Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ጥያቄ ፦ የጥፍር ቀለም የተቀባች ሴት ወዱእ እንዴት ይታያል? 【ሸይኽ መሐመድ ኢብኑ ሷሊህ አልዑሰይሚን ረሂመሁላህ】

ጥያቄ ፦ የጥፍር ቀለም የተቀባች ሴት ወዱእ እንዴት ይታያል?
መልስ ፦ ሴት የምትሰግድ ከሆነ (ማለትም ከወር አበባዋ ጊዜ ውጭ ከሆነች) የጥፍር ቀለም መቀባት የለባትም። በወዱእ ግዜ ውሃ ወደ ጥፍሯ እንዳይደርስ ያግዳልና። ውዱእ የሚያደርግ ወይም ገላውን የሚታጠብ ሰው ውሃ ወደ አካሉ እንዳይደርስ የሚያግድ ነገር መጠቀም የለበትም። አላህ « ፊቶቻችሁን፣ እጆቻችሁንም እስከ ክርኖች እጠቡ» ይላልና። ሴት በጥፍሯ ላይ ቀለም ካለ ውሃ ወደ ጥፍሯ እንዳይደርስ ስለሚያግድ እጇን እንደታጠበች አይቆጠርም። እናም ከውዱእ ወይም ከትጥበት ፈርዶች አንዱን ፈርድ ተወች ማለት ነው።
እንደ ወር አበባ ባለ ምክንያት ሰላት የማትሰግድ ከሆነ ግን ብትቀባው ችግር የለውም። ይህ ድርጊት የካፊር ሴቶች መለያ ከሆነ ግን ከነሱ ጋር መመሳሰል ስለሆነ አይቻልም።
አንዳንድ ሰዎች ይህ ድርጊት ማለትም የጥፍር ቀለም መቀባት ኹፍ (እስከ ቁርጭምጭሚት የሚሸፍን ጫማ) ከመልበስ ጋር አንድ ነው ሴት ባገሯ ነዋሪ ከሆነች ለአንድ ቀንና ሌሊት (24 ሰዓት) ተቀብታ መቆየት ትችላለች ሙሳፊር ከሆነች ደግሞ ለሦስት ቀን ተቀብታ መቆየት ትችላለች ብለው ፈትዋ መስጠታቸውን ሰምቻለሁ። ነገር ግን ይህ ፈትዋ ስህተት ነው። ሰዎች ገላቸውን የሚሸፍኑበት ነገር ሁሉ ከኹፍ ጋር ሊመሳሰል አይችልም። ኹፍ ላይ ማበስን ሸሪዓው ደንግጎታል። ምክንያቱም ባብዛኛው ለሰው ልጅ አስፈላጊ በመሆኑ ነው። እግር መሬትና አሸዋ ስለሚረግጥ እንዲሁም ብርድና ሌላም ነገር ስለሚያገኝው ከነዚህ ለመከላከል ሲባል ኹፍ (ጫማ) መልበስ አስፈላጊ አስፈላጊ ይሆናል። ስለዚህ ሸሪዓው በሱ ላይ ማበስን ፈቀደ። በጥምጣም ላይ ከማበስ ጋርም ለማመሳሰል ይሞክራሉ። ይህም ትክክል አይደለም። የጥምጣም ቦታ ራስ ነው። የራስ ፈርድ ደግሞ መጀመሪያውኑም ቀለል ያለ ነው። ስለዚህ ነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ለሴቶችም የእጅ ጎንት ላይ ማበስን አልፈቀዱም። እጅን እንደሚሸፍን የሚታወቅ ቢሆንም። እናም ይህ ውሃ ወደ አካል እንዳይደርስ የሚከለክለውን ማንኛውንም ነገር በጥምጣምና በኹፍ ላይ ቂያስ ማድረግ እንደማይቻል ያሳያል። አንድ ሙስሊም ሐቅን ለማወቅ የሚችለውን ያክል ጥረት ማድረግ ይጠበቅበታል። ለአንድ ነገር ፈትዋ (ብያኔ) ሲሰጥም አላህ እንደሚጠይቀው መገንዘብ አለበት። የሚናገረው ሸሪዓውን ወክሎ ነውና።
አላህ (ሱባሃነሁ ወተዓላ) ቀጥተኛውን መንገድ ይምራን።
【ሸይኽ መሐመድ ኢብኑ ሷሊህ አልዑሰይሚን ረሂመሁላህ】