Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ከሠለፎች ማኅደር ወየውልህ ተጠንቀቀው

📋ከሠለፎች ማኅደር

ወየውልህ ተጠንቀቀው

በሸይኹል ኢስላም ሱፍያን አስሰውሪ ረሂመሁላህ
ከሂጅሪያ 97 - 161 የነበሩ ታላቅ ሙሀዲስ
🎐
ተግባርህን… የሚያጠፋን
ወየውልህ ተጠንቀቀው እዩልኝን
ለዚያ ብለህ… መተግበርን።

ይታይልኝ ባይኖርብህ
በስሜትህ ባያድርብህ
በሌላ ጎን ስለራስህ መደነቅህ
የምትበልጥ ከወንድምህ
መሆንህን ማሰብህ
ይህን ያህል እስኪሰማህ
በአእምሮህ ተስሎብህ
ስለራስህ መደነቅህ
ያጠፋሃል በዚህ ይብቃህ
የማትሰራም ትሆናለህ
የሱን ያህል አሳምረህ።

ይሆናልም ካንተ ሚልቅ
ጌታህ አላህ
ህርም ያለውን
በመጠንቀቅ።

በጥረቱም ፅዱ ይሆናል
መልካም ስራው
ካንተው ይልቅ።

ብትሆን እንኳ
ስለ ራስህ ማትደነቅ
የሰዎችን ውዳሴዎች
ከመከጀልም ተጠንቀቅ።

በስራህም
አንዲያልቁህ
በአክብሮት
እንዲያዩልህ
በልባቸው ቦታ ቢጤ
እንዲሰጡህ
ለሌላውም ጉዳዮችህ
ከወደነሱ ልታገኝ ማሰብህ
ይኸ ነው… ውዳሴያቸው
ተጠንቀቀው

(በአንፃሩ)
ልታስበው… የሚገባህ
ተግባርና ፍላጎትህ
ይሁን… ለሀገረ ኣኺራህ
ከሱምሌላ… እንዳትሻ ይቅርብህ

ሞትን… ማውሳቱ
በብዛትም ማንሳቱ
ዱንያንም ቸል-ማለቱ
ለኣኺራ መጓጓቱ
ይበቃሃል በዚሁ ላይ መገኘቱ።

የምኞት መራዘም
የፍራቻም መዳከም
መዳፈሩ ወንጀልንም
ይብቃህ ተወው ይኸንንም።

ቁጭትና መፀፀትም
በትንሳዔው ኣለለትም
እያወቀው
ለማይሰራው።
═════ ❁✿❁ ════
【ሂልየቱል አውሊያእ: 6/391】

قال سفيان الثوري -رحمه الله-:
” إياك وما يفسد عليك عملك فإنما يفسد عليك عملك الرياء، فإن لم يكن رياء فإعجابك بنفسك حتى يخيل إليك أنك أفضل من أخ لك، وعسى أن لا تصيب من العمل مثل الذي يصيب ولعله أن يكون هو أورع منك عما حرم الله وأزكى منك عملا، فإن لم تكن معجبا بنفسك فإياك أن تحب محمدة الناس، ومحمدتهم أن تحب أن يكرموك بعملك ويروا لك به شرفا ومنزلة في صدورهم أو حاجة تطلبها إليهم في أمور كثيرة، فإنما تريد بعملك زعمت وجه الدار الآخرة لا تريد به غيره، فكفى بكثرة ذكر الموت مزهدا في الدنيا ومرغبا في الآخرة، وكفى بطول الأمل قلة خوف وجرأة على المعاصي، وكفى بالحسرة والندامة يوم القيامة لمن كان يعلم ولا يعمل.“
📓حلية الأولياء (6/391).

═════ ❁✿❁ ═════
©ከተንቢሃት የዋትሳፕ ግሩፕ
www.fb.com/tenbihat
መሰረታዊው የሸይኹ ፅሁፍ ከላይ ያለው ዓረብኛው ሲሆን ወደ አማርኛ ሲመለስ ወደ ግጥም ተቀይሮ ነው።
25 ሙሀር'ረም 1437
08 ኖቨምበር 2015

Post a Comment

0 Comments