የተየሙም መስፈርቶችና እንዲፈቀድ የሚያደርጉ ምክንያቶች
ውሃን በማጣት ወይም ህመምን ወይም ደግሞ ከባድ ብርድን በመፍራት ውሃን መጠቀም ካልተቻለ ተየሙም ማድረግ ይፈቀዳል፡፡ ለዚህ ማስረጃ ዒምራን ኢብን ሁሰይን ባስተላለፉት ሀዲስ ነብዩ (ሠለላሁ ዓለይሒ ወሠለም) እንዲህ ብለዋል “ንፁህ በሆነ መሬት ተየሙም ካደረግክ በቂ ነው፡፡” ወደፊት በዚህ ዙሪያ ተጨማሪ ማብራሪያ ይኖረናል፡፡
ተየሙም ትክክለኛ እንዲሆን የሚከተሉትን መስፈርቶች ሟሟላት ይኖርበታል፡፡
1. ኒያህ፦ ሰላትን ለመስገድ እንዲያስችል በልብ ማሰብ ማለት ሲሆን ኒያ በሁሉም የአምልኮ ስርዓቶች ላይ መስፈርት ነው፡፡
2. ሙስሊም መሆን፦ ካፊር ተየሙም ቢያደርግ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ ምክንያቱም ተየሙም ዒባዳ (አምልኮ) ነው፡፡
3. አዕምሮ ጤናማ መሆን፦ አዕምሮውን ያጣ ለምሳሌ በእብደት ወይም በአዙሪት ራሱን የሳተ ተየሙሙ ትክክል አይሆንም፡፡
4. የመለየት እድሜ የደረሰ፦ ከሰባት አመት በታች ከሆነ ተየሙሙ ትክክል አይሆንም፡፡
5. ውሃ ማጣት፦ አላህ እንዲህ ብሏል፡-
‹‹ውሃን ባታገኙ ንጹሕን የምድር ገጽ አስቡ›› (አል ማኢዳህ 6)
ነብዩም (ሠለላሁ ዓለይሒ ወሠለም) እንዲህ ብለዋል
“አስር አመት እንኳን ውሃ ቢያጣ የሙስሊም መፅጂያ ተየሙም ነው፡፡ ውሃ ካገኘ ግን አካሉን ያስነካው ይህ ለእርሱ የተሻለ ነው፡፡” (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)
ውሃን በመጠቀሙ ህመሙ የሚባባስ ወይም ፈውሱን የሚያዘገየው ከሆነም ውሃን ትቶ ተየሙም ማድረግ ይችላል፡፡
አላህ እንዲህ ብሏል፡-
“በሽተኞች ብትኾኑ”
ነብዩም (ሠለላሁ ዓለይሒ ወሠለም) በቁስሉ ምክንያት ስለሞተው ሰው እንዲህ ብለዋል
“ገደሉት አላህ ይግደላቸውና ካላወቁ አይጠይቁም እንዴ? ያለማወቅ መድኃኒት እኮ መጠየቅ ነው፡፡”
እንዲሁም ውሃን ከተጠቀመ የሚጐዳው የሆነ ከባድ ብርድ ቢኖርም ተየሙም ማድረግ ይቻላል፡፡ ለዚህ ማስረጃ ዓምር ኢብን አል ዓስ “ለዛቲ ሰላሲል” ዘመቻ በተላከበት የገጠመውን ሲናገር እንዲህ ይላል “በአንድ ብርድ ሌሊት በተኛሁበት የፍትወት ጠብታ ፈሰሰኝና ከታጠብኩ እንደምጐዳ ስላሰብኩ ተየሙም አድርጌ ጓደኞቼን ሱብሂ አሰገድኩ፡፡” (አህመድ አቡዳውድና ዳረቁጥኒይ)
6. ንፁህ በሆነና ባልተነጀሰ አቧራማ አፈር ማድረግ፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል፡-
‹‹ንጹሕን የምድር ገጽ አስቡ ፡፡ ከሱም ፊቶቻችሁንና እጆቻችሁን አብሱ፡፡›› (አል ማኢዳህ
ኢብኑ አባስ እንዲህ ብለዋል “الصعيد ” ማለት የእርሻ አፈር ሲሆን “الطيب ” ደግሞ ጠሃራ የሆነ ማለት ነው፡፡ አፈር ካልተገኘ ግን በጠጠር ወይም በድንጋይ ተየሙም ማድረግም ይቻላል፡፡ ምክንያቱም አላህ እንዲህ ብሏል፡-
‹‹አላህንም የቻላችሁትን ያክል ፍሩት›› (አል ተጋቡን 16)
#ፊቅህን_ለመረዳት
የፌስ ቡክ ገፃችንን ለማግኘት…
www.facebook.com/easyfiqh
ሼር ማድረግ እንዳይረሱ!