Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የጀናዛ ሰላት አሰጋገድ

የጀናዛ ሰላት አሰጋገድ

አራት ጊዜ ተክቢራ ይደረጋል፤

☞ ከመጀመሪያ ተክቢራ በመቀጠል አል ፋቲሀ (የመክፈቻው ምዕራፍ) ይነበባል። ከዚህም በተጨማሪ አጠር ያለ የቁርአን ምዕራፍ ወይም አንድ ወይም ሁለት አንቀፅ ቢያነብ ጥሩ ነው። ይህንን በማስመልከት ከአብደላህ ኢብን አባስ የተዘገበ ትክክለኛ ሀዲስ ስላለ ነው።

☞ ከዚያም ለሁለተኛ ጊዜ ተክቢራ ይደረጋል፤
ከተሸሁድ ቀጥሎ እንዳለው በነብዩ ላይ ሰለዋት ያወርዳል። ከዚያም በሶስተኛው ተክቢራ ከተደረገ በኃላ እንዲህ ይላል

(اللهم اغفر لِحينا وميتِنا، وشاهدنا وغائبنا، وصغيرنا وكبيرنا، وذَكَرِنا وأنثانَا، اللهم من أحيَيتَهُ منا فأحيه على الإسلام، ومن توفيته منا فَتَوَفهُ على الإيمان، اللهَم اغفر له، وارحمه، وعافه، واعف عنه، وأكرِم نُزُلَه، وَوَسع مُدخَلَه، واغسله بالماء والثلج وِالبرد، ونقه من الخطايا كما ينقى الثوب الأبيض من الدَنس، وأبدلهُ دارا خيرا من داره، وأهلا خيرا من أهله، وأدخله الجنة، وأعذه من عذاب القبر، وعذاب النار، وافسح له في قبره، ونور له فيه، اللهم لا تَحرمنَا أجره ولا تُضِلنا بعده)

(አላሁመ ኢግፊር ሊሐይና ወመይቲና ወሻሂድና ወጋኢቢና ወሰጊሪና ወከቢሪና ወዘከሪና ወኡንሳና አላሁመ መን አህየይተሁ ሚና ፈአህይሂ አለል ኢስላም ወመን ተወፈይተሁ ሚና ፈተወፈሁ አለል ኢማን አላሁመ ኢግፊር ለሁ ወግሲልሁ ቢልማኢ ወሰልጂ ወልበረዲ ወነቂሂ ሚነል ዙኑቢ ወል ኸጣያ ከማ ዩነቀሰውቡል አብየዲ ሚነደነሲ ወአብዲልሁ ዳረን ኸይረን ሚን ዳሪህ ወአህለን ኸይረን ሚን አህሊህ ወአድኺሉሁል ጀነተ ወአዒዙሁ ሚን ዓዛቢል ቀብሪ ወዓዛቢ ናር ወፍሰህ ለሁ ፊ ቀብሪሂ ወናዊርለሁ ፊህ አላሁመ ላተህሪምና አጅረሁ ወላቱዲለና ባዕደሁ።)

ትርጉሙም: “አላህ ሆይ በህይወት ያሉትንም፣ የሞቱትንም፣ በቅርብ ያለውንም ሩቅ ያለውንም፣ ትልልቆችንም፣ ትንንሾችንም፣ ወንዶችንም ፣ ሴቶችንም ማርልን። አላህ ሆይ ከመካከላችን የምትገለውን በእምነት ላይ እንዲሞት አድርገው። አላህ ሆይ ምህረት አድርግለት፣ እዘንለትም፣ ከእሳት ጠብቀው፣ ይቅርም በለው፣ መስተንግዶውን አሳምርለት፣ መግቢያውንም አስፋለት፣ አጢአቱንም በውሃ፣ በበረዶና በቀዝቃዛ ውሃ እጠብለት፣ ነጭ ልበስ ከቆሻሻ እንደሚፀዳው የእርሱንም ወንጀል አፅዳለት፣ ከቤቱ የተሻለ ቤት ከሚስቱ የተሻለ ሚስት ቀይርለት። ወደ ገነት አስገባው፣ ከቀብር ውስጥ ቅጣትና ከእሳትም ቅጣት ጠብቀው ቀብሩንም አስፋለት፣ አብራለት። አላህ ሆይ ምንዳውን አትንፈገን ከእርሱም በኃላ እጣችንን ጥመት አታድርግብን።”
ማለት ነው።

☞ ከአራተኛው ተክቢራ በኃላ በቀኝ ጐኑ ብቻ “አሰላሙአለይኩም” በማለት ያጠናቅቃል።

ተክቢራ በሚደረግበት ጊዜ እጅን ማንሳት ይወደዳል።
√ ሴት ከሆነች ዱዓው ላይ እንዲህ ይባላል፤
(اللهم اغفر لها . . ) (አላሁመ እግፊርለሃ)
√ ሁለት ከሆኑ ደግሞ (اللهم اغفر لهما . . . ) (አላሁመ እግፊር ለሁማ)
√ ከሁለት በላይ ከሆኑ ደግሞ (اللهم اغفر لهم . . ) (አላሁመ እግፊር ለሁም) ይባላል።
√ ሟቹ ህፃን ከሆነ ለእርሱ ምህረትን በዱዓው ውስጥ ከመለመን ይልቅ እንዲህ ይባላል።

(اللهم اجعله فرطا وذُخْرَا لوالديه، وشفيعاَ مُجَابا، اللهم ثقل به موازينهما، وأعظم به أجورهما، وألحقه بصالح سلف المؤمنين، واجعله في كفالة إبراهيم عليه الصلاة والسلام، وَقِهِ برحمتك عذاب الجحيم)

(አላሁመ ኢጅዓሉሁ ፈረጠን ወዙኽረን ሊዋሊደይሂ ፤ ወሸፊዓን ሙጃበን አሏሁመ ሰቂል ቢሂ መዋዚነሁማ፤ ወአዕዚም ቢሂ ኡጁረሁማ፤ ወአልሂቁሁ ቢሷሊሂ ሰለፊልሙእሚኒን፤ ወጅዓልሁ ፊ ከፋለቲ ኢብራሂመ አለይሂ ወሰላቱ ወሰላም ወቂሂ ቢራህመቲከ አዛበል ጀሂም)

√ ትርጉሙም “አላህ ሆይ በወላጆቹ (በወዲያኛው ህይወት) ቀደሞ ሄዶ የሚያመቻች፣ ለችግር ቀን አለኝታ፣ ተሰሚነት ያለው አማላጅ አድርግላቸው፣ አላህ ሆይ የመልካም ስራቸው ሚዛን ማክበጃና የምንዳቸው ማብዣ አድርገው፣ ከደጋግ ምእመናን ጋርም አስጠጋው ከነብዩ ኢብራሂም u እንክብካቤ ስር አድርገው፣ በችሮታህም ከጀሐነም እሳት ጠብቀው።”

☞ ኢማሙ በሟች ላይ ለመስገድ ሲቆም ወንድ ከሆነ በጭንቅላቱ አቅጣጫ ሴት ከሆነች በሰውነቷ መሀል አቅጣጫ ላይ መቆሙ ሱና ይሆናል።

☞ አስክሬኑ ወንድና ሴት ከሆኑ ወንዱ ወደ ኢማሙ በኩል ሴቷ ወደ ቂብላ በኩል ይደረጋሉ ።

www.fb.com/easyfiqh

Post a Comment

0 Comments