Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ዓኢሻና አሊሻ


ዓኢሻና አሊሻ
ሴት የማህበረሰቡ ግማሽ ነች፡፡ ቀሪውን ግማሽ ደግሞ ትወልዳለች፡፡ ስለሆነም የሷ መስተካከል የኡማው መስተካከል ነው፡፡ ጥፋቷም የህዝብ ጥፋት፡፡ ስትስተካከል ዓኢሻኛ ታወራለች፤ ሐምዛን ትወልዳለች፤ ፋጢማን ለዐልይ ታዘጋጃለች፤ ድንቅ ለሆነ የማህበረሰብ ግንባታ የማይነቃነቅ መሠረት ትሆናለች፡፡
ስትጠፋም ታዲያ አይጣል ነው፡፡ አጥፍቶ ጠፊ!!! በየጥጉ የተለጠፉ ራቁት ምስሎች ሁሉ የሷ መፈክር ይመስሏታል፡፡ ራቁት በሆነች ቁጥር የበለጠ “ነፃነት” ይሰማታል፡፡ ከአቡ ለሀብ ጋር ተጣምራ “ሐማለተል ሐጦብ” ሆና ሻሮኖችን ፈልፍላ ራይስኛ ፈንጥዛ ቡሽኛ ሂወት እየመራች ሁሉንም ይዛ ወደ ገደል!!! ያ ረቢ አንተ እህቶቻችንን የነ ዓኢሻን ምሳሌ የሚከተሉ አድርግል፡፡
(ኢብኑ ሙነወር፣ 2001)