Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ጤነኛው "እብድ"

ጤነኛው "እብድ"
በሐሩን አልረሺድ ኸሊፋ ዘመን በህሉል የተሰኘ አንድ ''እብድ'' ነበር። ከእለታት አንድ ቀን ''እብዱ'' በህሉል መቃብር ላይ ተቀምጦ ኸሊፋው ሐሩን አልረሺድ በአጠገቡ አለፈ። ከዚያም ሐሩን ለበህሉል በንቀት ንግግር እንዲህ አለው፡ "አንተ እብድ ሆይ! መቼ ይሁን ጤነኛ የምትሆነው?"
በህሉልም ከተቀመጠበት ተነሳና ረዥም ዛፍ ላይ ወጣ። ከዚያም ጮኽ ብሎ ፡ "አንተ ሐሩን ሆይ! አንተ እብድ ሆይ! መቼ ይሁን ጤነኛ የምትሆነው?"
አለው መልሶ
ወዲያው ሐሩንም በቅሎው ላይ እንደተቀመጠ ወደ ዛፉ መጣና " እኔ ነኝ እብድ ወይንስ መቃብር ላይ የምትቀመጠው አንተ?" አለው ለበህሉል
በህሉልም ፡ " ጤነኛውማ እኔ ነኝ" አለ
"እንዴት ሆኖ?" ብሎ ጠየቀ ሐሩን
በህሉልም ወደ ሐሩን ሕንፃዎች እያመላከተ፡ "እኔኮ ያኛው (ሕንፃ) ጠፊ መሆኑን አውቃለሁ።" ደግሞ ወደ ቀብሩ አመላከተና ፡ " ይህ ደግሞ (ቀብር) ዘውታሪ መሆኑን አውቃልሁ።" ካለ በኃላ '' ከዚያ (ከዱንያ) በፊት ይህን (አኼራዬን) ገነባሁ። አንተ ግን ያንን (ዱንያን) ገነባህና ይህንን (አኼራህን) አፈረስክ። ስለዚህ ከገንባሀው ወደ አፈረስከው መዘዋወርን ትጠላለህ። መቅረት የሌለው ጉዞ መሆኑን ከማወቅህ ጋር። " ከዚያም አስከትሎ . . " እንደው ንገረኝ እስኪ ታዲያ እብዱ ማን ነው?"
ሐሩንም በሰማው ነገር ተርገፈገፈ ፤ ፂሙ እስኪረጥብ ድረስም አለቀሰ። ከዚያም እንዲህ አለው ፡ " በአላህ ይሁንብኝ! እውነት ተናገርክ!" ከዚያም አስከትሎም " በህሉል ሆይ! እስኪ ጨምርልኝ" አለው
በህሉልም ፡ " የአላህ መፅሃፍ (ቁርአን) በቂህ ነውና እሱን ጠበቅ አድርገህ ያዘው!"
ሐሩንም ፡ "የማስፈፅምልህ ጉዳይ ይኖርሃልን?"
በህሉልም ፡ "አዎን! ሶስት ጉዳዮች ይኖሩኛል። እነዚህን ጉዳዮች ከፈፀምክልኝ አመሰግንሃልሁ" አለው
ሐሩንም፡ "ጠይቀኝ" ሲለው
በህሉል ፡ "እድሜ ልትጨምርልኝ ትችላለህን?"
ሐሩን፡ "አልችልም" ብሎ መለሰ
በህሉል፡ " ከሞት መላዕክት ልትከላከልልኝ ትችላለህን?"
"አልችልም" አለ ሐሩን
" ጀነት ልታስገባኝና ከእሳት ልታርቀኝ ትችላለህን?" ብሎ ሲጠይቅ
ሐሩን፡ "አልችልም" ብሎ መለሰ
በህሉልም እንዲህ አለ ፡ " እወቅ! አንተ ተገዢ እንጂ ንጉስ አይደለህም። በመሆኑም አንተ ዘንድ ምንም ጉዳይ የለኝም።" አለው ።
(ምንጭ ፡ ዑቀላኡል መጃኒን)