Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

መካ gtm

መካ

ሀሳብ ሰንቄያለሁ ከዚያ ከበረሃ
አንጀት ከሚበላው ከሚያሰኘው ውሃ
የነሱመያ ጣር የነቢላል “አሐድ”

ያብከነክነኛል በትዝታ ንዳድ
በነብይ ዱዐ የሞላሽ በረካ
ሰላማዊት ሀገር ቅድስቲቷ መካ!

(ኢብኑ ሙነወር፣ ጳጉሜ 2/2006)