Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ከሰፈርና ከፌስቡክ አሚሮች ተጠንቀቁ!

· July 21, 2014 · 
Ibnu Munewor
ከሰፈርና ከፌስቡክ አሚሮች ተጠንቀቁ!
እነዚህ አታላዮች እራሳቸውን በራሳቸው ወይም ከመጋረጃ ጀርባ በሚያሰማሯቸው መሰሎቻቸው ወይም ደግሞ በየዋሃን ይመረጡና አሚርን ስለመታዘዝ የሚያትቱ ኢስላማዊ ማስረጃዎችን እንዳለ ያለምንም ሀፍረት መሀይማንን እንዳሻቸው ለመሾፈር ይጠቀሙባቸዋል፡፡ “እንዴት” ስትሉ “የአሚር ትእዛዝ ነው” ትባላላችሁ፡፡ የበርካቶችን ልቦና መቆጣጠራቸውን ካስረገጡ በዲን ስም ሙስሊሞችን ወደተለያዩ ጥፋቶች ይጣራሉ፡፡ ልክ ዛሬ እንደምናየው፡፡ የእነዚህን ብልጣብልጥ መሳዮች ግን ሞኞች ስርአት አልባ አሚርነት(ሹመት) ዋጋ የሚሰጠው ብዙ ነው፡፡ ምክኒያቱ ደግሞ ዲናዊ ሺፋን መጠቀማቸው ነው፡፡ ጥሪያቸውን “አቤት” ያለ አደጋ ላይ መውደቁ አይቀሬ ነው፡፡ የሚጣሩበት ሁሉ ባጢል አይሆንም፡፡ ይህን ቢያደርጉማ ማን ይሰማቸዋል፡፡ ይልቁንም ጥሪያቸው እውነትን ከሀሰት የቀላቀለ ነው፡፡ ወይም ደግሞ ምክኒያቱ እውነተኛ ሆኖ አካሄዱ ግን ሱናን መሰረት ያላደረገ ይሆናል፡፡ አካሄዳቸውን የማይጋራቸውን ዋሽተው ይወነጅላሉ! ቆርጠው ይለጥፋሉ! በሌለበት ያሳጣሉ፡፡ የነሱን ከሱና የተኳረፈ ወደ የትም የማያደርስ ውሽልሽል አካሄድ ያልደገፈን ሁሉ “ከኛ ካልሆንክ ከጠላት ነህ” የሚል የአስተሳሰብ ሽብር በመንዛት ያስበረግጋሉ ወይም ሌሎች እንዲጠራጠሩት ያደርጋሉ፡፡
ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከዕብ ኢብኑ ዑጅራህ ለተባለው ሰሓባቸው እንዲህ ብለውታል፡-
(ከዕብ ኢብኑ ዑጅራህ ሆይ! አላህ ከሞኞች ሹመት ይጠብቅህ!)
“የአላህ መልእክተኛ ሆይ! የሞኞች ሹመት ደግሞ ምንድን ነው?” አላቸው፡፡
(በመመሪያዬ የማይመሩ በሱናዬ የማይጓዙ ከኔ በኋላ ያሉ አሚሮች ናቸው!! ውሸታቸውን የሚያምን፣ በበደላቸውም የሚያግዛቸው፣ እነዚህ እኔም ከነሱ አይደለሁም፡፡ እነሱም ከኔ አይደሉም፡፡ ወደ ሐውዴም አይደርሱም፡፡ ውሸታቸውን ያላመናቸው፣ በበደላቸውም ላይ ያላገዛቸው እነዚህ ከኔ ናቸው፣ እኔም ከነሱ ነኝ፡፡ ወደ ሐውዴም ይደርሳሉ፡፡))
አልባኒ ሰሒሕ ብለውታል፡፡ (ሰሒሕ አትተርጊብ ወትተርሂብ፡ 2/268)