Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ቢድዓቱል ሀሰናህ

ቢድዓቱል ሀሰናህ
አንዳንድ ሰዎች ‹‹ሁሉም ቢድዓ ጥመት ነው!!›› ከሚለዉ ነብያዊ መርሆ በመውጣት ‹‹ቢድዓ ሁለት ዓይነት ነው፤ጥሩና መጠፎ›› ይላሉ!! መውሊድ ጥሩ ቢድዓ (ቢድዐቱል ሀሰናህ) ነው፡፡ የተከለከለው ደግሞ መጥፎ ቢድዓ ነው፡፡ ለዚህም ሁለት ማደናገያዎችን በመጥቀስ ቢድዓ ሀሰናህ የሚለዉን ሃሳብ ለማጠናከር ሽንጣቸውን ገትረው ይሞግታሉ፡፡
አንደኛ፡- መልዕክተኛው እንዲህ ብለዋል ‹‹በኢስላም ውስጥ የጥሩ ፈለግ(ሱና) ፈር የቀደደ ለእርሱ የዚህ ስራ ምንዳ እና ይህንን ፈለጉን ተከትሎ የሚሰራ ሰውን ሁሉ ምንዳ አለው፡፡ ይህም ከእርሱ ምንዳ ምንም ሳይቀነስ ነው›› ሙስሊም በቁጥር 1017 ከጀሪር ኢብኑ አብዲላህ አል-በጀሊይ ዘግበውታል፡፡
የመጀመሪያዉ ማደናገሪያ ምላሽ እንደሚከተለው ይሆናል፡-
1ኛ፡- ነቢዩ (ሠ.ዐ.ወ) ይህንን ሀዲስ የተናገሩበትን ምክንያት በዚሁ ሀዲስ ላይ ስናነብ ሀሳቡን በትክክል እንረዳዋለን፡፡ነገር ግን ቢድዓቱል ሀሰናህ አለ የሚሉ ሰዎች የሀዲሱን ሙሉ ሀሳብ ማስቀመጥ
ስለማያዋጣቸዉ አይጠቅሱትም፡፡ ጀሪር በዚሁ ሀዲስ መግቢያ ላይ እንዲህ ይላል ‹‹ረሱል ዘንድ ተቀምጠን እያለ ከሙደር ጎሳ የሆኑ ሰዎች መጡ፡፡ ረሱልም በሰዎቹ ላይ ባዩት እንግልትና ችግር ስሜታቸዉ ተነክቶ ፊታቸዉ ተቀያየረ…›› ከዛም ሰሃቦችን ሰደቃ አንዲሰጡ ሲያነሳሷቸው አንድ ከአንሳር የሆነ ሰሃብይ ሊሸከመዉ የከበደዉን ምግብ ከሁሉም ቀድሞ በመስጠት መዋጮዉን ጀመረዉና ለሌሎቹ አርዓያ ሆነ፡፡ ሁሉም በሰደቃ ተሽቀዳደሙ፡፡ ጀሪር ‹‹የረሱል ፊት ልክ እንደወርቅ ሲያብረቀርቅ አየሁ›› አሉ፡፡ ከዛም ከላይ የቀረበዉን ንግግራቸዉን ተናገሩ…፡፡ቢድዓ የሚባለዉ በዲን ዉስጥ አዲስ የተጨመረ ነገር ነዉ፡፡ ሰደቃ ደግሞ በሸሪዓ አስቀድሞ የተደነገገ ተግባር እንጂ አዲስ ፈጠራ አይደለም! ስለዚህ ይህ በዲኑ ውስጥ ለሚጨምሩ ሰዎች በፍፁም መረጃ ሊሆን አይችልም።
2ኛ- ነቢዩ በዚህ ሀዲስ ላይ ‹‹በኢስላም ውስጥ›› እና ‹‹ (ሰነ ሱነተን ሀሰናህ) የጥሩ ፈለግ (ሱና) ፈር የቀደደ ›› ማለታቸውን እናስተዉል፡፡
3ኛ- ይህ ሀዲስ ሰዎች የረሱትንና የዘነጉትን ሱና ህያው ማድረግን ይመለከታል፡፡ ይህንን ሀዲስ በሚገባ የሚያብራራዉ ለመነገሩ ሰበብ የሆነዉ ክስተት ቢሆንም ሀሳቡን የሚያጠናክርና ምን እንደተፈለገበት የሚያሳይ መልዕክት ያለዉ ሀዲስም አለ፡፡ቢላል ኢብኑልሀሪስ ረሱል እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ ይላሉ ‹‹ከኔ በኋላ (የሞተን) የተረሳን ሱና ህያዉ ያደረገ (እርሱን ተከትለዉ) ይህንን ሱና በሰሩበት ሰዎች ሁሉ ከእነርሱ ምንዳ ምንም ሳይቀነስ ምንዳ ያገኛል፡፡
ሁለተኛ፡- (ሰዎች የተራዊህን ሰላት ተለያይተው በሚሰግዱ ጊዜ ኸሊፋው ዑመር ተሰባስበው እንዲሰግዱ ካደረጓቸው በኋላ ‹‹ምንኛ ያማረች ፈጠራ (ቢድዓ) ናት!›› አሉ) ቡኻሪ በቁጥር 2012 ዘግበውታል
1ኛ፡-የተራዊህ ሰላት ሱና እንጂ ቢድዓ አይደለም! ነቢዩ (ሠ.ዐ.ወ) የተወሰኑ ቀናትን ሰርተው
አቁመውታል፤ ምክንያታቸውንም ተናግረዋል፡-ዋጂብ (ግዴታ) እንዳይሆንብን ፈርተው ነው ግን ከአላህ የሚተላለፈዉ ወህይ ከነቢዩ (ሠ.ዐ.ወ) እልፋት በኋላ ስለማይመጣ በዑመር ጊዜ ዋጂብ እንዳይሆንብን የሚፈራበት ምንም ምክንያት አልነበረም፤ ስለሆነም ነቢዩ (ሠ.ዐ.ወ) የጀመሩትን ሥራ ዑመር ቀጠሉት፣ ይህን ይበልጥ የሚያብራራው የሚቀጥለው ነጥብ ይሆናል፡፡
2ኛ፡-በዲናችን የተከለከለዉ ቢድዓን መስራት ነዉ እንጂ ቢድዓ የሚለውን ቃል መጠቀም አይደለም። ቢድዓ እንደሌሎች አንዳንድ ቃላት ሸሪአዊና ቋንቋዊ ትርጉም ያለው ቃል ነው።ተቋርጦ እንደ አዲስ በመጀመሩ፤ ዑመር የፈለጉት ቋንቋዊ ትርጉሙን ነው።የሰሩትም ሥራ ሱናና መሰረት ያለው እንጂ አዲስ ፈጠራ አይደለም።
3ኛ፡-ዑመር የሠሩት ሥራ በሰሀቦች ሁሉ ስምምነት የፀደቀ የኹለፋዎች ፈለግ በመሆኑ በሸሪዓ ቢድዓ አይባልም!
እንደዚሁም ከላይ በተጠቀሱት ማስረጃዎች የተኮነነው ቢድዓ በዲን ውስጥ የሚተገበረውን የቢድዓ ዓይነት እንጂ አንዳንድ ሰዎች ‹አዲስ ፈጠራ ማምጣት ይቻላል!› ብለዉ ለመሞገት ሲፈልጉ የሚጠቅሷቸውን የቴክኖሎጂ የፈጠራ ውጤቶች አይደሉም።ነቢዩ (ሠ.ዐ.ወ) በዋነኝነት ለማስተማር የተላኩት እነዚህን ዝርዝር የዱንያ ጉዳዮች አይደለም፤ ለመዲና ገበሬዎችም ይህንን ምላሽ ሰጥተዋል፡-
“ስለ ዱንያ ጉዳያችሁ እናንተ ይበልጥ ታውቃላችሁ!” ስለዚህ ቁርዓንን በአንድ ጥራዝ ማስቀመጥ፣
የእስር ቤቶችን ማዘጋጀት፣ ስፒከርን (የድምፅ ማጉያ) መጠቀም የመሳሰሉት በመልእክተኛው ዘመን ባይከሰቱም ወጥ የዒባዳ ተግባራት ሳይሆኑ ወደ ኢባዳ የሚያዳርሱ አጋዥ መዳረሻዎች ስለሆኑ ነው።እነዚህ ደግሞ (መሳሊህ ሙርሰላ) ይባላሉ፣ ከቢድዓ ጋር በፍፁም አይገናኙም፡፡
------------------
🔊 Watch "ጥሩ እና መጥፎ ቢድዓ (ኢልያስ አህመድ) Refuting Ahbash 3 (Amharic)" on YouTube
https://www.youtube.com/watch…
🔊 Watch "ቢድዓ ሁሉ ጥመት ነው!! (ኢልያስ አህመድ) Refuting Ahbash 4 (Amharic)" on YouTube
https://www.youtube.com/watch…
© ተንቢሀት