Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ፍንዳታ ሙፍቲዎች!


ፍንዳታ ሙፍቲዎች!
ለትውስታ ያክል
ሰሞኑን የሆኑ ወጣቶች “ኢስላማዊ የጥበብ ድግስ” ብለው በሃገር ፍቅር ቲያትር ቤት የዛዛታና አልባሌ ነገሮች ድግስ አዘጋጅተው እንደነበር ይታወቃል፡፡ በርግጥ ጥፋታቸውን ኢስላማዊ ቅብ መቀባታቸው አሳዘነን እንጂ ያዘጋጁበት ቦታ ለድርጊታቸው የሚመጥን ነው፡፡ በርግጥ አሁን ስለሱ ላወራ አይደለም፡፡ ነገር ግን ለነዚህ ዛሬ ለሚታዩት “ኢስላማዊ” የጥበብ ድግስ፣ “ኢስላማዊ” ፊልም፣ “ኢስላማዊ” ድራማ፣ … መሰረት ከጣሉት ቀዳሚዎች ውስጥ አንዱ ሐሰን ታጁ ነው፡፡ ለረጅም አመታት ሙዚቃን ከ“ጠርዘኞች” ነፃ ሊያወጣ ሰይፉን በመሳል በመፅሀፍ፣ በጋዜጦች፣ በተለያዩ መድረኮች ሲፋለም ነው የኖረው፡፡ ከጥቂት አመታት በፊት ሸገር ሬዲዮ ስለሙዚቃ የሀይማኖት ሰዎችን አቋም ለመስማት ፕሮግራም ሲያዘጋጅ ከኦርቶዶክስ ክርስትና በኩል አንድ ቄስ ቀርቦ 99 በመቶ ዘፈን በመፅሃፍ ቅዱስ የተወገዘ ነው ብሎ ፍርጥም ብሎ ሲሟገት ኢኽዋኒው ሐሰን ታጁ ደግሞ ኢስላምን ወክሎ ሙዚቃን ከነዘር ማንዘሯ ሐላል አደረጋት፡፡ ሙዚቃን በተመለከተ አንድ መካከለኛና ሁለት ፅንፈኛ አቋሞች እንዳሉ አዲስ ግኝት ነገረን፡፡ “መካከለኛው” እሱ ያለበት ሙዚቃን የሚፈቅደው አቋም ነው፡፡ በሱ አመላለስ የልብ ልብ የተሰማው ጋዜጠኛም “እንግዲያው ሙዚቀኞቹን ቀጥታ ለመመልከት የምሽት ክበቦች መገኘትስ እንዴት ነው?” ብሎ ጠይቆት ነበር፡፡ የሴትና የወንድ ቅልቅል ስላለ እዚያ መገኘት አይቻልም ብሏል ጥንቁቁ ሐሰን፡፡ ድንቄም፡፡ “መቀላቀል ከሌለስ የሙዚቃ ባንዶች ላይ መገኘትም፣ መሳተፍም፣ መዝፈንም፣... ይፈቀዳል ማለት ነውን?” ካላችሁ ጥያቄችሁን ይዛችሁ ወደ ሐሰን ታጁ ጎራ በሉ፡፡ “የምላስ ጣጣ” የምትለዋን የሱን መፅሀፍ አስታውሱ፡፡ ከዚያም ሙዚቃን መፍቀዱን ጨምሩና ምርመራ አድርጉ፡፡
ታዲያ ያኔ ሀሰን ታጁ ኢስላምን ወክሎ ስለ ሙዚቃ መግለጫ መስጠቱ ሲሰማ ብዙ ሙስሊሞች ተሳቀቁ፡፡ በዚህ ጉዳይ ከቄሱ እንኳን ሳይሻል ሲቀር ተሸማቀቁ፡፡ “ሞኝ ባያፍር የሞኝ ዘመድ ያፍር” አይደል ብሂሉ? ግን እሱ ምን ያርግ? እስፖንጅ የያዘውን አይደል የሚተፋው? በእርግጥ በዲን ላይ ንግድ ይደብራል፡፡ ማጭበርበር ሲታከልበት ደግሞ ያንገሸግሻል፡፡ ብቻ በተለያዩ ኢስላማዊ ጋዜጦች በሙዚቃ ወዳጆችና ጠላቶች መሀል “ሙዚቃ ሐላል ነው”፣ “አይ ሐራም ነው” በርካታ ንትርኮች ተከታተሉ፡፡ “ሐሰን ታጁ ሙዚቃ ሐላል ነው አለ” ተብሎ በሰፊው ተወራ፡፡ የመልስ ናዳ ከያቅጣጫው ወረደ፡፡ ከዐሊሙም ከጃሂሉም ከደጋፊውም ከተቃዋሚውም ብዙ ንትርክ ተዥጎደጎደ፡፡ ሐሰን ተርበደበደ፡፡ ስሙን እየቀያየረ ያቅሙን ለማለት ተንገዳገደ፡፡ እንደለመደው ርዕሱን ጥሎ “ፍየል ወዲያ ቁዝምዝም ወዲህ” ነጎደ፡፡ ዐሊም “አክባሪው” ሐሰን ደሊል መስሎት እንደለመደው ዐሊሞችን መዘርጠጡን ወደደ፡፡ ሐሰን ማጣፊያው ሲያጥረው ወደመጨረሻ ደሊሉ ተጠጋ፡፡ አምቆ ይዞ ሲበሳጭ ብቻ ወደሚገነፍልበት ደሊሉ፡፡ የሰዑዲ ዐሊሞችን በነገር ወጋ፡፡ ከሀገር ውስጥም ስሙን እየቀያየረ ነካካ፡፡ በርግጥ ሐሰንን በቅጡ ለሚያውቀው ይሄ አካሄዱ ብዙም እንግዳ አይደለም፡፡ ደግሞስ ምን ያርግ? ድመት እራሷ ቤት ዘግተው ዱላ ካነሱባት ግራ ቀኝ ታያለች፡፡ ለማምለጥ የተቻላትህን ሁሉ ታደርጋለች፡፡ ማምለጫ ቀዳዳ ከሌለ ግን ነብር ልትሆን ያቅሟን ትጣጣራለች፡፡ አካሏን ነፋፍታ፣ ድምፅዋን ቀያይራ፣ ዐይኗን ጎልጉላ፣ ፀጉሯን አቁማ፣... የሚያስፈራ ድምፅ ታወጣለች፡፡ ለአካሏ በማይመጥን ወፍራም ድምፅ “ዋ..ው..!!” ትላለች፡፡ ታዲያ ሐሰንስ ሌላ ምን አረገ? ይህ የሆነው እንግዲህ ከሸገሩ ፈትዋ በኋላ ነው፡፡ የትችት እሩምታ ከያቅጣጫው ከተከታዮቹም ጭምር ከተሰማ በኋላ፡፡
በሸገሩ ፈትዋ ላይ ግን አደገኛ መርዞችን ነው የረጨው፡፡ አደጋውን የሚያከፋው ደግሞ የቁርኣን አያዎችንና ሐዲሶችን ያለቦታቸው መጠቃቀሱ ነው፡፡ ይህ አካሄድ በተለይም መሀይማን ዘንድ የሚፈጥረውን አንድምታ አስቡት፡፡ ምክንያቱም መድረክ ይዞ በኢስላም ስም የተናገረ ሁሉ ዓሊም የሚመስላቸው ቀላል አይደሉምና፡፡ በተለይ በተለይ ደግሞ ስሜታቸውን የሚከተሉ የሙዚቃ አፍቃሪያን ዘንድ ምን አይነት አቀባበል እንደሚያገኝ ገምቱት፡፡ እነኚህ ስሜታውያን ስሜታቸውን የሚያስደስት ደሊል መሳይ ነገር ካገኙ የሌላኛውን ወግን ማስረጃ መስሚያ ጆሮ አይኖራቸውም፡፡
አሁንም ጉዳዩን የበለጠ የሚያከፋው የሐሰን አቀራረብ ነው፡፡ ሐሰን ሙዚቃን በተመለከተ ሰዎችን ለሶስት ከፍሏል፡፡ ሁለት ፅንፎችና አንድ መካከለኛ አካሄድ፡፡ ይሄ የሁልጊዜ አካሄዱ ነው፡፡ የአስተሳሰብ ሽብር መፍጠር፡፡ እሱ የቆመለትን ሰንካላ አቋም የማይነቃነቅ ሐቅ ማድረግ ሲሻው እሱ የቆመበትን መካከለኛ የሚል ካፖርት ያለብሰዋል፡፡ የሚቃወሙት ጠርዘኛ ጭራቆች አድርጎ ለመሳል፡፡ ይሄ ከቀርዳዊ የኮረጀው ቆሻሻ “ታክቲክ” ነው፡፡
ታዲያ እዚህም ላይ ሀስዬ “መካከለኛ ነው” የሚለን መንገድ እሱ የሚጓዝበት ሙዚቃን የሚፈቅድበት መንገድ እንደሆነ ቀድሞ መገመት ይቻላል፡፡ ሁለቱን ፅንፎች ሐሰን ይግለፃቸው
‪#‎አንዱ‬-ፅንፍ-ሙዚቃን-የሚከለክለው-እይታ-ነው፡፡
- ሌላኛው ፅንፍ ደግሞ ሐሰን ታጁ የራሱን ሀሳብ መካከለኛ ለማድረግ ሲል ብቻ የሚስለው ምናባዊ ‪#‎ሀሳባዊ‬ አቋም ነው፡፡
በርግጥ የሐሰንን የሸገር ፈትዋ ጠበቅ አድርገን ከፈተሽነው የንግግሩ እንድምታ “ሙዚቃ ሐላል ነው” ከማለትም በላይ ይሻገራል፡፡ “ደግሞ ዋጂብ ነው ብሏል እንዳትለን” አላችሁኝ እንዴ? ኳስ በመሬት፡፡ እንደሱ አልወጣኝም፡፡ አፌን ሞልቼ ግን አይልም አልልም፡፡ እንዳውም እኔ ሐሰን ታጁ ምንም ቢል አይገርመኝም፡፡ እንዳውም እንዳውም “የህዝብ ውዴታ ያተርፍልኛል” ብሎ ከገመተ ሐሰን ምንም ቢሆን “አይልም” ብየ አፌን ሞልቼ መናገር ይከብደኛል፡፡ እናም ስመለስ ሐሰን በሸገሩ ፈትዋው ላይ “ሙዚቃ ሐላል ነው” ከማለት በላይ ነው የተናገረው ብያለሁ፡፡ “እንዴት?” ማለት ጥሩ፡፡ ሙዚቃን ሐላል ለማድረግ የሄደበትን አካሄድ አስታውሱ፡፡ ስለ ተፈኩር የሚያትቱ አያዎችን ማተቱን ያዙ፡፡ “ሙዚቃ ማለት ውበትን ማድነቅ ነው” ማለቱን ጨምሩ፡፡ “ቁርኣን በዜማ ነው የሚቀራው፣ አዛንና ኢቃማ በዜማ ነው የሚደረጉት ማለቱን ደምሩ፡፡ ታዲያ የዚህ ሁሉ ድምር ውጤት “ሐላል ነው” ላይ የሚቆም ነው? በጭራሽ! “ሐላል” ማለት እኮ “አጅርም” ወንጀልም የሌለው ማለት ነው፡፡ ታዲያ አዛንና ኢቋማ ማድረግ፣ በቁርኣን ድምፅን ማሳመር “አጅርም” ወንጀልም የሌለው ተግባር ነው እንዴ? በርግጥ እሱ የፈለገው ዜማ በራሱ የተከለከለ አይደለም ለማለት ነው፡፡ ግን ስለተፈኩር ማውራቱን ምን አመጣው? ብቻ ስገምት እንዲህ አይነት አካሄድ የሄደው ሙዚቃን ከሐራምነት አውጥቶ፣ ከውዝግብ ርእስ አሻግሮ የማይነቃነቅ “ሐላል” ለማድረግ ይመስለኛል፡፡
ያ ሁሉ ሲባል ምንም ደንገጥ አላለም፡፡ እንዳውም እልህና ትእቢት ነው የጨመረው፡፡ ምክር መቀበሉ ቀርቶ፣ አሊሞችን ማንቋሸሽ፡፡
ፍንዳታ ሙፍቲዎች
ለቅልቅሉ እንጂ ዳንስ ካልታገደ
ሀራምነት ቀርቶ ዘፈን ለተፈኩር እንዲያ ከፈየደ
ምናለ ቢኖሩን ከኢኽቲላጥ የራቁ የዳንስ ምሽቶች?i
> > >>>>>>>>>>>>>> ሙዚቀኛ ሸይኾች?i
>>>>>>>>>>>>>>>>>> አርቲስት ኸጢቦች?i
ምናለስ ቢኖሩን “አንቱ” የተባሉ ዘፋኝ ሰባኪዎች?i
>>> ሰፋ ቦርቀቅ ያሉ ተራማጅ ሙፍቲዎች?i
>>> ዲጄ ሙአዚኖች ኮሜዲያን ኢማሞች
>>> ምንድን ነው ማካበድ ምንድን ነው መወጠር?i
>>> ባይሆን ይራቁ እንጂ ከምላስ ጣጣና ከትርፍ ንግግር፡፡?i
አዋጅ በሬዲዮ ገብር በጋዜጣ
አይበቃም ይደገም በመፅሀፍ ይውጣ
ህዝቡ ለዘመናት ተሸውዷልና
ይስማ ይዝፈን ይውጣ ይጨፍር ይዝናና፡፡
ተቃዋሚ ካለ ጠባብ ነው ጠርዘኛ
ደሊል ከበዛ ግን ይፈለጋል ዳኛ
“ልዩነት ራህማ ነው” እያለ ሚያስተኛ፡፡
ሙሉ አልበሙ ቢቀር በነጠላ ዜማ መንፈስ የሚያድሱ
በተስረቅራቂ ድምፅ በተውረግራጊ አካል ሰው እያፈዘዙ
ምናለ ቢጣሩ ልብን አለስልሰው አይን እያስለቀሱ?i
>>> >>> >>> ካልተቀላቀሉ መጠጡን ካልጠጡ
ምናለስ ቢኖሩን “ናይት ክለብ” ገብተው እያቀነቀኑ “ፈትዋ” የሚሰጡ?i
በጊታር ታጅበው ማሲንቆ እየመቱ ጥበብ የሚያጠጡi
አታሞ እየመቱ “ራፕ” እየዘለሉ ሰውን የሚያቀኑi
ዘመናይ ቃዲዎች፣ኢማሞች ዱዓቶች ፅንፍ የሰለጠኑi
የታሉ ሞዴሎች መቼ ነው የምናይ ራቀብን ዘመኑ?i
“ዋቂዕ” የገባቸው “ሂክማ” ያጠለቁ ኡማን የሚያድኑi
ጥዑም ዜማ ሰምተው ምላሽ የማይሰጡ
ከለዘብተኛው ወንዝ “ገር” ውሀ ይጠጡi
ወደኛ ይውረዱ ቡራኬ ይውሰዱi
ቀሽት ነው መንገዱ ይመስጣል ሙዱi
መምሬንም ያዙ በዚያው በመንገዱ
አካብደዋልና ያው እንደለመዱi
ይህን ካልፈቀዱ ይህን ካላግራሩ
“ዲኑ ገር ነው” ማለት የታል ቁምነገሩ?i
ሙስሊሙ ወንድሜ ዜማ የለቀቅከው
ሀራም ሲሉ ሰምተክ የተሸማቀቅከው
ቀና በል ካንገትህ ከኛ ጋር ሌላ ነው
ሌላው እንኳን ቢቀር ቢያንስ ቢያንስ ሐላል ነውi
ሬዲዮ ጋዜጣው መፅሀፍ የፃፍነው
የዚህ ሁሉ ልፋት ትርፉ ምን ሊሆን ነው?
>>> ስለዚህ ቀና በል አዝናና እንዳትሰጋ
>>> “ትርፍ ወሬ” ግን ቀንስ እንዳትዘናጋ፡፡
ሞዴሊስትዋ እህቴ ራቁት ኢኽቲላጥ ቢሉሽ
አንቺ እንኳን በሙያሽ ኢስላምን አስጠራሽ
>>> ጭንቀትሽ ግልፅ ነው ያሳስባል በጣም
>>> ቢሆንም ታገሺ ተስፋ አይቆረጥም
የሚፈቅድ “ሙፍቲ” ፈልገን ፈልገን ፈልገን አናጣም!!!!
(ኢብኑ ሙነወር)