በናንተ ምክኒያት ስንት ኢስላማዊ ተቋም ተዘጋ፣ ስንቱ ተደበደበ፣ ስንቱ ታሰረ፣ ስንቱ ሀገሩን ጥሎ ተሰደደ፣ ስንት የደዕዋ እንቅስቃሴ ተገታ ስንትስ ቤተሰብ ተናጋ ከምንም በላይ ደግሞ በኢስላም ስም ስንት የተበላሸ ዐቂዳ ደካሞች ላይ አሰረፃችሁ ኢስላምን ስንት አመት ወደ ኋላ ለሞገተት እየተውተረተራችሁ እንደሆነ ለማንም አይሰወርም - ለካፊር እንኳን - ለናንተ ሲቀር፡፡ እናንተማ ከሰል ጠቆረ ውሃ ቀጠነ ብላችሁ የምትከራከሩ ናችሁ፡፡ እናንተ እኮ “የትኋንና የቅማል ደም ነጃሳ ነው፤ የነካውም ሰው አወቀም አላወቀም ሶላቱ ውድቅ ነው” የምትሉ ናችሁ፡፡ ሀሰት ካላችሁ ኪታባችሁ ይናገራል፡፡ (ቡግየቱ ጧሊብ፡ 87(ሁለተኛ እትም፡ 119)) በጣም ጥሩ! እንዴት ያለች “ፅድት” ያለች እምነት ነች የዝንብ ጡሃራ አይነት እንዳትሆን ብቻ “የዝንብ ጧሃራ ከነጃሳ እኩል ነው” ትል ነበር እህቴ፡፡ አባባሉን ከየት እንዳመጣችው አላውቅም፡፡ ብቻ ሳስታውስ አጓጉል የሆነ ንፅህና ስታይ ነበር እንዲህ የምትለው፡፡ ግን አህባሽ “ጡሃሪት” በነጃሳ ያውም በውሻ ኩስ፣ ሽንትና ልጋግ ተጨማልቆ መስገድ ይቻላል ትላለች፡፡ (ቡግየቱ ጧሊብ፡ 99-100 (አዲሱ እትም፡ 131-132))፡፡ እኔን የገረመኝ “የትኋንና የቅማል ደም ነጃሳ ነው” ማለታቸው አይደለም፡፡ ምንም እንኳን የሚገርም ቢሆንም፡፡ እኔን የገረመኝ “በውሻ ኩስ፣ ሽንትና ልጋግ ተጨማልቆ መስገድ ይቻላል” ማለታቸውም አይደለም፡፡ ምንም እንኳን የሚገርም ቢሆንም፡፡ እኔን የገረመኝ የሚገርመኝም ሁለቱ የተራራቁ ሀሳቦች ካንድ አካል መውጣታቸው ነው፡፡ እስኪ አስቡት “የውሻ ኩስ አይነጅስም” ያለ ሰው “የትኋን ደም ይነጅሳል” ...
ይላል ኧረ ተመስጌን በሉ “ምራቋም ይነጅሳል” ብለው የካፊር መሳለቀያ ቢያደርጉን ምን ይባል ነበር፡፡ ሞኝ ባያፍር የሞኝ ዘመድ ያፍር፡፡
ለነገሩ እንዳው ቢገርመኝ አነሳሁት እንጂ ከዚህ የከፋ ስንት የዐቂዳ ክፍተት አለባቸው አይደለም ወይ ለምሳሌ “አላህ አለም ውስጥም የለም ከአለም ውጭም የለም፣ ከአለም ጋር ተያይዞም የለም ተነጣጥሎም የለም” የሚሉት፡፡ ሱብሐነላህ! ሰዎቹ ምን እየሆኑ ነው ይሄ ማለት ምን ማለት ነው ይሄም ብቻ አይደለም “አላህ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ አይደለም” ይላል ሸይኻቸው አብደላህ አልሀረሪ፡፡ ምነው ስትሉ “ለምሳሌ አላህ መበደል አይችልም” ሲል ይፈላሰፍባችኋል፡፡ እናስ ሶቅራጠስ አላህ ስላቃተው ነው እንዴ የማይበድለው ፍትሃዊ ስለሆነ እንጂ፡፡ ይሄውና በሐዲሰል ቁድሲ ላይ፡- “ባሮቼ ሆይ እኔ በራሴ ላይ በደልን ክልክል አድርጊያለሁ፤ በናንተም መካከል እንዲሁ ክልክል አድርጌዋለሁና አትበዳደሉ” ይላል ጌታችን፡፡ ስለዚህ ስለሚችል አይደለም እንዴ በራሱ ላይ ክልክል ያደረገው፡፡ ባይችል እንዲህ ይል ነበር ኧረ እነኚህ ሰዎች በምንኛ ነው የሚያስቡት
ይሄን ሁሉ እያደረጉ ከማንም በላይ ለኢስላም እየሰሩ እንደሆነ ይነግሩናል፡፡ ድንቄም፡፡ “ጊዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል” ነውና ነገሩ ይሄው ለጊዜው የሚችሉትን ብቻ ሳይሆን የማይችሉትንም ጭምር እያደረሱ ነው፡፡ “ውጭ ካለ መቶ ጠላት ቤት ውስጥ ያለ አንድ ጠላት የከፋ ነው” ይላሉ ዐረቦቹ፡፡ ጥፋታችሁ ምንኛ ከፋ!!! ይሄ አቋማችሁ ድንገት አንድ ቀን ተሳስታችሁ ካሰባችሁ ያሳፍራችኋል፡፡ ምናልባት፡፡ ኧረ አላህን ፍሩ፣ ሞት አለ፣ የቀብር ጥያቄ አለ፣ ነገ አላህ ፊት መቆም አለ፣ ሲራጥ አለ፣….፡፡ ከውስጣችሁ አላህን የሚፈራ የለምንዴ ለነገሩ ይሄ ቋንቋ መቼ ይገባችኋል ጨው ቀምሳችኋላ! ምነው “አልገባንም” ብላችሁ ዝም ባላችሁ!!! ገልብጣችሁ መረዳታችሁ ከፋ እንጂ፡፡
ግን ቢገባችሁም ባይገባችሁም ወላሂ ወቢላሂ ወተላሂ ትሸነፋላችሁ! እርግጠኛ ሆኜ ነው የምናገረው! እየጠነቆልኩ አይደለም፡፡ በጥንቆላም በኹራፋትም አላምንም፡፡ ይቺ የናንተ ናት፡፡ እናም እላለሁ፡፡ አይወድቁ አወዳደቅ ነው የምትወድቁት፡፡ ሰማያዊ፣ መለኮታዊ መመሪያ አንብቤ ነው ይህን የምለው፡፡ ኢስላምን ሊያጠቃ የመጣ የውስጥም ይሁን የዉጭ ጠላት መቼም ቢሆን ቋሚ ድል ሊቀናው አይችልም፡፡ ይሄው አብረን እናንብብ፡ ((የአላህን ብርሃን በአፎቻቸው ሊያጠፉ ይፈልጋሉ፤ አላህ ግን ከሃዲዎቹ ቢጠሉም ብርሃኑን የበላይ ያደርጋል))፡፡ ታማኙና እውነተኛው ነብይም ዐለይሂሰላም እንዲህ ይላሉ “ውርደትና ጥፋት ትእዛዜን በጣሰ ላይ ይሁን”
በርግጥ ብዙ መስዋእትነት ታስከፍሉ ይሆናል፡፡ ቢሆንም ዲኑ ብዙ ሊከፈልለት የሚገባ ዲን ነውና ወደ ኋላ አንልም፡፡ በአላህ ፈቃድ ትወድቃላችሁ፡፡ እንዳውም የሮማን አወዳደቅ ነው የምትወድቁት፡፡ ታዲያ አትሰሙም እንጂ ወድቃችሁ መውደቃችሁ ላይቀር መፈራገጥ ባታበዙ መልካም ነበር፡፡
“የማይበስል ጭንቅላት መብሰሉ ላይቀር የሰው ማገዶ ያስጨርሳል”
(ኢብኑ ሙነወር፣ 10/01/2005)