Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ችግሮችን ማስተናገጃ መርሆዎች

🌴ችግሮችን ማስተናገጃ መርሆዎች🌴

1ኛ· ይህ ችግር ያጋጠመው አንተን ብቻ አይደለም።

2ኛ· ለጥበብ ቢሆን እንጂ አላህ ማንኛውንም ነገር አይወስንም

3ኛ· ጥቅም የሚያመጣውና ከጉዳት የሚከላከለው አላህ ብቻ ነውና በሱ ላይ እንጂ ልብህ አይንጠልጠል።

4ኛ· ያጋጠመህ ነገር ምንም ቢሆን አይስትህም… የሳተህ ነገር ምንም ቢሆን አይነካህም።

5ኛ· የቅርቢቱን ህይወት(ዱንያ) እውነታን እወቅና እረፍት ታገኛለህ።

6ኛ· በጌታህ ጥሩ ግምት እና አስተሳሰብ ይኑርህ።

7ኛ· የአላህ ምርጫ ከራስህ ምርጫ የተሻለ ነው።

8ኛ· ችግሩ በበረታ ቁጥር ከችግር መላቀቁ ቅርብ ነው።

9ኛ· ከችግሩ እንዴት እላቀቃለሁ ብለህ አትጨነቅ ምክንያቱም አላህ የሆነን ነገር ሲፈልግ መዳረሻውን ባልታሰበ መልኩ ያመቻቸዋልና።

10ኛ· የችግሮች መላቀቂያ ቁልፎች በእጁ የሆነውን ተማጸን።

ኢብኑል ቀይም (አላህ ይዘንለትና) እንዲህ ይላል፦
«لاتحسب أن نفسك هي التي ساقتك إلى فعل الخيرات ، بل إعلم أنك عبد أحبك الله فألهمك فعل الخيرات ، فلا تفرط في هذه المحبة فينساك»

"ነፍሴ መልካም እንድሰራ መራችኝ ብለህ አታስብ ይልቁንስ አላህ ወዶህና መልካም እንድትሰራ መርቶህ እንጂ… በመሆኑም ይህችን ውዴታ አታባክናት ይረሳሃልና።"

قواعد التعامل مع الشدائد
القاعدة الأولى: (لستَ وحدك)
القاعدة الثانية: (لا يقدر الله شيئا إلا لحكمة)
القاعدة الثالثة: (جالب النفع ودافع الضر هو الله، فلا تتعلق إلا به)
القاعدة الرابعة: (ما أصابك لم يكن ليخطئك ، وما أخطأك لم يكن ليصيبك)
القاعدة الخامسة: (اعرف حقيقة الدنيا تسترح)
القاعدة السادسة: (أحسن الظن بربك)
القاعدة السابعة: (اختيار الله لك خير من اختيارك لنفسك)
القاعدة الثامنة: (كلما اشتدت المحنة قرُب الفرج)
القاعدة التاسعة: (لا تفكر فى كيفية الفرج فإن الله إذا أراد شيئا هيأ له أسبابه بشكل لا يخطر على بال)
القاعدة العاشرة: (عليك بدعاء من بيده مفاتيح الفَرَج)

© ተንቢሀት

Post a Comment

0 Comments