Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ተየሙም



ተየሙም
ተየሙም ማለት የዓረብኛ ቋንቋ ትርጉሙ መፈለግ ማለት ሲሆን ሸሪዓዊ ትርጉሙ አላህን ለማምለክ በንፁህ መሬት ሸሪዓው በደነገገው መልኩ እጅና ፊትን ማበስ ማለት ነው፡፡
የተየሙም ሸሪዓዊ ድንጋጌና ማስረጃው:-
ተየሙም አላህ ለባሮቹ ገር ያደረገው ድንጋው ሲሆን የነብዩ ህዝቦች ከሌላው የሚለዩበት መለያ ነው፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡-
‹‹እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ወደ ሶላት በቆማችሁ (ለመቆም ባሰባችሁ) ጊዜ ፊቶቻችሁን፣ እጆቻችሁንም እስከ ክርኖች እጠቡ፡፡ ራሶቻችሁንም (በውሃ) አብሱ፡፡ እግሮቻችሁንም እስከ ቁርጭምጭሚቶች (እጠቡ)፡፡ (ሴት ጋር በመገናኘት ወይም በሌላ ምክንያት «ጀናባ») ብትኾኑ (ገላችሁን) ታጠቡ፡፡ በሽተኞች ወይም በጉዞ ላይ ብትኾኑም ወይም ከእናንተ አንዳችሁ ከዓይነ ምድር ቢመጣ ወይም ሴቶችን ብትነካኩና ውሃን ባታገኙ ንጹሕን የምድር ገጽ አስቡ ፡፡ ከሱም ፊቶቻችሁንና እጆቻችሁን አብሱ፡፡ አላህ በእናንተ ላይ ምንም ችግር ሊያደርግ አይሻም፡፡ ግን ታመሰግኑ ዘንድ ሊያጠራችሁና ጸጋውን በእናንተ ላይ ሊሞላ ይሻል፡፡››
(አል ማኢዳህ 6)
ነብዩም (ሠለላሁ ዓለይሒ ወሠለም) እንዲህ ብለዋል
“ውሃ ለአስር አመታት ባታገኝ እንኳን ንፁህ መሬት በቂህ ነው፡፡ ውሃ ስታገኝ ግን ገላህን አስነካው፡፡”(አቡዳውድና ቲርሚዚይ ዘግበውታል)
በሌላም ሀዲስ እንዲህ ብለዋል
“መሬት ለእኔ መስገጃና ጠሃራ ማድረጊያ ተደርጎልኛል፡፡” (ቡኻሪና ዘግበውታል)
ተየሙም መስፈርቶቹ ከተሟሉ በሸሪዓው የተፈቀደ ስለመሆኑና የውሃን ጠሃራ ተክቶ በውሃ ጠሃራ ሊሰሩ የሚችሉ ለምሳሌ ሰላት፣ ካዕባን ጠዋፍ ማድረግ፣ ቁርአን ማንበብና ሌሎችም በተየሙም ሊፈፀሙ እንደሚችሉ ዑለማዎች ሁሉም ተስማምተውበታል፡፡
በመሆኑም ተየሙም ሸሪዓዊ ድንጋጌ ስለመሆኑ ቁርአን ሀዲስና የኡለማዎች ስምምነት (ኢጅማዕ) መረጃ ሊሆኑ ችለዋል ማለት ነው፡፡
የፌስ ቡክ ገፃችንን ለማግኘት…
www.facebook.com/easyfiqh
ሼር ማድረግ እንዳይረሱ!