Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

እህቴ... ከድግምትና ከምቀኞች ሴራ አላህ ይጠብቅሽ!


√ ይነበብ!
እህቴ... ከድግምትና ከምቀኞች ሴራ አላህ ይጠብቅሽ!
ጥሩ ስብእና ያላቸው ምርጥ ሙስሊም ሴቶች በድግምት ሴራዎች ሲጠቁ ማየት እጅግ ያሳምማል። እርኩሶች፤ የሰውና፣ የጂን ሰይጣናት ሙስሊሟን ኢላማ ማድረግ ከጀመሩ ሰነባብተዋል። አዎን! የሙስሊሟ በሂጃቧ መበርታትና እራሷን ለእይታቸው ግልፅ አለማድረግ
እርኩስ ኢአማንያንን እረፍት ይነሳል። በሌላ በኩል ፀረ ኢስላም ሀይሎች የሙስሊሟን ጥንካሬና የአላማ ፅናት ለማሽመድመድ የሚነዟቸው ውዥንብሮችና የተለያዩ መሸንገያዎች ሁሉ እርባና ቢስ ሆነው ሲንኮታኮቱ ተመልክተዋል። ስለሆነም በተደራጀ መልኩ ሰይጣናዊ ተልእኳቸውን ለማሳካት እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ።
በትምህርት ተቋማት ያለው ሁኔታ ከማንም የተሰወረ አይደለም። በተለይም ጥሩ ውጤት የላትን ተማሪ ማሰናከላቸውና ከተሳካላቸውም የልጅቷ ኢስላማዊ ማንነት ሙሉ በሙሉ በማስወገድ ኩፍር ውስጥ እንድትገባ መጣራቸው የተለመደ ሆኗል። ይህ ባይሳካለቸው የማንም መሀይም የስሜት አገልጋይ ሆና እንድትቀር ይከጅላሉ።
እህቴ ሆይ! ሀሳብ አይግባሽ...
የአላህ መልእክተኛ ይህ አይነቱን ፈተናዎች የምናልፍባቸውን መንገዶች ሁሉ አስተምረውናል።
ካንቺ የሚጠበቀው ተውሂድሽን ከማጠንከር በአላህ ያለሽንም ተወኩል ከማበልፀግ ጋር በመጠበቂያ አዝካሮች መመሸግ ብቻ ነው።
[ﻓَﺎﻟﻠَّﻪُ ﺧَﻴْﺮٌ ﺣَﺎﻓِﻈًﺎ ۖ ﻭَﻫُﻮَ ﺃَﺭْﺣَﻢُ اﻟﺮَّاﺣِﻤِﻴﻦَ] يوسف 64
«አላህም በጠባቂነት (ከሁሉ) የበለጠ ነው፡፡ እርሱም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነው፤» ዩሱፍ 64
ችግሩ ሁሉንም ሙስሊሞች የሚያሳስብ በመሆኑና፤ ችግሩን ለመከላከል የሚረዱ የተለያዩ መርሀግብሮችን በመንደፍ ለተግባራዊነታቸው መንቀሳቀስ እንዲቻል ፕሮጀክቱን በሀላፊነት ተረክቦ የሚሰራ ተቋም በማስፈለጉ የአላህ ፍቃድ ሆኖ በቅርቡ "ሺፋእ የመንፈሳዊ ህክምና እና የምክር አገልግሎት" በበጎ ፍቃደኞች ተመስርቶ ከቀናት በፊት መስከረም 1/2008 በይፋ ስራዉን ጀምሯል።
ተከታዩ ፔጅ ይህንን አይነት ችግሮችን ለመቅረፍና ሳይከሰቱም ለመከላከል የሚያስችሉ ትምህርቶችን በማስተላለፍ አላማ ተመስርቶ ላለፉት ሶስት አመታት በመጠኑ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየ ሲሆን፤ በያዝነው የ2008 አመት በተቀናጀና ቀጣይነት ባለው መልኩ ጠቃሚ ትምህርቶችን ለማካፈል ይችል ዘንድ "ሺፋእ የመንፈሳዊ ህክምና እና የምክር አገልግሎት" በሀላፊነት ተረክቦታል።
ቁርአናዊ ፈውስ ለጂን እና ሲህር
www.Facebook.com/nosihr
ፔጁን like እና follow ማድረጋችን ብዙ እንደምንማርበት ተስፋ እናደርጋለን። ለሌሎችም የማስተዋወቅ ስራ በመስራት ሁላችንም የበኩላችንን አስተዋፅኦ እናድርግ።
በመጨረሻም፤ በነዚህ በተከበሩ ቀናት አላህ የድግምተኞችን ሴራ ያመክን፣ በድግምት የተጠቁ ሰዎችን ይታደግ ዘንድ ሀያሉን አላህ እንለምነው።
© ተንቢሀት

Post a Comment

0 Comments