Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የዓሹራእ ቀን ከተላለፈው የእናቶችን ዓኢሻ ታሪክ የምናገኛቸው ትምህርቶች

بسم الله الرحمن الرحيم
<የዓሹራእ ቀን ከተላለፈው የእናቶችን ዓኢሻ ታሪክ የምናገኛቸው ትምህርቶች>
(ማሳሰቢያ፦ ይህ ፅሁፍ ታሪኩን ካነበቡና ካደመጡ ተማሪዎች የተላከ ነው)
➊ አላህ (ሱብሀነሁ ወተዓላ) ከሰባቱ ሰማያት በላይ የናታችን ዓኢሻን ንፁህነት የሚገልፅ መልዕክት በሱረቱ -ኑር 11-20 አንቀፅ ማውረዱን
➋ የሙናፊቆች አለቃ(ኢብኑ ኡበይ ቢን ሰሉልን በመከተል ሺዓዎች እናታችን አኢሻን በዝሙት መወንጀላቸው እና የነብዩን (ሰለላሁዓለይሂ ወሰለም) ቤተሰቦችን እንወዳለን ብለው መዋሸታቸውንና
የአህለሱና ኡለማዎች እናታችን አኢሻን አላህ ካጠራት በሀላ በዝሙት የጠረጠራትን ሰዉ ካፊር (ከእስልምና እንደሚወጣ) መስማማታቸዉ፤ ምክንያቱም አላህ የለም ያለውን ነገር አለ በማለት ቁርኣንን ማስተባበል ስለሚሆን
➌ኢማምማሊኪ(ረሂመሁላህ) ከሰሀቦች መካከል አንዱን የተሳደበ ሰው መገረፈ አለበት ሲሉ እናታችን አኢሻን በዝሙት የወነጀለ ሰው ግን መገደል አለበት ብለው መናገራቸውን
➍ንፁህ ሰውን በዝሙት የወነጀለ 80 ጅራፍ እንደሚገረፍ
➎ቁርኣንን ያስተባበሉና የነብዩን ክብር የሚነካ ከባድ ወንጀልን የፈፀሙት ሽዓዎች አላህ በጥበቡ በየአመቱ አሹራ/ሙሀረም ራሳቸዉን በራሳቸዉ እጅ እንዲገርፉና የአለም መሳለቂያ እንደሆኑ
➏ሁሴን የተገደለው በራሳቸው በሽዓዎች ምክንያት ሆኖ ሳለ በኡማው መካከል ፊትናን ለመፍጠር ፣በአሹራ ቀን ሁሴንን ጠላቶቹ የገደሉበት ቀን ሰለሆነ በሀዘን ደማችንን እናፈሳለን በማለት ድንበር ማለፋቸውንና በተቃራኒው አህለሱናዎች በሁሴን(ረድየላሁ ዓንሁ) መገደል ሀዘን ቢሰማቸውም ሸሪዓን የሚፃረር ድርጊት አለመፈፀማቸውን
➐ምስክርነት ስንጠየቅ ሀቅን ብቻ መናገር እንዳለብን
➑ችግር ሲገጥመን አላህን ብቻ መማፀን እዳለብን
➒ገይብን (የማይታይና ያልተከሰተን ነገር) እናውቃለን የሚሉ ሰዎች ልያፍሩ እንደሚገባቸው ምክንያቱም (ነብያችን) ሰለላሁ አለይህ ውሰለም ዋሕይ ከአላህ.እስኪመጣ ድረስ እውነታውን ማወቅ አልቻሉም
➓ የሙስሊሞችን ስም የሚያጠፋ በዱንያም ሆነ በአኸራ አሏህ ጅዛውን እንደሚከፍላቸው
➊➊ እውነት ምንም ቢደበቅ ምንም ግዜው ቢረዝም አንድ ቀን መውጣቱ የማይቀር መሆኑን
➊➋ ድል ምንግዜም ለሙእሚኖችና ለታጋሾች መሆኑን
➊➌ ምላሳችንን መቆጣጠር ስለ አንድ ጉዳይ ከመናገራችን ከማስወራታችን በፊት ስለ እውነተኝነቱ ማረጋገጥ ወይም ሁሉን ለአላህ ትቶ ዝም ብለን ማለፍ እንዳለብን
➊➍ በዝሙት ሰዎችን መጠረጠር ምን ያህል የከፍ መሆኑና ሰዎች በአይናቸው ማየት እስካልቻሉ ድርስ በዚህ ነገር ላይ መጠርጠር ትልቅ አደጋ እንደሆነ
➊➎ በእስልምና እጣ ማውጣት እንደሚቀድ
አንድ ሰው ጉዞ ሲጓዝ ከሚስቱ ጋር መጓዝ እነደሚችል (ጥሩ እንደሆነ)
በሚስቶቹም መካከል ፍትሃዊ መሆን እንዳለበት ➊➏ የሴት ልጅ ሙሉ የሆነ ሂጃብ [ፊትንም ጭምር መሸፈን ] ግዴታ መሆኑ
➊➐ አንድ ጉዳይ በተምታታብን ጊዜ ለሙእሚን እህቶቻችን (ወንድሞቻችን) ማማከር እንደምንችልና አስፈላጊ መሆኑን
➊➑ አንድ ሠው ሥለ ቤተሠቤ መጥፎ አወራ ብለን ለዛ ሠው እናደርግለት የነበረን እርዳታ ማቋረጥ እንደሌለብን
➊➒ አንድ ችግር በሚያጋጥመን ጊዜ የደረሠብንን ሙሢባ አላህ እሥኪያነሣልን እና ኸይሩን እሥኪያመጣልን በአላህ መታገዝ እና መወከል እንዳለብን
20 ከአንድ ሠው አንድን መጥፎ ነገር ስንሠማ በቅርብ የሚያውቁትን እና አብረውት የሚኖሩ ሠዎችን መጠየቅ እንዳለብን
➋➊ እናቶች ልጆቻቸውን እንዴት ማረጋጋት እንዳለባቸውም ያስተምራል
➋➋ አንዲት ሴት አጠገብ ወይም በአካባቢዋ ከመህረሟ ውጭ (አጅነቢ) ወንዶች ካሉ «ፊቷን» መገላለጥ እንደማትችልና መሸፈን እንዳለባት።
➋➌ ማንኛዋም ሴት ብትሆን ተቸግራ ስናያት እኛ በዛ ቦታ ላይ አስፈላጊ ሆነን ከተገኘንና እሷን የማገዝ አቅሙ ካለን የሚረዳት ሰው ባለመኖሩ ለሷ አጅነቢ ብንሆንም የአላህን ትእዛዝ ሳንጥስ በምንችለው ነገር ሴትን ልጅ ልንረዳት እንደምንችል።
በምንረዳት ወቅትም ጉዞ ስንጓዝ ሴት ልጅ አጅነብይ ከሆነባት ከወንድ ልጅ በስተኋላ ወንዱ ደግሞ ከፊት ለፊት መሄድ እንዳለበት እንረዳለን።
➋➍ ማንኛውም የምንወደው ሰው ቢሞትብን ለዛ ሰው ልባችን ሊያዝን እንዲሁም ከእዝነት የመነጨ እንባም ሊፈሰን ይችላል ነገር ግን ከዚህ ተግባር አልፎ አላህን የሚያስቆጣ ተግባር ማድረግ እንደሌለብንና ለሟች አላህ እንዲምረው፣ ቀብሩን እንዲያሰፋለት፣ ከጀነት ሰዎች እንዲያገርገው ዱዓ ከማድረግ ውጭ አላህን የሚያስቆጡ ነገሮችን መስራት እንደሌለብን።
➋➎ እናታችን ዓኢሻ ረዲአሏሁ ዓንሃ የበፊትም ሙናፊቆች ይሁኑ አሁን ያሉት ሺዓዎች ከሚቀጥፉባት ዉንጀላ የፀዳች መሆኗን
➋➏ የሙናፊቆች ተንኮልና ሴራ በጣም ከባድ መሆኑን
➋➐ እናታችን ኣዒሻ ረዲየሏሁ ዐንሃ አሏህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ዘንድ ያላት ደረጃ
➋➑ የሺዓዎች ጥመት ምን ያህል ከሱና ያፈነገጠ መሆኑን
➋➒ የበድር ዘመቻ የተሳተፉ ሰሃቦች በሙሉ ልዩ ክብር እንዳላቸውና እነሱን በመጥፎ አለማንሳት
30 አንዲት ሴት ከቤቷ ስትወጣ የምትጓዘው ወደ ቤተሰቦቿ ቤት ቢሆን እንኳን ባሏን ማስፈቀድ እንዳለባት
➌➊ ነቢዩ ሙሀመድ ሰላሏሁ ዐለይሂ ወሰላም ከበድ ያለ ጉዳይ ሲገጥማቸው ሰሀባወችን ጠርተው ያማከሯቸው እንደነበረ
➌➋ የእናታችን ኣዒሽን ረዲየሏሁ አንሃ ንጹህነት አላህ ሱብሃነሁ ወተኣላ በቅዱስ ቁርኣኑ እንዳረጋገጠላትና ከዚህ በኋላም እሷን በዝሙት የሚወነጅል አካል እንደሚከፍር
➌➌
ሺዓዎች ቁርዓንን እንደሚያስተባብሉ
➌➍ ስሜትን መከተል አደጋ መሆኑን
➌➎ እናታችን ኣኢሻን ረዲየሏሁ አንሃ በሂወት እያለች የተከሰተው ስም የማጉደፍ ዘመቻ አሁን ካለው የሺዓዎች ስም የማጥፋት ዘመቻ ጋር ተመሳሳይ መሆኑን
➌➏ ነብዩ ሙሀመድ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በባለ ቤቶቻቸው መካከል ፍትሃዊ እንደነበሩና ከሁለት በላይ ሚስት ያለው ማዳላት እንደሌለበት ምክንያቱም ነብዩ ሙሀመድ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ከሚስቶቻቸው መካከል እጣ አውጥተው ከእርሳቸው ጋር የምትሄደዋን ስለመረጡ
➌➐ ለሴቶች የአንገትጌጥ የተፈቀደ መሆኑን
➌➑ ሙናፊቆች የሚያናፍሱት ወሬ ሙስሊሞችን እንደ ሚያውክ
والحمد لله رب العالمين والصلاة والسلام على نبينا محمد
والله اعلم "
✍ ከተማሪዎች ምላሽ የተመረጡ ምላሾች እነዚህ ናቸው
✔መልሶችን አሰባስበው ላጣሩ የ"ተኣውን ጉሩፕ" እህቶችና ለሌሎችም መልካም ምንዳቸውን አሏህ ይክፈላቸው
والسلام عليكم ورحمة الله

Post a Comment

0 Comments