Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ፈጣን ምላሽ ለአሚር ሳዳት አሕመድ



ፈጣን ምላሽ ለአሚር ሳዳት አሕመድ
1. “(ሰለፍዮችን) ከመሰሪዎቹ ይሁዲዎች ጋር የሚያመሳስሏቸውን ነጥቦች በአጭሩ ማንሳት እፈልጋለሁ፡፡”
#መልስ፡- ኧረ አላህን ፍሩ! እውነት ከኢኽዋንና ከሰለፍዮች የትኛው ነው ከአይሁድ ጋር የሚመሳሰለው? “ፂማችሁን አሳድጉ ከአይሁድ ጋር አትመሳሰሉ” የሚለውን ነብያዊ ትእዛዝ የሚያከብረው ወይስ በፂም የሚሳለቀው ያሳደጉትን በክፉ የሚያየው ኢኽዋኒ? የኢኽዋን መስራች ሐሰን አልበና ያደረገውን አገላብጡ፡፡ “ሀሰት” ካላችሁ በማስረጃ እመለሳለሁ)
- ከአይሁድ ጋር የሚመሳሰለው (ስብስብ ይመስሉሃል ልቦቻቸው ግን የተበታተኑ ናቸው) ሲል የገለፃቸውን የሁዶች ፋና ተከትለው ሺዐውንም፣ ሱፊውንም፣ ኸዋሪጁንም፣ ወዘተውንም አቅፈው በሀሰት “አንድ ነን” የሚሉት ኢኽዋኖች ወይስ “ቅድሚያ ለተውሒድ” የሚሉት ሰለፍዮች?
2. “ራሳቸውን ከወንጀል #በሙሉ አፅድተው፤የጀነት ዕጩዎች ያደርጋሉ፡፡”
#መልስ፡- እስኪ የትኛው ሰለፊ ነው “ከወንጀል ሙሉ ለሙሉ ንፁህ ነኝ” ያለው? ምናለ ጥላቻ አይንህን ባይጋርድህ?! ወላሂ ባንተ ውሸት ሰለፍዮች አይጎዱም የምትጎዳው እራስህ ነህ!!
- ቢገባህ ሸሂድ ሰይድ ቁጥብ፣ ሸሂድ ሀሰነልበና እያሉ የሸሂድነት ማእረግ የሚያከፋፍሉት ናቸው ይልቅ በማያውቁት ሰዎችን የጀነት እጩ እያደረጉ ያሉት፡፡
3. “በነገራችን ላይ እነኚህ አካላት በአሜሪካው CIA እና የሳኡዲ ደህንነት ስምምነት አሜሪካ የኢስላማዊ መነቃቃትን ወገብ ለመስበር፤ የስዑዲ መንግስት ደግሞ የንጉሳዊ አገዛዝ ህልውና ይቀጥል ዘንድ ኡማውን ብጥብጥ እንዲያደርጉ በነቀዘ አዕምሮ ተረግዘው የተወለዱ ስሪቶች እንደሆኑ የመስራቹ ሰው ፐሮፋይል ሲጠና ያመለክታል፡፡”
#መልስ፡- ወላሂ ወቢላሂ ወተላሂ ለዚህ ቅጥፈት አንዲት ነጠላ ማስረጃ የላችሁም፡፡ ቂላቂሎችን ለማጥመድ የምትጠቀሙበት የበሰበሰ መረብ ነው፡፡ ስለቅጥፈታችሁ ደግሞ አላህ ፊት ትጠየቃላችሁ፡፡
- ሰለፍያ አንዳንዶች እንደሚያላዝኑት ከመስከረም አስራ አንዱ ጥቃት በኋላ የተመሰረተ አንጃ አይደለም፡፡ እንዳውም አብዛሃኞቹ ጥመቶቻቸውን ያጋለጡ ኪታቦች የተፃፉት ከዚህ ክስተት በፊት ነው፡፡ ኢኽዋን ፀረ-ሱና ጠማማ አንጃ እንደሆነ ለምሳሌ እነ ሸይኽ አሕመድ ሻኪር፣ አልባኒ፣ ኢብኑ ባዝ፣ ኢብኑ ዑሠይሚን፣ ሙቅቢል በግልፅ አስፍረዋል፡፡ #ሁሉም ከመስከረም አስራ አንዱ ጥቃት #በፊት ነው የሞቱት፡፡ ሸይኽ ረቢዕ በሰይድ ቁጥብ ላይ ለፃፉት ኪታብ አልባኒ መግቢያ ፅፈውላቸዋል፡፡ አልባኒ የሞቱት በ1999 ሲሆን የአሜሪካው ጥቃት ደግሞ በ2001 ነው፡፡
4. “በኢስላማዊ እይታ እና ሚዛን እዚህ ግባ የማይባሉ ጥቃቅን ጉዳዮችን በማንሳት አቧራ ሲያቦሉ ይስተዋላሉ፡፡ ወንድማማችነት ዋጂብ ሆኖ እነርሱ ግን ነሽዳ ይበቃል አይበቃም እድር ሀራም ነው ላይ ሰውን በማነታረክ ልቡን ያቃቅሩታል፡፡”
#መልስ፡- ወንድሞችና እህቶች እባካችሁ በሰከነ አእምሮ አስተውሉ፡፡ እውን ሺርክ ከህዝባችን ውስጥ የተንሰራፋ አይደለምን? በበርካታ የዐቂዳ ችግሮች የተተበተበ ህዝብ የለንምን? ከጠንቋዩ ታምራት ዘንድ ይመላለሱ ከነበሩት ውስጥ ሙስሊሞችስ አልነበሩበትምን ዛሬ በርካታ ተመሳሳይ ጉዳዮች የሉምን? ታዲያ የዐቂዳ ጉዳይ እዚህ ግባ የሚባል አይደለምን? አስተዋይ የሆነ ሰው ይሄ ብቻ ለመወሰን ይበቃዋል፡፡ ለዐቂዳ ዋጋ የማይሰጥ ሰው ምን ያህል ነው ዋጋው?
- ስለ ቢድዐስ መነጋገር ሰዎችን የሚያንገሸግሻቸው ለምንድን ነው? ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “ቢድዐ ሁሉ ጥመት ነው” አላሉም እንዴ? ይህን ያክል ከቢድዐ ጋር ሙጭጭ ማለቱን ምን ይሉታል? ነብዩን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከወደዳችሁ ለምን ትእዛዛቸውን አታካብሩም?
- እናንተ ትንንሽ የምትሏቸውንም ነገሮች ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዋጋ ሰጥተው አስተምረዋቸዋልና ዋጋ እንሰጣቸዋለን፡፡ የፂም ጉዳይ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዋጋ ሰጥተው በቃልም በተግባርም ቢያስተምሩትም ለናንተ ግን ቀላል ነው፡፡
5. “ውሀ ቀጠነ ፤ ፀጉር ስንጠቃ ... ከነርሱ የጎርፍ ኩሬ ታህል እውቀት ጋር በማመዛዘን ሲያከፍሩ ፤የቢድዓ ኮድ ሲያድሉ እና ሙሽሪክ ሲያደርጉ በሙሉ መተማመን ነው፡፡”
#መልስ፡- በቅድሚያ እነማን ናቸው ባለኩሬ ታክል እውቀቶቹ እነ አልባኒ፣ ኢብኑ ባዝ፣ ሙቅቢል? ቀርዳዊ እንኳን (አል-ሐላል ወልሐራም) ኪታቡ ላይ የጠቀሳቸውን ሐዲሶች ብይን እንዲሰጡለት ለሸይኽ አልባኒ መስጠቱን ካላወቃችሁ እወቁ፡፡ ከ500 አካባቢ ሐዲሦች ውስጥ 1/5ኛ ያክሉ በኪታቡ ውስጥ የተጠቀሱት ሐዲሶች ደካሞች እንደሆኑ ብይን ሰጥተዋል፡፡ እውን ማነው ባለኩሬው ደፋር ጥራዝ ነጠቅ?! እነዚህን መሻኢኾች ሌላ፣ ተከታዮቻቸውን ደግሞ ሌላ ልታደርጉ ትፈልጋላችሁ፡፡ ልክ እነኚህ ታላላቆች ስለ ኢኽዋን እንዳላወሩ፡፡ ኢኽዋንን አልባኒ ፀረ ሱና እንደሆኑ ገልፀዋቸዋል፡፡ ኢብኑ ባዝ ከ72ቱ ጠማማ አንጃዎች ውስጥ ቆጥረዋቸዋል፡፡
- ደግሞ ሰለፍዮች ማንን አከፈሩ? ኧረ የውሸት ውንጀላችሁ የኋላ ኋላ ደጋፊዎቻችሁን ያሳጣችኋል፡፡ ይልቅ የሚያከፍሩትና ፅንፈኞቹ እነ ሰይድ ቁጥብ ናቸው፡፡ ይህን የናንተው ቀርዳዊም መስክሯል፡፡ ደግሞስ አህሉሱናን በጅምላ ከሚያከፍሩት ወይም ከሚያወግዙት ሺዓዎች ጋር ተቃቅፎ የሚሰራው ማነው? እነሱ ከማክፈር የቢድዐ ኮድ ከማደል ነፃ ሆነው ነው ከነሱ ጋር ህብረት የፈጠራችሁት?
6. “በርግጥ ሰነፍ ናቸው ነገር ግን ሰለፍ ነን ይላሉ፡፡”
#መልስ፡- አዎ ሰነፎች ነን፡፡ የሚተቹን ግን የከፉ ንፍሮዎች ናቸው፡፡ ደግሞ ሰለፍዮች እንጂ “ሰለፍ” ነን አላልንም፡፡ ይቺን እንኳ መለየት አትችሉም ማለት ነው የኛ ውቅያኖሶች? ይሄ እራሱ ኩሬ ታክል እውቀት ይዞ የሚንቦጫረቀው ማን እንደሆነ ያሳያል፡፡ ሰለፍ ሌላ ሰለፍይ ሌላ! ሰለፍ ማለት ቀደምት ማለት ነው፡፡ ሰለፍይ ደግሞ እነዚያን በነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አንደበት ምርጥነታቸው የተመሰከረላቸውን ቀደምቶች የሚከተል ማለት ነው፡፡ የሰለፍያን ምንነት የማያውቅ እንዲሁ ሌሎች ሲቃወሙ አይቶ ተቃውሞ የሚያስተጋባ ግልብ እንጂ ይህን የሚቃወም የለም፡፡ የሰለፍያ መንገድ የሶሐቦች መንገድ እንጂ ከቶ ሌላ አይደለምና፡፡ ማነው የሰሐቦችን መንገድ አልከተልም የሚለው? በሚገርም ሁኔታ ሙብተዲዖች እንኳን እራሳቸውን ሰለፍዮች ነን ለማለት በከንቱ ሲጣጣሩ የኢኽዋን ሮቦቶች ግን ሙጭጭ ብለው ቃሉን ይቃወማሉ፡፡ “እኛ ሙስሊሞች ብቻ ነን” ይላሉ ልክ ሰለፍዩ “ሙስሊም አይደለሁም” ያለ ይመስል፡፡ እነኚህ በሌሎች ጭንቅላት የሚያስቡ ሮቦቶች ከኢኽዋኑ መስራች ሀሰነል በና ዛሬ እስካለው ቀርዳዊ በሀሰት እራሳቸው የሰለፍያን መንገድ እንደሚከተሉ መናገራቸውን አያውቁም፡፡
- “ሰለፍያ” ማለትን መከፋፈል ሲያደርጉ፣ “አሽዐሪ፣ ሱፍያ፣ ኢኽዋን፣ ተብሊግ፣ ኸዋሪጅ (ኢባዲ)፣ አልፎም ሺዐ ማለት ግን መከፋፈል ነው ብለው አያወግዙም፡፡ በሰለፍያ ላይ እንደሚዘምቱትም አይዘምቱም፡፡ የኛ የአንድነት ጠበቃዎች ለምን በአንድ እራስ ሺ ምላስ ትሆናላችሁ?
7. “በእርግጥ ያለፉት ሰለፎች እንደዛሪዎቹ ሰለፍ ነን ባይ ሰነፎች አልነበሩም፡፡ ጀግኖች እንጂ እንደዛሬዎቹ በፍርሀት በየጓዳው ተደብቀው መርዛማ ምላሳቸውን የሚያወናጭፉ ምቀኞች አልነበሩም፡፡ ለኡማው የበላይነት ታግለዋል፡፡ በጦር ሜዳ ውለዋል፡፡ ኢብኑ ተይሚያ፤ኢብኑል ቀይም…ወዘተ”
#መልስ፡- በመጀመሪያ ለእውቀት ያክል ሸይኽ ረቢዕ አፍጋኒስታን ድረስ ሄደው ተዋግተዋል፡፡ የጠማሞችን ጥመት ስላጋለጡ ግን እንደፈሪ እየተሳሉ ነው፡፡ በርግጥ ይሄ የመሀይማኖቹ ስራ ነው፡፡ ያለበለዚያ ዐሊሞቹ እነ ኢብኑ ባዝ፣ አልባኒ፣ ኢብኑ ዑሠይሚንማ የሚደንቅ የሆነ አድናቆታቸውን ችረዋቸዋል፡፡ ኢማሙ አል-ዘህቢን አላህ ይማራቸውና “ጃሂል የራሱን ልክ አያውቅም ታዲያ እንዴት የሌሎችን ልክ ሊያውቅ ይችላል” ይላሉ፡፡
አዎ ሰለፎች ጀግኖች ነበሩ፡፡ ሙብተዲእ ላይ ብርቱዎች ነበሩ፡፡ አስታውሱ ኢማሙ ማሊክ ዛሬ ኢኽዋኖች የሚያቃልሉትን የኢስቲዋእ ጉዳይ ላይ ብዥታ ሊያነሳ የሞከረውን ሰው ሙብተዲእ እንደሆነ ተናግረው ከቤታቸው አባረውታል፡፡ ኢማሙ አሕመድ ለአንዱ ሰው ሙዓውያን ከሚሳደብ አጎቱ ጋር ምግብ እንኳን እንዳይበላ መክረውታል፡፡ ሙዐውያህ በሰይድ ቁጥብ ብዙ መወንጀሉን አስታውሱ፡፡ ሰለፎች ባደባባይ ህዝብ በተሰበሰበበት ሙብተዲእን ሲያጋልጡ ነበር፡፡ በየአጋጣሚው ሲያስጠነቅቁም ነበር፡፡ አንተ ስታስመስል የጠቀስከው ኢብኑ ተይሚያም ጠላት ወዳጁ ሁሉ የሚያውቀው ሙብተዲኦችን በማጋለጥ ነው፡፡ ሲጀመር በምን ምክኒያት ከእስር ቤት ሞተና፡፡ እንዳውም ዛሬ እናንተ ድብቅ የአይሁድ ሴራ የምትቆጥሩትን በአጥፊዎች ላይ መልስ መስጠትን በመሳሪያ ከሚደረገው ጂሃድ እንደሚበልጥ ነው የተናገረው፡፡ በስሙ የሚነግዱ ስለበዙ ጥቂት አባባሉን መቀንጨብ አይከፋም፡፡ (ወደ ቢድዐው የሚጣራ ሰው በሙስሊሞች የጋራ አቋም ቅጣት ይገባዋል፡፡ ቅጣቱ አንዳንዴ በሞት ሌላ ጊዜ ደግሞ ከዚያ ባነሰ ሊሆን ይችላል፡፡ ለምሳሌ ሰለፎች ጀህም ኢብኑ ሶፍዋንን፣ አልጀዕድ ኢብኑ ዲርሀምን፣ ገይላንንና ሌሎችንም ገድለዋል፡፡ #ቅጣት_የማይገባው ሆኖ ከተገኘ ወይም ደግሞ #መቅታቱ_የማይመች ሆኖ ከተገኘ#የግድ_ቢድዐውን_ማሳወቅና #ሰዎችን_ከቢድዐው_ማስጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ ይህን ማድረጉ አላህና መልእክተኛው ያዘዙት ከሆነው በመልካም ማዘዝና ከመጥፎ መከልከል ውስጥ የሚካተት ነው)) (አልፈታዋ፡ 35/414) (ከቁርኣንና ከሱና ጋር የሚፃረሩ ንግግሮች(መቃላት) ወይም ዒባዳዎች #ያላቸውን_ሰዎችሁኔታ #ግልፅ_ማድረግ፣ #ከነሱም_ህዝብን_ማስጠንቀቅ #በሙስሊሞች_የጋራ_አቋም #ግዴታ ነው፡፡ እንዳውም ኢማሙ አሕመድ “(ግዴታ ያልሆኑ ፆሞችን) የሚፆም፣ (ግዴታ ያልሆኑ ሶላቶችን) የሚሰግድና ኢዕቲካፍ የሚያደርግ ከሆነ ሰውና ከቢድዐ ሰዎች የሚያስጠነቅቅ ከሆነ ሰው አንተ ዘንድ ማንኛው ይበልጣል” ተብለው ሲጠየቁ እንዲህ ብለው ነው የመለሱት፡- “የመጀመሪያው ቢፆም ቢሰግድ ኢዕቲካፍ ቢያደርግ ለራሱ ነው፡፡ በቢድዐ ሰዎች ላይ ሲናገር ግን ለሙስሊሞች ነው እየሰራ ያለውና እሱ በላጭ ነው፡፡” ስለዚህ ኢማሙ አሕመድ ግልፅ እንዳረጉት በቢድዐ ሰዎች ላይ መናገር ጥቅሙ ልክ በአላህ መንገድ ላይ እንደመፋለም አጠቃላይ ለሙስሊሞች ዲናቸውን የሚጠብቅ ጥቅም አለው፡፡ ምክኒያቱም ከቢድዐ ባለቤቶች የአላህን መንገድና ሸሪዐውን ማፅዳት፣ በዲን ላይ መተላለፋቸውንም መከላከል በሙስሊሞች የጋራ አቋም ግዴታ ነው፡፡ የነኝህን ተንኮል ለመከላከል አላህ የሚመድበው ባይኖር ኖሮ ዲን ይጠፋ ነበር፡፡ በነዚህ ሰዎች አማካኝነት ዲን ላይ የሚደርሰው ጥፋት ደግሞ ጠላት የሙስሊም ሀገርን ይዘው ከሚያደርሱት ጥፋት የከፋ ነው፡፡ ምክኒያቱም ጦረኛ ጠላቶች አገርን ስለተቆጣጠሩ ልብንና በውስጧ ያለን ዲን ባንድ ጊዜ ማጥፋት አይችሉም - በሂደት ነው እንጂ፡፡ የቢድዐ ሰዎች ግን ከመጀመሪያ የሚያጠፉት ልብን ነው” (አልፈታዋ፡ 28/321፣232)
8. “ለኢስላም ኖረው ለርሱው የተሰዉ እና ለኢስላም የሚሰሩ ስብዕናዎችን ማጉደፋቸው”
#መልስ፡- ሰይድ ቁጥብ የተገደለው በመንግስት ላይ በማሴር ወንጀል ተከሶ እንጂ በሙስሊምነቱ አይደለም፡፡ እሱን ለመስቀል ስትሯሯጡ ሌሎችን ባላወቃችሁት አቅጣጫ እየወነጀላችሁ መሆኑ ቢታያችሁ መልካም ነበር፡፡
- በምንም ቢገደል ደግሞ የሱ በግፍ መገደል ኡማውን ማክፈሩን፣ ሶሐባ መሳደቡን፣... ሐቅ አያደርግለትም፡፡ ኻሪጂዩ ኢብኑ ሙልጂም ዐልይ ኢብኑ አቢ ጣሊብን ሲገድል ጀነትን አስቦ ነው “ለኢስላም ብሎ”፡፡ ከነህይወቱ በስለት ሲቆራርጡት ቁጭ ብሎ በፅናት ዚክር ሲያደርግ ነበር፡፡ በኢኽዋን ቀመር መሰረት ለኢስላም ኖሮ ለኢስላም የተሰዋ ታጋይ ነው ማለት ነው፡፡
9. “Rand corporation በ 2010 ባስነበበው annual report ላይ ፕሮፌሰር ኢማም ዩሱፍ አልቀርዷዊን theologian of terror (የሽብር ሰባኪ) በማለት የማይሳካ የረዥም ጊዜ የግድያ እና ጥቃት ዕቅድ ይዞ ነበር፡፡”
#መልስ፡- አሁን ይሄ ቀርዳዊን ከማስተዋወቅ ባለፈ ምንድን ነው ፋይዳው?
- በጠላት በአሸባሪነት የተወነጀለ ሁሉ ሐቅ ላይ ነው ማለት ነው? እንግዳው ከማንም በላይ በኢስላም ጠላቶች የምትወነጀለው ሳዑዲና የሳዑዲ ኣሊሞች ናቸው፡፡ አሁን እንኳን አሕባሽና ጋሻ አጃግሬዎቹ “ወሃቢ” እያሉ ጣታቸውን በቀዳሚነት የሚቀስሩት ወዴት እንደሆነ ሳር ቅጠሉ ያውቀዋል፡፡ ስለዚህ እነዚህን የሱና ዓሊሞች ከመወንጀል ምናለ ላፍታ እንኳን ብትታቀቡ?
- በአሜሪካ ስለተወነጀለ የቀርዳዊ ተራራ ተራራ የሚያካክሉ ስህተቶች ሐቅ ሊሆኑ ነው? አቤት ሂሳብ አቤት ጭንቅላት!
10. “ታዲያ ሰነፊዎቹ እነዚህን ብርቅ የኢስላም ፍሬዎች(ቁጥብና ቀርዳዊ) በሀሰት ማንቋሸሻቸው ለምን ይሆን፡፡” “መረጃ ብለው በስብዕናዎች ላይ የሚሰነዝሯቸው ጥቅሶች #በሙሉ ቅጥፈቶች ናቸው፡፡”
#መልስ፡- የቀርዳዊ ዘፈንን መፍቀድ፣ የሰይድ ቁጥብ ሰሀባ መሳደብ፣ ኡማውን በጅምላ ማክፈር፣ ኢስቲዋእን ዛሬ አሕባሾች በሚረዱት መልኩ ማስቀመጥ፣ የኢኽዋን በጥቅል ከሺዐ ጋር ጠንካራ ግንኙነት መመስረት፣... አሁን እነኚህ ነጥቦች ማስረጃ የሌላቸው ናቸው?
- ፀሀፊው ልክ እንደሌሎች ኢኽዋኖች በክር አቡ ዘይድን ሊያጥቅስ ሞክሯል፡፡ በዚህ ረገድ ሰዕድ አል-ሁሰይን የተባሉ ሸይኽ የፃፉትን ቢመለከት ይጠቀማል፡፡ ከሌሎች ዓሊሞች መሀል እየመረጠ አቋሙን የሚደግፍለትን ብቻ እየመረጠ የሚቀበለው ሙብተዲእ ነው፡፡ ሐቅ ፈላጊ የሆነ ሰው ረጋ ብሎ ነፃ ሆኖ ሌሎችስ ምን አሉ ብሎ ይመረምራል፡፡ የሰይድ ቁጥብን አደገኛ ስህተቶች በማጋለጥ በኩል ሸይኽ ረቢዕ ብቸኛ አይደluም፡፡ እውነቱን የፈለገ አያጣውም፡፡ ፀሀፊው በሚገርም ሁኔታ በክር አቡ ዘይድን አጣቅሶ “ሰይድ ቁጥብ (ረዐ) ቁርአን መኽሉቅ ነው የሚል አንዲትም ቃል አላገኘሁም” እንዳላለ “ይህ #ቁርአና#የተፈጠረው በአላህ እንጂ በሰው አይደለም” በማለት የገነባውን አፍርሷል፡፡ ታዲያ ከምኑ ነበር የተከላከለው? “ያላዋቂ ሳሚ ንፍጥ ይለቀልቃል!” ከሙብተዲዕ እከላከላለሁ የሚል ሁሉ ልክ እንዲህ ትርምስ ውስጥ ይዘፈቃል!!
11. “ኢስላማዊ መነቃቃት(ሰህዋ) እና መንሰራራት ለነርሱ የእግር እሳት ነው”
#መልስ፡- ፈያሱብሐነላህ! ኧረ ያረቢ ጠላቴን ብልጥ አርግልኝ! ቢያንስ ቢያንስ ምናለ ባይዋሽ! “ውሸትን ፈጥሮ የጠላቶቹ መገለጫ ያደረገው ጌታ ጥራት ይገባው” ይላል ኢብኑ ተይሚያህ ረሒመሁላህ፡፡ ይህን ለሺርክና ለቢድዐ ጠበቃ የምትሆኑበትን ለተውሒድና ለሱና ደንቃራ የምትሆኑበትን ከንቱ ልፋት ነው መነቃቃት የምትሉት? አዎ በዲን ስም እየነገዳችሁ የዋሆችን ማታለላችሁ በርግጥም ለሰለፊዮች የእግር እሳት ነው!!
12. “የእነ ዑመርን ልቦና በአንዲት ጀንበር መቀየርን አንግበው ነብያችን አልተነሱም፡፡”
#መልስ፡- ኢኽዋን ተውሒድን ትኩረቱ ሳያደርግ ሁሌ ለስልጣን ሲባዝን ሰማኒያ አምስት አመት ደፈነ፡፡ እንኳን ህዝብ ሊያተርፍ ተራሮቹም አነጋጋሪ የአቂዳ ግድፈቶችን መስራታቸውን ቀጥለዋል፡፡ እስኪ አሁን አንድ ቄስ ሞተ ብሎ “አላህ ይማረው” ብሎ ዱዓ የሚያደርገው አሊም ቀርቶ የትኛው ጃሂል ነው፡፡ እንደለመዳችሁት ሀሰት ካላችሁ ቀርዳዊን ከነድምፁ እናሰማችኋለን፡፡
13. “ሰነፎቹ በምንም መልኩ ዳእዋችን ከርዳዳ፤ ሰውን የሚያሸሽ ሸካራ የማይመች በርበሬ አይን የሚያቃጥል ነው፡፡”
#መልስ፡- የፀሀፊውን ሙሉ ፅሁፍ ግቡና እዩ፡፡ ከዚያ ለሚተቻቸው አካላት እንዲት ለስላሳ አረፍተነገር ሲጠቀም ካገኛችሁ ሞክሩ፡፡ ረሒመሁላህ ኢብኑ ተይሚያህ የሙብተዲዕ የመጀመሪያ ቅጣቱ ንግግሩ እርስ በርሱ መጋጨቱ ነው ይላል፡፡
14. “ኡማው በስልጣኔ እና እድገት ላይ ይወጣ ዘንድ ብናኝ ጥረት ማደረግ አይስተዋልም፡፡”
#መልስ፡- ኡማው ጨሌ እየጎዘጎዘ፣ ስኒ እየዘቀዘቀ፣ ለጠንቋይ እያጎበደደ እያየ “ሺርክ ሺርክ ተውሒድ ተውሒድ አትበሉ” እያለ ባሉበት ጨለማ እንዲጓዙ የሚያደርገውን ቅቤ አንጓችስ ምን እንበለው? ይሄ ነው ለስልጣኔ መስራት?
15. “ሁሉም ቀሚስ ለብሶ ኪታብ አንተልትሎ መስጊድ እንዲመላለስ እንጂ ‹‹ጠንካራ ሙስሊመ ከደካማው እንደሚሻል ማስተማርን ድርቅ መትቶታል፡፡ ትላልቅ ኢንዱስተሪዎችን ማቋቋም የሚችለው ሙስሊሙ ማህበረሰብ ካልሲ ቸርቻሪ እና ሞባይል ካርድ ሻጭ ሆኖ ይቀር ዘንድ ፤ በትምህርት እና ዕወቀት ቴክኖሎጂ ዘርፍ ምጡቅ መሆን የሚችለውን የብሩህ አዕምሮ ባለቤት ሰንካላ አድርጎ ማስቀረት የኤሁዶች እንጂ የሙእሚኖች ባህሪ አይደለም፡፡ እነዚህ ታዲያ ሙስሊሙን ሚና-ቢስ (role less) በማድረግ የሚወዳደራቸው የለም፡፡”
#መልስ፡- ሱሪህን ስለረገጥክ ፂምህን ስለላጨህ ጨረቃ ላይ መውጣት ከቻልክ አሳየን፡፡ ደግሞስ እውነት ለሙስሊሙ ጥንካሬ ከታሰበ ቀዳሚው ጠንካራ ዐቂዳ እንዲገነባ መስራት ነው፡፡ አቡ ጀህል ግዙፍ ግመል ያክል ነበር፡፡ ግን ተውሒድ ስለሌለው ቢከፍቱት ተልባ ነው ገለባ፡፡ ኢብኑ መስዑድ ደቃቅ ነበር ሰዎች የሚስቁበት እግረ-ቀጫጫ፡፡ ግሩ በተውሒድ ምክኒያት እነዚያ ደቃቅ እግሮቹ ከኡሑድ ተራራ የሚበልጥ ክብደት ይኖራቸዋል፡፡ ደግሞስ ሚና-ቢስ ማድረግ ማለት ምን ማለት ነው? ይህን መሰረት ሳትጥሉ ጣራ ለመስራት የምትሮጡበትን የቀውስ ሩጫ ነው ትልቅ ሚና የምታደርጉት? ወይ ጉድ! ጭራሽ ኪታብ መቅራት “ኪታብ ማንጠልጠል” እየተባለ የሚሳለቁበት ጊዜ ላይ ደረስን!! አዎ የምትፈልጉት ዲኑን በማስረጃ የማያውቅ ስትስሉ የሚስል ስታነጥሱ የሚያነጥስ ባዶ የኢስላም አፍቃሪ ወጣት ማፍራት ነው፡፡ ሚና-ቢስ ስትል እነማንን ለማለት እንደፈለግክ ገብቶኛል፡፡ በግልፅ ስትመጣ በግልፅ እፅፋለሁ፡፡ ለጊዜው ግን የምልህ የፈለግካቸውም ሰዎች ፊልም ለማየት ብለው በጁሙዐ ቀን ፊልም ቤት ዙህርና ዐስርን ባንድ ከሚሰግዱ የኢኽዋን አመራሮች ስንት እጅ ይሻላሉ፡፡
16. “የማህበራዊ ኑሮ ምስቅልቅልነት መንስኤዎች ተገንዝበውትም ሁን አሽትተውት ሁሌ የሚዘፍኑለት ዐቂዳ እና ተውሂድ ወደ ሰው ሲያስተምሩት ወደ ጉሮሮ ከተላከ ክሽሽ ካለ ዳቦ ይበልጥ አሳማሚ ስለሆነ ብዙ ጊዜ ስኬታማ ኤደሉም፡፡”
#መልስ፡- ታዲያ እናንተ በለስላሳው አንደበታችሁ ለምን አስተምራችሁ ውጤቱን አታሳዩንም? ኢኽዋን እሄው 85 አመቱ፣ የተወለደባት ግብፅ ላይ እንኳን ሚሊዮኖች የሚጎበኟቸው መቃብሮች ላይ የሚፈፀመው ጥፋት ዛሬም እንደቀጠለ ነው፡፡ የት አለ ስኬታችሁ? የት አለ ሚናችሁ? የት አል መነቃቃታችሁ? ለነገሩ “የሌለው አይሰጥም!!” እንኳን ለሌላ ሊተርፉ እራሳቸውንም አላዳኑም፡፡ ዛሬ እንኳን አለም በሰለጠነበት “ስልጡኖቹ” ኢኽዋኖች ራቢዐተል ዐደውያ ላይ ጫማ ሲያመልኩ ታይተዋል፡፡ በዚህ ገብቶ ማረጋገጥ ይቻላል፡፡https://www.facebook.com/photo.php?v=196745403833835&set=vb.274235849340927&type=2&theater እንደለመዱት አይናቸውን ጨፍነው “ውሸት ነው” ይላሉ፣ ጠብቁ፡፡ ሌሎችን ቀጥፈው ይወነጅላሉ፡፡ ከራሳቸው አይናቸውን ጨፍነው ይከላከላለ፡፡
17. “በነባራዊ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ችግር ላይ ለዐቂዳ ተቆርቋሪ ነን እያሉ በፌስቡክ እና መሰል ማህበራዊ ገፆች ላይ የተለመደ የመበጥበጥ ስራን የያዘባቸው የለም፡፡”
#መልስ፡- እውነት ለመናገር ትክክለኛው በጥባጭ በየትኛውም ምክኒያት ይሁን ህዝባችንን ከሺርክ ለማትረፍ አለመስራቱ አልበቃ ብሎ ሌሎች ሲሰሩ ደንቃራ የሚሆነው ግሳንግስ ነው፡፡
18. “እስቲ ‹‹መዓሊሚ ፊጦሪቅ›› ወይም ‹‹Milestones›› የሰይድ ቁጥብን መፅሀፍ አንብቡት፡፡ እውን ሀቦችን ይሰድባል! እንደውም ምዕራፍ አንድ ምን ሲል እንደሚጀምር ልነግራችሁ ፈለግሁ፡<< The unique quranic generation.>> ሲል ነው የሚጀምረው፡፡ ስም ማትፋቱ እና እንደ ጋሪ መነዳቱ ለምን ታዲያ!!!”
#መልስ፡- በኑ ኡመያን ጥቅማጥቅም የሚሰበስባቸው ሙናፊቆች ናቸው ማለት፣ ኢስላም ለነሱ እንደጥቅማቸው የሚለብሱት የሚያወልቁት ጋቢ ነው ማለት ሰሐባ መስደብ አይደለም? አሁን አንተ በዚህ መልኩ ብትገለፅ ትቀበላለህ? የዑሥማንን ገዳዮች ከኢስላም ሩሕ የመነጩ የኢስላም የመጀመሪያ አብዮተኞች ናቸው ማለት፣ የዑሥማን ኺላፋ በኢስላም ታሪክ ውስጥ የገባ ክፍተት ነው ብሎ መግለፅ ዑሥማንን ማንቋሸሽ አይደለምን? እርግጥ ነው የኢኽዋንን ጡት ሲጠባ ያደገ ሰው ከሰሐባ ይልቅ የቡድኑን ሰዎች ነው የሚያስቀድመው፡፡ ያለበለዚያ ስለሰይድ ቁጥብ እሱ ሰሐቦችን የገለፀበትን ያክል እንኳን ሳይባል ብዙ ስትወራጩ በውሸት ስትወነጅሉ እያየናችሁ ነው፡፡
19. “ኢስላም በእነርሱ መስታወትነት ቢለካስ!!!!! ውይ ኢስላም ከባድ እና አቸናናቂ ነበር!!! ቀሚስ ያለበሰ ሙስሊም ሰላምታ ሲያቀርብ አይመለስለትም፡፡ ሀጅር ይደረጋል፡፡ በተለይ ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎችማ ከማህበራዊ ኖሮ ግምትም ውስጥ አይገቡም፡፡ ኢስላም እንደነርሱ ከሆነ ይቅር ያሰናል፡፡ ኢስላማዊ እሴቶቻችንን ገደል ሊያስገቡ ሌት ተቀን በግር ፈረስ የሚኳትኑት ይሁዲዎች ከላይ የዘረዘርናቸውን ነገሮች ይተገብራሉ፡፡ ታዲያ ይህን ባህሪ የተጋራ ማንና ምን ሊሆን ይችላል፡፡”
#መልስ፡- ኢስላም በኢኽዋን መስታወት ቢለካስ ዘፈን የሚፈቅድበት፣ የፈረንጅ ዳንስ እየከፈሉ የሚማሩበት፣ ፊልም ለመከታተል እያሉ ጁሙዐ የሚተውበት፣ ሰሐባ የሚሰደብበት፣ ኡማው የሚከፈርበት፣ ሺርክ የሚነግስበት፣ ተውሒድ የሚጠላበት፣ ቢድዐ የተንሰረፋበት፣ ጠንቋይ የሚፈራበት፣ ለመቃብር ሐጅ የሚደረግበት፣ እንደ ኦርቶዶክስ በአላት የፈሰሱበት፣... አያችሁ ይህን “ኢስላም”?