ጥቂት የተንሻፈፉ እምነቶች በወልይ ዙሪያ
(ኮፒ ራይት የሌላቸው አድቬንቸር ፊልሞች?)
ለወልይ ያለን የተዛባ ግንዛቤ ለበርካቶች ሺርክ ላይ መዘፈቅ ትልቅ አስተዋፅኦ አለው፡፡ አንድን ሰው ወልይ ነው ሲሉ ብዙ ሰዎች ገይብ (አእምሮም፣ ህዋሳትም የማይደርሱበትን ነገር) የሚያውቅ፣ የታመመን የሚፈውስ፣ ጭንቅ ላይ ያለን የሚገላግል፣ “ሁን” ያለው የሚሆንለት፣… ነው ይላሉ፡፡ በዚህም የተሳሳተ ግንዛቤ የተነሳ የሩቁን “አውቃለሁ” ብሎ የሞገተ ሁሉ፣ ወይም የተሞገተለት ሁሉ እንደ ወልይ ተቆጥሯል፡፡ ጠንቋዮች ሳይቀሩ “አዋቂ” ናቸው እየተባሉ እንደ ወልይ የሚቆጠሩበት ብዙ አካባቢ እንዳለ ይታወቃል፡፡
ለወልይ ያለን የተዛባ ግንዛቤ የሰፋ የተንሰራፋ እንደሆነ ከሚያሳዩን ጥሩ ጠቋሚዎች፣ ግን አሳፋሪ እውነታዎች አንዱ ሀፃናት እንኳ ሲጫወቱ ከመሀላቸው አንዱ በቀላሉ የማይታወቅን ነገር “አውቃለሁ” ካለ “አንተ ወልይ ነህ እንዴ” ይባላል፡፡ ትንቢትና ወልይነት ያለ አግባብ ከመቆራኘታቸው የተነሳ “የሸህ እንትና ትንቢቶች”፣ “አራት አይናው” ፣ ቅብጥርሴ እያሉ መፅሀፍ እስከመፃፍም ተደርሷል፡፡
የሌሎችን አካባቢዎች በቅጡ ባላውቅም በተለይ በሀገራችን በአብዛሃኛው የወልይ ስርኣት ንጉሳዊ ስርኣት ነው፡፡ በውርስ የሚተላለፍ፡፡ አባቱ ወልይ የሆነ ሁሉ እሱም ወልይ ነው፣ ልጁም ወልይ ነው፡፡ ወልይነት በኢማን፣ በተውሒድ፣ በሱና የሚገኝ ሳይሆን በውርስ የሚተላለፍ ንጉሳዊ አገዛዝ ሆኗል፡፡
አስታውሳለሁ ልጅ እያለሁ በወልይ ቀብር አቅራቢያ ነው የምታልፉት ተብለን በቀብሩ ሳይሆን በትይዩው ስላለፍን ብቻ ጫማችንን እንድናወልቅ እንደረግ ነበር፡፡ ሱረቱ ጣሀ ላይ ከተጠቀሰው አላህ ሙሳን “በተቀደሰው ሸለቆ ውስጥ ነህና ጫማህን አውልቅ” ያለውን ለሸህየው ቀብር እየተጠቀሙበት እንደሆነ እጠረጥራለሁ፡፡ “ቀብር ጠባቂው ጂን እንዳይጣላችሁ ድምፃችሁን ዝቅ አርጉ” እየተባልን በሹክሹክታ ስናወራ ትዝ ይለኛል፡፡ ከሸሆች ቀብር አፈር እየተዘገነ ለበረካ፣ ለመድሀኒት ለሀጃ እየተባለ በፌስታል፣ በጨርቅ ሲታደልም በአይኔ አይቻለሁ፡፡ ከቤታቸው መረቅ የሚባል ነገር ሳያዩ አመት እየዞረ ከአንድ ወልይ ቀብር ዘንድ ግን አባታቸው በየጊዜው ፍየል እንደሚያርድ አንድ ጓደኛየ ነግሮኛል፡፡ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሚታወቅ ቦታ ለነበሩ አንድ ወልይ -ስማቸውን መጥቀስ አልፈልግም- እና ለሳቸው እየተባለ፣ በቦታው እያሉ ለጂን ሲታረድላቸው ተመልክቻለሁ፡፡
የቂሷውን ነገርማ ተውት!!! “እከሌ የሚባሉት ወልይ ጁሙዐ መካ ነበር የሚሰግዱት”፣ “አምስት አውቃት ሶላት ሀረም ነበር የሚሰግዱት”፣ “ሙሶላቸውን ቀይ ባህር ላይ አንጥፈው እንደዋዛ ሸገር ብለው ሐጅ አርገው መጡ”፣ “ሶላት ዐርሽ ላይ ነበር የሚሰግዱት”፣ “ልጅ እያሉ ለናታቸው እንጨት ለቅመው በእባብ አስረው ይመጡ ነበር”፣ “ዝናብ ያዘንቡ ነበር”፣ “እህል ያዘንቡ ነበር” ኧረ ምኑ ቅጡ! ምን የማይባል ነገር አለ! “እከሌ የሚባሉት ወልይ ነብር ይጋልቡ ነበር” የሚለው ብዛቱ!! ለመሆኑ ባገራችን ነብር ያልጋለበ ወልይ ይኖር ይሆን፡፡ እስኪ አሁን ነብር መጋለብ ምንድን ነው ፋይዳው? አድቬንቸር ፊልም ነው እንዴ ሺ ጊዜ ነብር ከመጋለብ 2 ረከዐ መስገድ አይሻልም!! “እከሌ የሚባሉት ወልይ ሌላውን ወልይ ካሉበት ሆነው በርቀት በመዕና ገደሏቸው”፣ “አከሌ ደግሞ ባንድ ሌሊት አርባ አባወራ ጨረሱ”፣ “እከሌ ደግሞ የሆኑ ሰዎችን ድንጋይ አረጓቸው” ሱብሐነላህ!!! ምንድን ነው ይሄ ሁሉ ሆረር? አይችሉም እንጂ ይሄን ሁኑ አርገው ቢሆን የመጨረሻ አውሬዎች ናቸው! ሰው በላዎች፡፡ ጫፍና ስሩን ያላገኘሁት አንድ ግጥ ትዝ አለኝ
… ሲቲና ሀለውያ
ስንት ወልይ ነበሩ
በሰማይ የሚበሩ!!!…
እሜቴ ሲቲና የየት ሀገር ወልይ እንደሆኑ አላውቅም፡፡ ግን ስማቸው ለጊዜው ትዝ ባይለኝም በቅፅበት የመን በረው ጫት የሚያመጡ፣ ወደ ግብፅ በረው ልዩ ፍራፍሬ ያመጡ የነበሩ እንስት ወሊያት እንደነበሩ አንዱ እሱ ለኢስላም አንድ ነገር አበረከትኩ ብሎ በሚያስበው መጥሀፉ ላይ ጠቅሷል፡፡ ይሄኛውማ ጭራሽ አያፍርም፡፡ እከሊት የሚባሉት ወልይ ጡታቸው መሬት ይነካ ነበር፡፡ ሩኩዕና ሱጁድ ሲያደርጉም ግራና ቀኝ ያጣፉት ነበር ይለናል፡፡ አሁን ይሄ አድናቆት ነው?
እዚጋ ደግሞ ሌላ ግጥም
አርሽ አደባባይ ያለው “ህም ህም”
የዘቡራ ልጅ ሰይድ ኢብራሂም
ላሐውለ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላህ!!! እዚጋ ደግሞ ሌላ ሙሲባ!
አደም ሲፈጠር ጭቃው ሲቦካ
ውሃ አግዘናል እንደ መለይካ
ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!!! እውነት እንዲህ ገጥመው ነው ወይስ አምላኪዎቻቸው ገጥመውባቸው ነው?
“በረሩ፣ ጋለቡ፣ ገደሉ፣…” ካልተባለ ወልይ አይሆኑም የተባለ ይመስል እንዲህ መቅደዱን ምን አመጣው?
እንዲህም ይሉናል “እከሊት የሚባሉት ወልይ አራት ጡት ነበራቸው፡፡” ምነውሳ እንስሳ ነበሩ እንዴ? እሺ ቀጥል “ከአራቱ ጡታቸው የተለያየ ነገር ነበር የሚታለበው፣ ካንዱ ወተት፣ ካንዱ ማር፣…” አቤት የሰው ልጅ!!! “የተማሩት” እንዲህ ካሉ መሀይሙ ምን ይበል እንዲህ አይነት የተማሩ ደንቆሮዎች ባሉበት ሀገር ነው እንግዲህ “ተውሂድ ተውሂድ አትበሉ” እየተባለ በተውሂድ ላይ ደባ የሚሰራው፡፡ አሁን ይሄ “ፈረሰኛው ጊዮርጊስ አድዋ ላይ ጣሊያኖችን ተዋግቷል” ከሚሉት የሀገራችን “ታሪክ ከታቢዎች” በምን ይለያል?
እያንዳንዱ የሚያውቀውን በዚህ ዙሪያ የሚፈፀሙና የሚራገቡ መሰረተ-ቢስ እምነቶችን (ኹራፋቶችን) ቢዘረዝር አቤት ስንት የሚገርም ነገር አለ?!
Ibnu Munewer