Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

በእምነት ላይ መፈላሰፍ አላህን ያስክዳል

በእምነት ላይ መፈላሰፍ አላህን ያስክዳል

الرَّحْمَنُ عَلَى الْعَرْشِ اسْتَوَى
“አረህማን ከዐርሽ በላይ ከፍ አለ (ሆነ)” (ጣሃ 5)

አህባሾችና መሰሎቻቸው‘ኢስተዋ’ (ከበላይ ሆነ) የሚለውን ቃል ‘ኢስተውላ’ (ስልጣንን ተቆናጠጠ) በሚል ከቁርአናዊው መርሆ ጋር በማይጣጣም ሌላ ቃል በመተርጎም “አላህ ከዓርሽ በላይ ነው” ብሎ መናገር “ኩፍር ነው” ይላሉ። ይህ አረፍተ ነገር ቁርዓን ላይ ያለና አላህ እራሱን የገለጸበት ቃል መሆኑ ሲነገራቸው፤ ይህ “ሌላ ትርጓሜ ሊሰጠው ይገባል እንጂ የቃሉ ቀጥተኛ ትርጉም “ተሽቢህ በመሆኑ ኩፍር ነው” ብለው ይሞግታሉ። በአላህና እና በመልዕክተኛዉ ንግግር ያመነ ሰው በፍጹም ለኩፍር የሚዳርግ መልዕክት ያስተላልፋሉ ብሎ አያስብም።

ለመሆኑ ይህንን አይነት ግንዛቤ ለምን አዳበሩ?
“አላህ ከዓርሽ በላይ ነው” የሚለውን አረፍተ ነገር የሚረዱት ፈጡራን ከነገሮች በላይ የሚሆኑበትን ሁኔታ እና ይዘት መሰረት ባደረገ መልኩ ስለሆነ፤ “አላህ ከዓርሽ በላይ ነው” ማለት፤ «አላህን ዓርሽ ተሸክሞታል ማለት ነውና አላህን ከዚህ ማንጻት አለብን» ይላሉ። ይህ እንግዲህ ከትክክለኛው የሰለፎች ግንዛቤ ወጣ ያለና አላህን ከፍጡራን ጋር ማመሳሰልን መሰረት ያደረገ ጥመት ለመሆኑ ጥርጥር የለውም። ሰሀቦችና የነሱ ምትክ ሰለፎች ሁሉ ለአላህ የነበራቸው ክብር አንቀፁን በተገቢው መንገድ እንዲረዱት አድርጓቸዋል። አዎን! ምንም አይነት ፍልስፍና ውስጥ ሳይዘፈቁ አላህ ስለራሱ የተናገረውን ብቻ በማመን እንዴት ስለሚል አኳኋንን የሚመለከት ጥያቄም ይሁን ማሰላሰል ርቀዋል። የቢድዓ አራመጆች ግን፤ ፍልስፍናን መሰረት ያደረገው ፅንፍ የተለያዩ መስመሮችን እንዲይዙ አድርጓቸዋል። ከፊሎቹ “አላህ ሁሉም ቦታ አለ” የሚል ባጢል ለመሆኑ አስረጅ የማይፈልግ የጥመት ልስፍና ሲያራምዳሉ፤ እንደ አህባሽ ያሉት ደግሞ “አላህ የሚገኘው ካለ ቦታ ነው፤ ለአላህ ቦታ “መካን” እና አቅጣጫ “ጂሀ” የለዉም” የሚል ሌላ ፍልስፍና ውስጥ ተዘፍቀዋል። አላህን ከ‘ጂሀ’ እና ከ“መካን” ማጥራት ማለት ምን እንደሆነ ሲያብራሩም፤ «አላህ ከፍጥረታት በላይ የለም፤ ከታችም፣ ከቀኝም፣ ከግራም፣ ከኋላም፣ ከፊትም የለም፤ ከፍጥረተ አለሙ ውስጥም አይደለም፤ ከፍጥረተ አለሙ ውጭም አይደለም» በማለት እርስ በእርሱ የተምታታ፣ ሰሀቦችና ታቢዒዮችም ዘንድ ይታወቅ ያልነበረ እና መቋጫውም “አላህ የለም” የሆነን ፍልስፍና ያስተምራሉ።

አላህ የማያውቁትን ከመቀባጠርና ከመወናበድ ይጠብቀን።

አስማእ ወሲፋት
http://www.facebook.com/asmaewesifat

Post a Comment

0 Comments