመጨረሻው ተገጣጥመው ይቆዩ ማለት አይደለም፡፡ ዑለማዎች እንዳወሱት ቁርጭምጭሚትን ማገጣጠም በራሱ ተፈልጎ ሳይሆን ሰፍን ለማስተካከል ነውና፡፡
አንዳንድ ሰው ከልክ ያልፋል፡፡ ይኸውም እግሩን በሰፊው ከፍቶ ቁርጭምጭሚቱን አጠገቡ ካለው ሰው ቁርጭምጭሚት ጋር ያገጣጥምና በትከሻዎቻቸው መካከል ግን ሰፋ ያለ ክፍተት ይቀራል፡፡ ይህ የሱና ተቃራኒ ነው፡፡ የሚፈለገው ትከሻዎችና ቁርጭምጭሚቶች በትክክል ትይዩ እንዲሆኑ ማድረግ ነው፡፡