Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የጁምዓ ትምህርት በጁምዓ ክልክል የሆኑግባራት

የጁምዓ ትምህርት
www.facebook.com/easyfiqh
በጁምዓ ክልክል የሆኑግባራት
1 ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ መናገር አይፈቀድም።
ነብዩ (ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል ፡-
«በጁምዓ ቀን ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ የተናገረ መፅሐፉን እንደተሸከመ አህያ ነው» (አህመድ 1/230 ዘግበውታል)
በሌላም ሐዲስ እንዲህ ብለዋል ፡-
«ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ ለጓደኛህ ዝም በል ካልክ ከንቱ ንግግር ተናገርክ» (ቡኻሪ 394 ሙስሊም 851 ዘግበውታል)
2 በተቀመጡ ሰዎች ትከሻ በኩል መሸጋገር አይፈቀድም።
ነብዩ (ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) የሰዎችን ትከሻ እየተሸጋገረ ሲያልፍ ለተመለከቱት ሰው
«ተቀመጥ ሰውን አስቸገርክ» ብለውታል።
በዚህም ሰውን ማስቸገርና ኹጥባን የሚያዳምጥን ማዘናጋት ይፈጠራል። ኢማሙ ግን የሰዎችን ተከሻ እየተሸጋገረ ካልሆነ ወደ ሚንበሩ የሚደርስበት ሌላ አማራጭ ከሌለው ይህን ሊፈፅም ይችላል።
3 ሁለት ሰዎችን በመለያየት በመካከላቸው መቀመጥም አይፈቀድም
ነብዩ (ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡-
«የጁምዓ ሰላት ገላውን ታጥቦ በጊዜ ወደ ጁምዓ የሄደ ከዚያ በኃላ በሰዎች መካከል ሳይለያይ አላህ የወሰነለትን የሰገደ በዕለቱና በሚቀጥለው ጁምዓ መካከል የሚፈፅመው ኃጢዓቶች ይሰረዝለታል» (ቡኻሪ 910 ዘግበውታል)
የዕለቱ ጥያቄ
በጁምዓ ክልክል ከሆኑግባራት ቢያንስ አንዱን ይጥቀሱ
የፊቅህ ዕውቀትዎን ያዳብሩ ዘንድ ይህንን ፔጅ like ያድርጉ
www.facebook.com/easyfiqh
ሼር ማድረግ እንዳይረሱ።
https://telegram.me/sultan_54