Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የወቅቱ ኣ ጀ ን ዳ ለሀጅና ዑምራ የሚቀርቡ እርዶችን (ሀድይ) በተመለከተ ከሠለፎች ፊቅህ


` የወቅቱ ኣ ጀ ን ዳ

💥ለሀጅና ዑምራ የሚቀርቡ እርዶችን (ሀድይ) በተመለከተ ከሠለፎች ፊቅህ

ፊቅህ በእውቀት ላይ የመስረፅ፣ ያወቁትን ደግሞ ግራ ቀኙን አስተውሎ የመገንዘብ ውጤት ነው። ለጥልቅ እውቀትና ግንዛቤ የበቁ ታላላቅ ምሁራንም ከብዙዎቹ ኡለሞች ለየት የሚያደርጋቸውን በርካታ ብቃቶችን ያስመዘግባሉ።

የሚዳስሱት መረጃና ግራ ቀኝ እንዲሁም በዙሪያው ላለው ነገር ያላቸው ምልከታ ሰፋ ያለ በመሆኑም አሻሚና ግልፅ ባልሆኑ ጉዳዮች ላይ እንኳ የሚሰጡት ብይን ሆነ ትንታኔ አርኪና አጥጋቢ ነው።

የአላህ መልእክተኛም ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ለሙጅተሂድ ሊቃውንት ሀቅን ሲገጥሙም ሆነ ሲስቱ ባለ መልካም ምንዳ መሆናቸውን መስክረውላቸዋል። ጥረታቸው እውነታው ጋር ለመድረስና ለሰዎችም ለማብራራት ነውና።

የምሁራንን ብቃት ገታ ላድርግና ከወቅታዊው ጉዳይ ጋር በተያያዘ ሀጅ ለማድረግ ሙተመቲዕ ወይም ቃሪን ሆኖ የሄደ ሰው እንዲሁም የሀጅ ወይም የዑምራ ዋጂብ የሆነን ነገር ያልፈፀመ ሰው ምን ማድረግ እንዳለበትና ሀጁ ወይም ዑምራው ብይኑ ምን እንደሆነ ከሊቃውንቶች አንደበት ላካፍላችሁ☞

1🔖ሙተመቲዕ ወይም ቃሪን የሆነ ሰው ሀድይ ማቅረብ አለበት ?
የእርዱ አነስተኛ መጠንስ ምን ያህል ይሆን?
•••••••••••••••••••••••••

ኢብኑ ከሲር [ረሂመሁላህ] አልበቀራህ ምእራፍ አንቀፅ 196ትን ሲፈስሩ «የሀጅ ወይም የዑምራ ስራችሁን (ኑሱካችሁን) መፈፀም ሲመቻችላሁና ከናንተ መሃል ዑምራን እስከ ሀጅ ተመቱዕ ማድረግ የፈለገ ማለትም አጣምሯቸው (ቂራን) ያደረገ ወይም በቅድሚያ ዑምራ አድርጎ ሲጨርስ ደግሞ ለሀጅ ኢህራም ያደረገ ሰው፤ በፉቀሃእ አነጋገር እንደሚታወቀው
" فَمَا اسْتَيْسَرَ مِنَ الْهَدْيِ
ከመስዋዕት ቤዛ አለበት" ብሏልና የቻለውን ሀድይ ይረድ። ይህም አነስተኛ መጠኑ አንድ በግ ይም ፍየል ነው።»
【ተፍሲር ኢብኑ-ከሲር(1/537)】
የማረጃ ስፍራውም በመካ የሃረም ክልል ነው።

2🔖ሙተመቲዕ ወይም ቃሪን የሆነ ሰው እርዱን ከሃረም ክልል ውጭ አርዶስ ከሆነ ?
••••••••••••••••••••••

የሀጅ ተግባሩን የፈፀመ ሰው የሀድይ እርዱን ያረደው ከመካ የሃረም ክልል ውጭ ከሆነ ሀጁ ትክክለኛ ቢሆንም ከሃረም ውጪ ላረደው ተተኪ ሌላ ሀድይ ሃረም ክልል ላይ ማረድ ግዴታው ነው። ወደ ሀረም መመለስ ያልቻለ እንደሆን እንኳን የሚተማመንበትን ሰው በመወከል በሃረም ክልል እንዲታረድለት ማድረግ ግድ ይለዋል።

ይህንንም ሸይኽ ኢብኑ-ባዝ [ረሂመሁላህ] ሲያስረዱን እንዲህ ይላሉ☞

« ተመቱዕ እና የቂራን ሀድይን ከሃረም ውጭ ማረድ አይበቃም (አይፈቀድም)። ከሃረም ውጭ እንደ አረፋት፣ ጂዳ እና የመሳሰሉት ቦታ ላይ አርዶ ስጋውን ሃረም ክልል ላይ ያከፋፈለው እንኳ ቢሆን ሀድዩ አልደረሰም። ስለዚህም ሀረም ላይ ሌላ ሀድይ ማረድ ይጠበቅበታል። ይህ እንግዲህ ባለማወቅም ይሁን አውቆት ከፈፀመው እንደገና ለማረድ ይገደዳል። ነቢዩ [ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም] خذوا عني مناسككم
የሀጅ አፈፃፀምን ከኔ ቅሰሙ ብለዋልና።
ሶሃቦቹም [ረዲየላሁ አንሁም] እሳቸውን [ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም] በመከተል እርዳቸውን ሃረም ክልል ላይ ፈፅመዋል።»
【መጅሙዕ ፈታዋ ኢብኑ-ባዝ: 18/ 31-32】

3🔖ከተመቱዕ እና ከቂራን ሀድይ የእርዱን ስጋ እሱም መመገብ ይችላልን ?
••••••••••••••••••

የተመቱዕ እና የቂራን ሀድይ የምስጋና ሀድይ ነው። በመሆኑም ለሀረም ድሆች ብቻ ማካፋፈሉ ግድ አይደለም። የዚህ ብይኑ ልክ እንደ ዑድሂያ ብያኔ ነው። ማለትም ከሚያርደው ነገር ላይ መመገብ ይችላል፤ ለሀረም ድሆችም ስጦታ መስጠትና ሰደቃ ማድረግም ይችላል። እንዲሁም አንድ ሰው የሙተመቲዕነቱን ወይም የቃሪንነቱን ሀድይ መካ ላይ ቢያርድና ከዚያም ስጋውን ከሃረም ክልል ውጭ ወደሆኑት ወደ ሸራኢዕ ወይም ወደ ጀዳ ወይም ወደሌሎች ስፍራዎች መውሰድ ከፈለገ ምንም ችግር የለበትም። ነገር ግን ከስጋው ላይ ለሃረም ድሆች መስጠቱ ግዴታ ነው። »
【ሸርሁል-ሙመት'ተዕ: 7/203】

4🔖ሙተመቲዕ ወይም ቃሪን የሆነ ሰው እርድ ማረድ ካልቻለስ ?
•••••••••••••••••••••••••

ሙተመቲዕ የሆነ ማለትም ዑምራን አድርጎ ካበቃና ነፃ ከሆነ በኋላ በሀጅ እለት ለሀጅ ኢህራም የሚያደርግ ሰው ወይም ቃሪን የሆነ ማለት ሀጅና ዑምራን ባንድነት ያጣመረ ሰው ሃድይ (እርድ) ማቅረብ አለበት። ካልቻለ የእርዱ ፋንታ ሶስት ቀናት መካ ላይ ይፆምና ሰባቱን ሀገሩ ሲገባ ይፆማቸዋል። ይህም ህግ የመካ ነዋሪ ላልሆነ ሰው ነው።

አላህ እንዲህ ብሏልና☞
[ሐጅንና ዑምራንም ለአላህ ሙሉ፡፡ ብትታገዱም ከሀድይ (ከመሥዋእት) የተገራውን (መሰዋት) አለባችሁ፡፡ ሀድዩም እስፍራው እስከሚደርስ ድረስ ራሶቻችሁን አትላጩ፡፡ ከናንተም ውስጥ በሽተኛ ወይም በራሱ ሁከት ያለበት የኾነ ሰው (ቢላጭ) ከጾም ወይም ከምጽዋት ወይም ከመሥዋዕት ቤዛ አለበት፡፡ ጸጥታም ባገኛችሁ ጊዜ እስከ ሐጅ በዑምራ የተጣቀመ ሰው ከሀድይ የተገራውን (መሠዋት) አለበት፡፡ ያላገኘም ሰው ሶስትን ቀኖች በሐጅ ወራት፤ ሰባትም በተመለሳችሁ ጊዜ መጾም አለበት፡፡ ይህች ሙሉ ዐሥር (ቀናት) ናት፡፡ ይህም (ሕግ) ቤተሰቦቹ ከቅዱሱ መስጊድ አቅራቢያ ላልኾኑ ነው፡፡ አላህንም ፍሩ፤ አላህም ቅጣተ ብርቱ መኾኑን እወቁ፡፡]
【አል-በቀራህ: (196)】

🌱ዋጂብ የሆነን ነገር ለሳተ⇣🌱

1💥ሙተመቲዕ ወይም ቃሪን የዑምራ ወይም የሀጅ ዋጂብ የሆነን ነገር ካልፈፀመ ምን ያድርግ ?
•••••••••••••••••••••

የሀጅ ወይም የዑምራ ዋጂብ የሆነ ነገርን ባለመፈፀም የሚደረግ እርድን በተመለከተ ከግዴታዎቹ አንዱን የተው ሰው ይህንን ጉድለት በግ ወይም ፍየል በማረድ መጠገን አለበት።

ከዐብደላህ ኢብኑ ዓባስ [ረዲየላሁ ዐንሁ] እንደተላለፈው “ ከኑሱኩ የሆነ ነገር የረሳ ወይም የተወ ሰው ደም ያፍስስ (እርድ ይረድ)። ” ብለዋልና።
【በኢማሙ ማሊክ ሙወጦዕ: 1583 ተዘግቧል】

2💥ዋጂብ የሆነን ነገር ባለመፈፀሙስ እርድ ማረድ ካልቻለ የመፆም ግዴታ አለበትን ?
••••••••••••••••••••
በተለይ ኢህራም ሳያደርግ ከሚቃት ያለፈ ሰው ወይም ካለፈ በኋላ ያደረገ ሰው ሀጁ ወይም ዑምራው ትክክል ነውን ? ደንቡን በመጣሱስ ምን ይሆን ቅጣቱ ?

ምላሹን ከኢብኑ ዑሰይሚን ህንካችሁ☞
«አንድ ሰው ለሀጅ ይሁን ለዑምራ ሲነሳ የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም] የወሰኗቸውን ሊሀርምበት ከሚገባው ሚቃት ውጭ [ካለፈው በኋላ] ኢህራም ካደረገ ኢህራሙ የግድ ነውና ትክክል ነው። ሀጁም ሆነ ዑምራውም ትክክለኛ ነው። ነገር ግን ሊቃውንት እንደሚሉት በሚቃቱ ላይ ኢህራም ማድረጉ የሀጁ ወይም የዑምራው ግዴታ ነው። ከሀጅ ወይም ዑምራ ግዴታዎች የሆነ ግዴታ ነገር የጣሰ ደግሞ ይህን ጉድለት የሚጠግንበት ቤዛ ማቅረብ አለበት።

ይህም መካ ላይ አንድ እርድ [በግ ወይም ፍየል…] ይታረድና እዚያው ላሉ ድሆች ይከፋፈላል። ከዚያ ስጋ ላይም ምንም መብላት የለበትም። አንዳንድ ሊቃውንት እንዳሉት ይህን እርድ መፈፀም ያልቻለ 10 ቀናት መፆም አለበት ይላሉ። ሌሎች ደግሞ ማረድ ካልቻለ ምንም የለበትም ብለዋል።

ይሁንና ትክክለኛው አቋም ማረድ ያልቻለ ሰው ምንም የለበትም የሚለው ነው። ምክንያቱም የሆነ ግዴታ ነገር ስለሳተ ቤዛ መክፈል ያለበት ሰው ካልቻለ 10 ቀናት ይፁም የሚል ትክክለኛ የሆነ ማስረጃ የለምና።»
[ሊቃእ ባበል-መፍቱህ: 14/175]

••••••••√√√••••••••
ዚል-ሂጅ'ጃ 06/12/1436
Sep 19/09/2015

Post a Comment

0 Comments