Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አብደላህ አልሀበሺ እውነታውን ሲያምን!! መውሊድን የማክበር ሀሳብ ከክርስቲያኖች ...

አብደላህ አልሀበሺ እውነታውን ሲያምን!!
መውሊድን የማክበር ሀሳብ ከክርስቲያኖች ገና የመጣ መሆኑን ተናግሯል፤ የ «ኢዝሀሩል አቂደቲሱኒያህ» የድምፅ ማብራሪያ ካሴት ቁ.9 የመጀመሪያው ክፍል ላይ የመውሊድን አጀማመር አስመልክቶ ሲናገር፤ መውሊድን ለመጀመሪያ ጊዜ ያከበረው የኢርቢሉ ንጉስ ሙዘፈር እንደሆነ እና አጀማመሩም ክርስቲያኖች የመሲህን ልደት ሲያክሩ አይቶ ሙሀመድ ﷺ በዚህ አለም ብቅ በማለታቸው አላህን ሊያመሰግን እንደሆነ ያብራራል።
እኛም እውነታዉን በማመኑ እያመሰገነው ተከታዮቹን ነጥቦች እንጠቁማለን፤
1) መውሊድን በዓል አድርጎ ማክበር መልእክተኛው ﷺ ወደዚህ አለም በመምጣታቸው ለአላህ ምስጋና የማቅረቢያና ውዴታንም የመግለጫ መንገድ ከሆነ ከሰሀቦችና ታቢዒዮች ዘመን ጀምሮ የኖሩ ምርጥ የኢስላም ልጆች ሳያውቁት በ630 ዓ.ሒ የሞተው ንጉስ ተገለጠለትን?
2) በላጭ ትውልዶች የተባሉት ቀደምቶች ይህንን መውሊድ ያልፈፀሙት አላህን የማመስገኛ መንገድ መሆኑን ክርስቲያኖችና አህባሾች እንዳወቁት እነሱ ማወቅ ተስኗቸው ነውን? ይህንን ካላችሁ ጥመታችሁ ግልፅ ወጣ አለያ ወደነሱ መንገድ ተመለሱ።
3) ይህ የተምታታ ግንዛቤ የሚያሳየው ክርስቲያኖች የኢሳን ልደት በማክበራቸው አላህን በማመስገን ከምርጦቹ ትውልዶች መቅደማቸውን ነው። ይህ ደግሞ ባጢል ነው።
4) መልእክተኛው ﷺ በብዙ ሀዲሶች፤ በኢስላማዊ እንድንኮራ ማዘዛቸውና አይሁዶችና ክርስቲያኖችን አርአያ እንዳናደርግ አበክረው መምከራቸውን ለምን ዘነጉ?
ሙስሊም ከካፈር ጋር መመሳሰል እንደሌለበት በብዙ አያውቁምን??
መልዕክተኛው ﷺ እንዲህ ብለዋል፤
عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيّ، قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللّهِ صلى الله عليه وسلم "لَتَتّبِعُنّ سَنَنَ الّذِينَ مِنْ قَبْلِكُمْ. شِبْراً بِشِبْرٍ، وَذِرَاعاً بِذِرَاعٍ. حَتّىَ لَوْ دَخَلُوا فِي جُحْرِ ضَبَ لاَتّبَعْتُمُوهُمْ" قُلْنَا: يَا رَسُولَ اللّهِ آلْيَهُودُ وَالنّصَارَىَ؟ قَالَ "فَمَنْ؟".
[رواه البخارى ومسلم ].
አቢ ሰዒድ አልኹድሪይ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ አሉ፤ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ አሉ፤
«ከናንተ በስተፊት የነበሩትን (ህዝቦች) ፈለግ ስንዝር በስንዝር እርምጃ በእርምጃ ትከተላላችሁ። የድብ ጉድጓድ እንኳ ቢገቡ ትከተሏቸዋላችሁ።»
የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ሆይ ይሁዶችንና ነሳራዎችን ነው ? «ሌላ ማንን ነው!» (እነሱን ነው እንጂ) አሉ።
ይህንን ነብያዊ ትንቢት ባንሰማ ኖሮ በሙዘፈር ድርጊት ተገርመን አናበቃም ነበር።
5 )አላህ ዲናችን የተሟላ አድርጎት ሳለ፤ ክርስቲያኖች ሰሩት ብለን በዲናችን የሌለን ነገር እንፈፅማለን??
(ٱلْيَوْمَ أَكْمَلْتُ لَكُمْ دِينَكُمْ وَأَتْمَمْتُ عَلَيْكُمْ نِعْمَتِى وَرَضِيتُ لَكُمُ ٱلْإِسْلَـٰمَ دِينًۭا ۚ فَمَنِ ٱضْطُرَّ فِى مَخْمَصَةٍ غَيْرَ مُتَجَانِفٍۢ لِّإِثْمٍۢ ۙ فَإِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٌۭ رَّحِيمٌۭ) المائدة 3
«ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለእናተ ሞላሁላችሁ። ጸጋዬንም በናንተ ላይ ፈጸምኩ። ለእናንተም ኢስላምን ከሃይማኖት በኩል ወደድኩ።»
አልማኢዳህ 3
በእውነትም የዛኔ ዲን ያልነበረ አሁን ዲን ሊሆን አይችልም።
አኹኩም አቡጁነይድ
ረቢኡልአወል 9/1436 ዓ.ሒ