Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የስፖርት ወይም የስፖርተኞች ውዴታ በገደብ ይሁን የስፖርትና የስፖርተኞች ልብሶችን በተመለከተም "ለጅነቱ ዳኢማ" ያሰፈረውን ፈትዋ ልጋብዛችሁ።



የስፖርት ወይም የስፖርተኞች
ውዴታ በገደብ ይሁን

በሀይማኖታችን በኢስላም ሁሉም ነገር ገደብና ስርዓት አለው። የተፈጠርነው ፈጣሪ ጌታችን አላህን ለማምለክ ብቻ እንደመሆኑ የአኗኗር ስልታችንንም የሚቀርፅልን እሱው ነው። ለዚህም መልእክተኛን ልኮብናል። መመርያውንም አውርዶልናል። ስለሆነም ከሀይማኖታችን መመርያ ውጭ የምንከተለው እምነትም ሆነ ተግባር የለም።

የስፖርት ድጋፍን፣ ውዴታን፣ የኩፋር ስፖርተኞችን ልብስና መሰል ነገሮችን በተመለከተ ምሁራን ብዙ ፅፈዋል። ከነሱም መካከል አንኳር ነጥብ የሆነው፣

~ አንድ ሙስሊም በምንም አይነት ሰበብ ሙስሊም ያልሆነን ሰው መውደድ፣ የልብ ጓደኛ ማድረግ የተከለከለ መሆኑን።

~ በስፖርቱ ድጋፍና በመሳሰለው ሰበብ ወደ ቅያሜ፣ ወደ ግጭትና የመሳሰሉት ጠላትነት መግባት እንደሌለበት።

~ የስፖርት ቡድኑም ሆነ የስፖርተኛው ልዩ አርማ ወይም ምልክት ከኢስላም አስተምህሮ ጋር የሚጋጭ ከሆነ ያንን መጠቀም የተከለከለ መሆኑን።

~ የተጫዋቹን ምስል ጨምሮ ህይወት ያላቸው ነገሮች ያለበትን ልብስና የመሳሰሉትን ኣለመጠቀምና የመሳሰሉት ከእምነታችንና ከኢስላማዊ ስርዓታችን ጋር ከሚጋጩ ነገሮች መራቅ እንዳለብን ያመለክታሉ።

የስፖርትና የስፖርተኞች ልብሶችን በተመለከተም "ለጅነቱ ዳኢማ" ያሰፈረውን ፈትዋ ልጋብዛችሁ።

💥« ይህ ልብስ መስቀልን የመሳሰለ የኩፋሮች ሀይማኖት ምልክት ያለበት እንደሆነ ለገበያ ማቅረቡም፣ መልበሱም፣ መሸጡም፣ መግዛቱም አይፈቀድም።

💥 በልብሱ ላይ ያለው ምስሉም ሆነ ስሙ ወይም የተጫዋቹ ቁጥርን የመሰለ መገለጫዎቹ ያንን ካፊር ለማድነቅ፣ ከፍ ለማድረግ የተቀመጠ እስከሆነ ድረስ መጠቀሙ ሃራም ነው።

💥ልብሱ ላይ ያለው ምልክት የአምልኮ መገለጫ ካልሆነ፣ እንዲሁም ያንን ስፖርተኛ ለማድነቅ የሚገፋፋ ነገር ከሌለበት ለተፈቀዱ የንግድ ምልክትነት የተቀመጠ ከሆነ ማለትም
"ماركة Trade Mark ወይም"
አይነት ከሆነ ችግር የለውም።»

ምንጭ☞
የፈትዋ ቋሚ ኮሚቴ ቁጥር ( 24 / 24 ، 25)
≅ ፈትዋውን በጋራ የሰጡት የኮሚቴው አባላት☞
ሸይኽ ዐብዱልአዚዝ ቢን ባዝ
ሸይኽ ዐብዱላህ ቢን ጘድያን
ሸይኽ ሷሊህ አልፈውዛን
ሸይኽ ዐብዱልአዚዝ ኣ'ሊ ሸይኽ
ሸይኽ በክር አቡ ዘይድ

🏆 🌍 🏆

1. ” إن كانت هذه الشعارات ترمز إلى ديانات الكفار كالصليب ، ونحوه : ففي هذه الحالة لا يجوز استيراد هذه الملابس ، ولا بيعها ، ولا لبسها .

2. إن كانت هذه الشعارات ترمز إلى تعظيم أحدٍ من الكفار ، بوضع صورته ، أو كتابة اسمه ، ونحو ذلك : فهي أيضاً حرام ، كما سبق .

3. إذا كانت هذه الشعارات لا ترمز إلى عبادة ، ولا تعظيم شخص ، وإنما هي علامات تجارية مباحة ، وهي ما يسمى بـ " الماركات " : فلا بأس بها .

الشيخ عبد العزيز بن باز ، الشيخ عبد الله بن غديان ، الشيخ صالح الفوزان ، الشيخ عبد العزيز آل الشيخ ، الشيخ بكر أبو زيد .

" فتاوى اللجنة الدائمة "
( 24 / 24 ، 25 ) .
---------※----------
ተንቢሃት የዋትሳፕ ግሩፕ
www.fb.com/tenbihat
27 muharram 1437
10 Nov 15

Post a Comment

0 Comments