Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ማነው አሸባሪ? Gtm




ማነው አሸባሪ?
.
.
ዳኛው ቢጠፋ እንጂ ፍትህ አስከባሪ
እኛ ነን እነሱ ማነው አሸባሪ?!

ምንም ዳኛ ባይኖር እኛ እንነጋገር
ብዙም ርቀን አንሄድ ከስም እንጀምር
እስኪ እናነፃፅር
ሺፈራው አንበርብር
አስደንብር አሸብር
ወይስ አብዱል ገፉር
የቱ ነው እሚያሸብር?
ስምን መልአክ ያወጣዋል የሚለው ማን ነበር?
ማንም ያውጣው ማንም ሀቅ እንነጋገር
ሰላም እያስፈራው ሽብር የሚቀምር
ማነው “ያየህ ይራድ” ይሄን ሁሉ እሚያሴር
ይሄን ሁሉ እሚያስር?!
በዘመነ -መቶ ሺ ይፍራህ ቢጠሩት
መች በቅቶት መች ጠቅሞት?!
የሚሊዮን ሰላም የሱን ሰላም ነስቶት

(ኢብኑ ሙነወር፣ 29/2/2005)