Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የዒልምና ዑለማእ ዘንድ የመቀመጥ በረከት


ከዓርአያዎቻችን አንደበት 
 
የዒልምና ዑለማእ ዘንድ
የመቀመጥ በረከት
🌴 🌴

ኢብነል-ቀይ'ዪም [ረሂመሁላህ] አሚረል ሙእሚኒን ዑመር ኢብነል-ኸጣብ [ረዲየላሁ ዐንሁ] ስለ እውቀትና ሊቃውንት ዘንድ በመፅናት እውቀት የመፈለግን ትሩፋት እንዲሁም ምንም ኃጢኣተኞች ብንሆን እንኳ ምክር ሰምተን፣ ስህተታችንን አውቀን፣ ታርመን ወደ ጌታችን በተቃረብን ቁጥር ጀርባችንን ያጎበጠውን ወንጀላችንን እንደሚያረግፍልን የተናገሩትን አጠር ያለችና ጥልቅ ምክር እንደሚከተለው ያወሱናል።

« አንድ ሰው የቱሃማ ተራሮችን የሚያህል ወንጀል ተሸክሞ ከቤቱ ይወጣል። ይሁንና ዒልምን ሲሰማ ፍርሃት ይይዘዋል፤ ወደ ጌታውም ይመለሳል፤ ተውበት ያደርጋል።
ወደ ቤቱም ያለምንም ወንጀል ፀዳ ብሎ ይመለሳልና ዑለማእ ዘንድ ከመቀመጥ እንዳትቦዝኑ »።

【ሚፍታህ ዳሩስ'ሰዓዳህ 1/122】
_______________

بـركـة الـعـلـم ومـجـالـسـة
الـعـلـمـاء
ذكر ابن القيم رحمه الله
أن أمير المؤمنين ﻋﻤﺮ ﺑﻦ ﺍﻟﺨﻄﺎﺏ - ﺭﺿﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻨﻪ قال -:
” إﻥ ﺍﻟﺮﺟﻞ ﻟﻴﺨﺮﺝ ﻣﻦ ﻣﻨﺰﻟﻪ
☜ ﻭﻋﻠﻴﻪ ﻣﻦ ﺍﻟﺬﻧﻮﺏ ﻣﺜﻞ ﺟﺒﺎﻝ ﺗﻬﺎﻣﺔ،
☜ ﻓﺈﺫﺍ ﺳﻤﻊ ﺍﻟﻌﻠﻢ ﺧﺎﻑ ﻭﺭﺟﻊ ﻭﺗﺎﺏ،
☜ ﻓﺎﻧﺼﺮﻑ إﻟﻰ ﻣﻨﺰﻟﻪ ﻭﻟﻴﺲ ﻋﻠﻴﻪ ﺫﻧﺐ،
👈 ﻓﻼ‌ ﺗﻔﺎﺭﻗﻮﺍ ﻣﺠﺎﻟﺲ ﺍﻟﻌﻠﻤﺎﺀ “.

ﻣﻔﺘﺎﺡ ﺩﺍﺭ ﺍﻟﺴﻌﺎﺩﺓ (١٢٢/١).
منقول
--------------
ዚል-ሒጅ'ጃ 05/12/1436
መስከረም 09/01/2008

Post a Comment

0 Comments