1. ሐላል ብቻ ይመገቡ፡፡ ያለበለዚያ በሚመገቡት ይጠየቃሉ፡፡ ዱዐዎትንም አላህ ባይቀበለዎት አይደነቁ፡፡ ስለዚህ የሚመገቡት ነገር ምንጩ ሀላል መሆን አለበት፡፡ ከዚያ ባለፈ ለጤናም፣ ለዲንም፣ ለኢኮኖሚም፣ ለቤተሰብም፣ ለማህበረሰብም ጎጂ የሆነ ነገር ሁሉ ሀራም ነውና ይራቁ፡፡
2. አቀራረቦን ያስተካክሉ፡፡ አንዴ ሁለቴ ያጋጥም ይሁን፡፡ ሁሌ ግን ይበቃል ተብሎ ከሚገመተው በላይ እያቀረቡ ያለጥንቃቄ ነካክቶ መድፋት ከአላህ ዘንድ ያስጠይቃል፡፡ አባካኞች የሸይጧን ወንድሞች ናቸውና፡፡
3. ከምግብ በፊት እጅዎን ይታጠቡ፡፡ ከጤናዊ ፋይዳውም ባለፈ ሱና ነው፡፡
4. ተስተካክለው ይቀመጡ፡፡ በምግብ ጊዜ ትራስ ላይ መደገፍ፣ መጋደም፣ ወይም ስርኣት የሌለው አቀማመጥ መቀመጥ ወይም ቆሞ መብላት ክልክል ነው፡፡
5. ቢስሚላህ ይበሉ፡፡
6. በቀኝ እጅዎት ይብሉ፡፡ በግራ መብላት የሸይጧን ስራ ነው፡፡ ሲጠጡም እንዲሁ፡፡ እቃው እንዳይጨማለቅ በሚል አጉል ምክኒያት በግራ እንዳይጠጡ፡፡ ወይ አስተካክለው ይያዙ፡፡ ያለበለዚያ እቃው ኋላ ይታጠባል እንጂ የሸይጧን ስራ አይስሩ፡፡
7. በሶስት ጣት መብላት ከሱና ነው፡፡
8. ከፊት ከፊቶ ይብሉ፡፡ አንዴ እዚያ ማዶ አንዴ እዚህ መቅበዝበዝ ስርኣት አይደለም፡፡
9. ከምግቡ አናት ወይም ከመሀሉ አይጀምሩ፡፡ መሀሉን ይደርሱበት የለ? ምን አናቱን/መሀሉን አስበረቆሰዎት? መናልባት ከመሀል ሳይደርሱ ከበቃዎትም ቀሪውን ሌላ ሰው ሊመገበው ይችላል፡፡ ከመሀል ሲጀመር ግን ለሌላ ሰው ይደብራል፡፡
10. በልክ ይብሉ፡፡ ሲበቃው ሳይሆን ሲያመው የሚያቆመው ህፃን ነው፡፡
11. ሲጨርሱ ጣትዎን ይላሱ፡፡ አንዳንዱ ካፊር እንዳይስቅብኝ ብሎ በዚህ ሱና የሚያፍር አለ፡፡ ጠላ እሚጠጣ፣ አሳማ የሚበላ፣ እስቲንጃ የማያደርግ ሰው ሳቀብኝ ብሎ ሱናን መተው እንዴት አይነት አሳፋሪ ነገር ነው?! አንዳንዱማ ጭራሽ አስቂኝ ነው፡፡ “እጅን መላስ ያስጠላል” ይላል፡፡ የበላህበትን እጅ መላስ ከደበረህ በሪሞት ኮንትሮል ብላ ወይ ደግሞ ምግቡን ጭራሽ ቶወው፡፡ አጂነብይ ሲጨብጡ አያፍሩም አይደብራቸውም፤ ሲዘፍኑ፣ ሲያዳምጡ አያፍሩም አይደብራቸውም፤ ወለድ ሲበሉ አያፍሩም አይደብራቸውም፤ … ሱና ለመተግበር ግን ያፍራሉ፣ ይደብራቸዋልም፡፡ ከእንዲህ አይነት የተገለበጠ ጭንቅላት አላህ ይጠብቀን፡፡
12. ሲጨርሱ አላህን ያመስግኑ፡፡
13. ተጋብዘው ከሆነ ለጋበዘዎት ዱዐ ያድርጉ፡፡
14. ጨርሰዋ; እጅዎትንና አፍዎትን ይጠቡ፡፡
15. ውሃ ሲጠጡ ይቀመጡ፡፡ ቆመው አይጠጡ፡፡
16. እንደማንቆርቆሪያ ባለ ነገር ሲጠጡ በጡቱ አይጠጡ፡፡ በጡቱ የሚመጣውን ውሃ ንፁህነት ማረጋገጥ አይቻልምና፡፡
17. የሚጠጡበት እቃ ውስጥ አይተንፍሱ፡፡ ለተመልካችም ያስጠላል፤ በሽታ የመተላለፍ እድሉም ሰፊ ነው፡፡ እንዳውም በሶስት እስትንፋስ እያረፉ መጠጣት ሱና ነው፡፡ ሱናውን እኛ ካልሰራነው ማን ይስራው?
===========
(ኢብኑ ሙነወር፣ 20/2/2005)