"ተመይዩዝ"— ትኩረት የተነፈገው ሐቅ
የሰለፍያ ደዕዋ አንዱ መታወቂያ ተመይዩዝ ነው፣ የዐቂዳ ልዩነት ካላቸው አፍራሽ ሃይሎች ጋር አለመጋፋት። እራስን ችሎ መቆም። መልለየት። ዐቂደቱል በራእ ከካፊር ጋር ብቻ አይደለም፣ በኢስላም ስም ከሚንቀሳቀሱ የጥመት አንጃዎችም ጭምር እንጂ። ባይሆን ሚዛን ትጠብቃለህ። ማለትም ከነሱ አንፃር የሚኖርህ አቋም ባለባቸው ጥፋት ልክ ይሆናል ማለት ነው። እንጂ ሚዛን ትጠብቃለህ ማለት ትላንት ከነበረህ አቋም ትንሸራተታለህ፣ ትላንት ስታወግዛቸው የነበሩ አካላትን ከጥፋታቸው ሳይመለሱ ታደንቃለህ ማለት አይደለም። ሚዛን ትጠብቃለህ ማለት መሰረታዊ የአህሉ ሱንና አቋሞችን ለድርድር ታቀርባለህ ማለት አይደለም። ይሄ ግልፅ ነው።
ተመይዩዝ ብዙ ትርፍ አለው። ለምሳሌ ያክል
① ተመይዩዝ አብሮ በመሰለፍ ሊከተል ከሚችል የአቋም መሟሸሽ ያተርፋል። መቼስ በጋራ መድረክ ላይ ሙብተዲዖችን ማውገዝ አይቻልም።
② ተመይዩዝ ወደ ሙዳሀና (መመሳሰል) ከመውረድ ይጠብቃል። አብረህ ስትሆን ግን "እከክልኝ ልከክልህ" ፖሊሲ በቦታው ይነግሳል።
③ ተመይዩዝ ተራው ሙስሊም ዘንድ በአህሉ ሱንና እና በቢድዐ አንጃዎች መካከል ያለው ልዩነት በግልፅ እንዲታይ ያደርጋል። አብሮ መጓዝ ሲኖር ግን የአቋም ልዩነቶችንም፣ ጤነኛና በሽተኛ አካሎችንም መለየት አይቻልም። ይሄ ከባድ አደጋ ነው። ለምሳሌ ከኢኽዋኖች ጋር ብትሰለፍ ሙስሊሙን በጅምላ የሚያከፍረው፣ ሶሐባ የሚያብጠለጥለው፣ የአላህን ከዐርሹ በላይ መሆን የሚያስተባብለውን ሰይድ ቁጥብ ሲያወድሱ ያንተም አቋም ተደርጎ እንዲታሰብ ያደርጋል።
④ ተመይዩዝ የጥፋት አንጃዎችን ጭፍራ ከማድመቅ፣ ሃይላቸውን ከማጠናከር ያቅባል።
⑤ ተመይዩዝ ለአህሉ ሱንና የጥንካሬ መንሰኤም ነው። ከቢድዐ አንጃዎች ጋር አብረህ የምትሰለፍ ከሆነ ሃይላቸው ሀይልህ፣ ህብረታቸው ህብረትህ እየመሰለህ በከንቱ ትደክማለህ። ከነሱ ተነጥለህ እራስህን ችለህ ስትቆም ግን መፍተሄ የምትፈልገው፣ አንድነትህን የምታጠናክረው ከመሰሎችህ ጋር ነው። መሰረታዊ መርሆዎችህን ሊንድ ከተሰለፈ አካል ጋር ሆነህ ደካማ ጎንህን አታሳይም። ሴራ ለሚጠነስሱ አካላት እራስህን አታመቻችም።

ተመይዩዝ ማለት እራስን ከማህበረሰብ ማግለል አይደለም። ስለ ተመይዩዝ ስናወራም ከማህበረሰብ ወደ ማግለል እየተጣራን አይደለም። ይሄ የተክፊሮች አካሄድ ነው። ተመይዩዝ ከህዝብ ሳይሆን ከቢድዐ ተጣሪዎች እራስን ማግለል ነው። ያለ ተመይዩዝ የሱንናን የበላይነት እውን ማድረግ አይቻልም። ይህ የሱንና ዑለማዎች አቋም ነው። ለምሳሌ ሸይኽ ሙቅቢል ኢብኑ ሃዲ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ:–
ولن تقام سنة رسول الله صلى الله عليه وعلى آله وسلم إلا بالتميّز،
"የአላህ መልእክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወዐላ ኣሊሂ ወሰለም ሱንና በመልለየት እንጂ አትቆምም።" (ቱሕፈቱል ሙጂብ: 85)

«وننصح أهل السنة أن يتميزوا …، فإنّهم لن يستطيعوا أن ينشروا سنة رسول الله صلى الله عليه وعلى آله وسلم إلا بالتميّز وإلا فالمبتدعة لن يتركوهم ينشرون السنة» اهـ «تحفة المجيب على أسئلة الحاضر والغريب» (ص: 208)
"የሱንና ሰዎችን የምንመክረው እንዲለዩ ነው። … ምክንያቱም የአላህ መልእክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወዐላ ኣሊሂ ወሰለም ሱንናን በመልለየት እንጂ ሊያሰራጩ አይችሉምና። ካልሆነ ግን ሙብተዲዖች ሱንናን ሲያሰራጩ አይተዋቸውም።" (ቱሕፈቱል ሙጂብ: 208)
« وأنصح الإخوة السلفيين أن يبتعدوا عن هؤلاء الحزبيين، لأنّهم لا يريدون إلا تكثير سواد حزبهم.
"ሰለፊ ወንድሞቻችንን ከነዚህ ቡድንተኞች እንዲርቁ እመክራቸዋለሁ። ምክንያቱም ጭፍራቸውን ማብዛት እንጂ አይፈልጉምና።" (ቱሕፈቱል ሙጂብ: 117)

ጌታችንም እንዲህ ብሏል:—
وَلَا تَرْكَنُوا إِلَى الَّذِينَ ظَلَمُوا فَتَمَسَّكُمُ النَّارُ وَمَا لَكُمْ مِنْ دُونِ اللَّهِ مِنْ أَوْلِيَاءَ ثُمَّ لَا تُنْصَرُونَ_ [هود: 113]
"ወደነዚያም ወደበደሉት አትጠጉ። እሳት ትነካችሁዋለችና። ከአላህም ሌላ ጠባቂዎች የሏችሁም። ከዚያም አትረድዱም።" (ሁድ: 113)

የዚች አንቀፅ መልእክት ከሃዲዎች ላይ የተገደበ እንዳልሆነ ይልቁንም ሙብተዲዖችንና ሌሎች ወንጀለኞችንም እንደሚያካትት ቁርጡቢ ይገልፃሉ። አስገዳጅ ሁኔታዎች ካልገጠሙ በስተቀር ይሄ ከአጥፊዎች መራቅ ቋሚ ህግ ነው። ባይሆን አስገዳጅ ሁኔታ ማለት ተጨባጭ ምክንያት እንጂ ያልተረጋገጠ ሰበብ፣ የተለጠጠ ምኞት፣ ስብስባዊ ፍላጎት አይደለም።
0 Comments