Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ከጁምዓ ማህደር

ከጁምዓ ማህደር
، 👌🏼 فضلُ يوم الجمعةِ
ـ """"""""""""""""""""""
1⃣ قال رسول الله ﷺ :
(أفضلُ الأَيَّامِ عندَ اللهِ يومُ الجمعةِ)
አቡ ሁረይራ [ረዲየላሁ አንሁ] እንዳስተላለፉልን
የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም] «አላህ ዘንድ በላጩ ቀን የጁምዓ እለት ነው።» ብለዋል።
📚صححه الألباني في
السلسلة الصحيحة - رقم: (1502)
صحيح الجامع - رقم: (1098)
2⃣ قال رسول الله ﷺ :
(( أفضلُ الصلواتِ عند اللهِ صلاةُ الصبحِ يومَ الجمعةِ في جماعةٍ ))
አብደላህ ኢብኑ ዑመር [ረዲየላሁ አንሁማ] ባስተላለፉልን መሰረት
የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም] «አላህ ዘንድ ከሰላቶች መካከል በላጭ የሆነው ሰላት የጁምዓ እለት በጀማዓ የተሰገደ የሱብሂ ሰላት ነው።» ብለዋል።
📚السلسلة الصحيحة -
الألباني صحيح - رقم: 1566
3⃣ قال رسول الله ﷺ :
(( أكثِروا الصَّلاةَ عليَّ يومَ الجمُعةِ و ليلةَ الجمُعةِ ، فمَن صلَّى عليَّ صلاةً صلَّى اللهُ عليهِ عَشرًا ))
አነስ ኢብኑ ማሊክ [ረዲየላሁ አንሁ] ባስተላለፉልን መሰረት
የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም] «ጁምዓ ቀንና ጁምዓ ምሽት በኔ ላይ ሰለዋትን አብዙ። በኔ ላይ አንዴ ሰለዋትን ያወረደ አላህ በሱ ላይ አስር ሰለዋትን ያወርድለታል።» ብለዋል።
📚صحيح الجامع
الألباني حسن - رقم: 1209
4⃣ قال رسول الله ﷺ :
(( ما مِن مسلمٍ يموتُ يومَ الجمعةِ أو ليلةَ الجمعةِ إلَّا وقاهُ اللَّهُ فِتنةَ القبرِ ))
አብደላህ ኢብኑ ዑመር [ረዲየላሁ አንሁማ] እንዳስተላለፉልን
የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም] «ከሙስሊሞች መካከል ማንኛውም ሰው በጁምዓ ቀን ወይም በጁምዓ ምሽት ከሞተ … አላህ ከቀብር ፊትና ሳይጠብቀው አይቀርም።» ብለዋል።
📚حسنه الألباني في صحيح الترمذي - رقم: (1074) ، تخريج مشكاة المصابيح - رقم: (1316) الألباني :إسناده حسن أو صحيح لغيره
5⃣ قال رسول الله ﷺ :
(( الصَّلاةُ الخمسُ والجمعةُ إلى الجمعةِ كفَّارةٌ لما بينَهنَّ ما لم تُغشَ الْكبائرُ ))
አቡ ሁረይራ [ረዲየላሁ አንሁ] እንዳስተላለፉልን
የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም] «አምስቱ የግዴታ ሰላቶችና ከጁምዓ እስከ ጁምዓ … ከባባድ ወንጀሎች ኖረው ካልጋረዱ በስተቀር በመካከላቸው የተፈፀሙትን ሌሎች ኃጢኣቶች ያብሳሉ።» ብለዋል።
📚صحيح مسلم - رقم: (233)
6⃣ وفي رواية اخرى :
(( الجمُعةُ إلى الجمُعةِ كفَّارةُ ما بينهما ما لم تُغْشَ الكبائرُ ))
አባሁረይራ [ረዲየላሁ አንሁ] እንዳስተላለፉልን
የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም] «ከጁምዓ እስከ ጁምዓ … ከባባድ ወንጀሎች ኖረው ካልጋረዱ በስተቀር በመካከላቸው ያሉትን ሌሎች ኃጢኣቶች ያብሳሉ።» ብለዋል።
📚الألباني - صحيح الجامع رقم: (3110)
7⃣ قال رسول الله ﷺ :
(( لا يُقيمَنَّ أحدُكم أخاه يومَ الجُمُعةِ . ثم لِيخالفَ إلى مقعدِه فيقعدُ فيه . ولكن يقولُ : أَفسِحُوا ))
አብደላህ ኢብኑ ዑመር [ረዲየላሁ አንሁማ] ባስተላለፉልን መሰረትም
የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም] «አንዳችሁም የጁምዓ እለት (መስጂድ ውስጥ) ወንድሙን ከተቀመጠበት አያስነሳው፤ ከዚያም ወንድሙ ከተነሳበት ቦታ እሱ ሊቀመጥ አይገባውምነ። ነገር ግን (ክፍተት ካለ) ሰፋሰፋ አድርጉ (ተጠጋግታችሁ ክፍት መቀመጫ ስጡን) ይበል።» ብለዋል።
📚صحيح مسلم - رقم: (2178)
8⃣ قال رسول الله ﷺ :
(( إذا راح أحدُكم إلى الجمعةِ فليغتسلْ ))
አብደላህ ኢብኑ ዑመር [ረዲየላሁ አንሁማ] እንዳስተላለፉልን
የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም] «አንዳችሁ ወደ ጁምዓ ሲሄድ ይታጠብ።» ብለዋል።
📚صحيح البخاري - رقم: (882)
9⃣ قال رسول الله ﷺ :
(( مَن قرأَ سورةَ الكَهفِ في يومِ الجمعةِ ؛ أضاءَ لهُ منَ النُّورِ ما بينَ الجُمعتَينِ ))
አቢ ሠዒድ አልኹድሪይ [ረዲየላሁ አንሁ] ባስተላለፉልን መሰረት
የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም] «የጁምዓ ቀን ሱረቱል ካህፍን ላነበበ ሰው በሁለቱ ጁምዓዎች መካከል (ያለውን ርቀት ያህል) ከብርሃን ያበራለታል።» ብለዋል።
📚حسنه الألباني في
تخريج مشكاة المصابيح - رقم:(2116)
🔟 وفي رواية اخرى :
(( من قرأ سورةَ الكهفِ ليلةَ الجمعةِ ، أضاء له من النورِ ما بينه وبين البيتِ العتيقِ ))
አቢ ሠዒድ አልኹድሪይ [ረዲየላሁ አንሁ] ባስተላለፉልን መሰረት
የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም] «የጁምዓ ቀን ሱረቱል ካህፍን ላነበበ ሰው በሱ እና በበይተል ዐቲቅ መካከል ያለውን ርቀት ያህል ከብርሃን ያበራለታል።» ብለዋል።
📚صححه الألباني في
صحيح الترغيب -رقم: (736)
የኢስላም ምሁራን እንዳሉት… ብርሃን ማለት በዱንያ ላይ ሳለ ከወንጀሎች የሚጠበቅበት፣ መልካም ስራዎች ላይ የሚተጋበት እውቀት፣ ኢማን ይጨምርለታል። ወይም ነገ የቂያም ቀን ከእግሩ ስር ብርሃን ይሆንለታል በማለት አስተያየት ሰጥተዋል።
'''''''''''''''‘"""""""""""""""
ረቢዕ አልአወል 14/1437
ከተንቢሃት የዋትሳፕ ግሩፕ