Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ማንን ላግባ አዳዲስ ሰለምቴዎችን ማግባትን ኢስላም ይከለክላልን ?


` 🌸ማንን ላግባ

አዳዲስ ሰለምቴዎችን ማግባትን ኢስላም ይከለክላልን ?

ምላሹን ከሸይኽ ኡስታዝ ዶክተር ሙሀመድ ቢን ዑመር ቢን ሳሊም ባዝሙል (ሀፊዘሁላህ)

« አዳዲስ ሰለምቴዎችን ማግባት ልክ ሌሎችን ሙስሊም ሴቶች እንደማግባት ነው። ነገር ግን እንዲህ አይነቷን ማግባቱ ለሷ ዳዕዋ ለማድረግና መልካም ሙስሊም እንድትሆን በማስተማር አርአያዋ በመሆን ዲኗ ላይ ትጉ እንድትሆን ይረዳል።

ለዚህም አላማ እነሱን ለማግባት ተጨማሪ እውቀትና ተጨማሪ ትዕግስት ያስፈልጋል።

ለዚህ አይነቱ ትግል ብቁ ኣለመሆኑን በራሱ ላይ ያወቀ ሰው በሰብሩ ማነስ እንዲሁም በእውቀቱ ድክመት ሰበብ እንዳይጎዳት (እንዳያሰቃያት) እሷን ለማግባት መጋበዝ የለበትም።

እሷን ከማስተካከል ፈንታ አበላሽቷት ከዲኗ ለመቀልበስም ሰበብ እንዳይሆን ቢቀርበት ይሻለዋል።

ባጠቃላይ ወንድ ልጅ ለሚስቱ በተለይ ደግሞ አዲስ የሰለመች ከሆነች ታጋሽና መልካም የሚውል መሆን አለበት።

አዲስ የሰለመች በመሆኗም ከማስተካከል ይልቅ በሚያበላሻት መልኩ ሊጠቀምባት አይገባምና።»

ምንጭ☞ http://mohammadbazmool.blogspot.com/2015/07/blog-post_36.html?m=1
_________

ማንነትህን እወቅ
ከማትወጣው… ሮጠህ እንዳትዘፈቅ
ደህና የቀረበቿን … ጭራሽ ከምታርቅ
ምርጫህን መጥነው… አድረህ ከመሳቀቅ።

ፍቅር ተቀይሮ … በደረቅ ጭቅጭቅ
መታገስ ተስኖህ… ትዳር ሲነቃነቅ
እንደዲንህ እንዳትይዝ …ምኑንም አታውቅ
የቋመጥከው ገላ … በየእለቱ ሲርቅ
ምትጨብጠውን አጥተህ … ጥለህ ከምትወድቅ
ምርጫህን መጥነው …ወልቀህ እንዳታወልቅ።

ተመሳስለህ ከኖርክ … ከአላህ ልትርቅ
በሃይል ላትመራት … ፍፁም አያዛልቅ
እንዲሁ ሳትስማሙ …ሳትገጣጠሙ
ሥጋ ስታጣጥሙ
ለሱ እንደተፈጠረ …ለሱ ስትጠሙ
ሌላም ጨምራችሁ …እናንተ ሳትቆሙ
ዜጋ አታበላሹ… ትውልድን አታድሙ።

ህይወታችሁ ቢመርር… እኝኚ ቢጀመር
አንተ ባዶ ከሆንክ …ለመስጠት ያልታደልክ
ቅን ሆና የመጣቿን …መንከባከብ ካልቻልክ
በሂደት ተወስውሳ …ቀልበስ ብትልብክ
ወይም አቅልህን ስተህ … ከሷ እንዳታለከልክ
ካሁኑ ተመዘን… ምርጫህንም መጥን።

ለአምሮትህ ብለህ …ባክነህ እንዳታባክን

ለሁሉም ወደቅኑ ጎዳና መመራትንና ሀቅን መግጠምን አላህ እንዲለግሰን እለምነዋለሁ።

≅≅≅💐🌸💐≅≅≅
abufewzan
🎐ዚል-ሂጅ'ጃ 07/12/1436
Septemer 21/09/2015