መጃሊሱ_ሸህሩ_ረመዷን
መጅሊስ 22 #ለይለተል_ቀድር
በነዚህ በተከበሩ የመጨረሻዎቹ አስር ቀናት ውስጥ አሏሁ - ሱብሓነሁ ወተዓላ - ከሌሎቹ ሌሊቶች ያላቃት እና በዚህ ህዝብ ላይ ትልቅ ችሮታውን የቸረባት የሆነችው ለይለተል ቀድር ትገኛለች። የሷን ትሩፋት አስመልክቶ አሏሁ - ተዓላ - እንዲህ ይላል ፦
{ إِنَّا أَنزَلْنَاهُ فِي لَيْلَةٍ مُّبَارَكَةٍ ۚ إِنَّا كُنَّا مُنذِرِينَ *
فِيهَا يُفْرَقُ كُلُّ أَمْرٍ حَكِيمٍ * أَمْرًا مِّنْ عِندِنَا ۚ إِنَّا كُنَّا
مُرْسِلِينَ * رَحْمَةً مِّن رَّبِّكَ ۚ إِنَّهُ هُوَ السَّمِيعُ الْعَلِيمُ *
رَبِّ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَمَا بَيْنَهُمَا ۖ إِن كُنتُم مُّوقِنِينَ }
°
[| እኛ (ቁርኣኑን) በተባረከች ሌሊት ውስጥ አወረድነው፡፡ * እኛ አስፈራሪዎች ነበርንና፡፡ በውስጧ የተወሰነው ነገር ሁሉ ይልለያል፡፡ * ከእኛ ዘንድ የኾነ ትእዛዝ ሲኾን (አወረድነው)፡፡ * እኛ (መልክተኞችን) ላኪዎች ነበርን፡፡ከጌታህ በኾነው ችሮታ (ተላኩ)፡፡ እነሆ እርሱ ሰሚው ዐዋቂው ነውና፡፡ * የሰማያትና የምድር በመካከላቸውም ያለው ነገር ሁሉ ጌታ ከኾነው (ተላኩ)፡፡ የምታረጋግጡ እንደኾናችሁ (ነገሩ እንዳልነው መኾኑን እወቁ)፡፡ |] (ዱኻን ፥ 3 -7)
አላህ የተባረከ በማለት ገለፃት። ምክንያቱም በውስጧ ብዙ መልካም ነገር ፣ በረካ እና ትሩፋት ስላላት ነው። ከበረካዎቿ ውስጥ ደግሞ ቁርአን በሷ ውስጥ መውረዱ ነው። እንደዚሁ በውስጧ በአመስ ውስጥ የሚከሰተው ነገር በሙሉ ይፈረድባታል።
በሌላም አንቀጽም ላይ እንዲህ ይላል ፦
{ إِنَّا أَنزَلْنَاهُ فِي لَيْلَةِ الْقَدْرِ * وَمَا أَدْرَاكَ مَا لَيْلَةُ
الْقَدْر * لَيْلَةُ الْقَدْرِ خَيْرٌ مِّنْ أَلْفِ شَهْرٍ * تَنَزَّلُ
الْمَلَائِكَةُ وَالرُّوحُ فِيهَا بِإِذْنِ رَبِّهِم مِّن كُلِّ أَمْرٍ * سَلَامٌ
هِيَ حَتَّىٰ مَطْلَعِ الْفَجْرِ }
[| እኛ (ቁርኣኑን) በመወሰኛይቱ ሌሊት አወረድነው፡፡ * መወሰኛይቱም ሌሊተ ምን እንደ ኾነች ምን አሳወቀህ? * መወሰኛይቱ ሌሊት ከሺሕ ወር በላጭ ናት፡፡ * በርሷ ውስጥ መላእክትና መንፈሱ በጌታቸው ፈቃድ በነገሩ ሁሉ ይወርዳሉ፡፡ * እርስዋ እስከ ጎህ መውጣት ድረስ ሰላም ብቻ ናት፡፡ |] (ቀደር ፥ 1-5)
ለይለተል ቀደር ሁለት ትርጉሞች አሏት። አንደኛው የክብር እና ደረጃ ያላት ሌሊት ማለት ሲሆን ሁለተኛው ትርጉሟ ደግሞ የመወሰኛዋ ሌሊት ነው። ይህም የተባለችው በሷ ውስጥ በአመቱ የሚከሰተውን ክስተት በሙሉ የሚወሰንባት ሌሊት ስለሆነች ነው።
ለይለተል ቀድር ብዙ ትሩፋቶች አሏት። ከነሱም ውስጥ ፦
1.ለሰዎች ልጆች መመሪያ የሆነውን እና በዱንያም ይሁን በአኺራቸው እድለኝነት የሚያገኙበት የሆነው ቁርአን የወረደበት ሌሊት ነው። *
2.መወሰኛይቱም ሌሊተ ምን እንደ ኾነች ምን አሳወቀህ? በማለት በጥያቄ መልክ መምጣቱ ያላትን ትልቅ ደረጃ ያመላክታል።
3.እሷም ከአንድ ሺወር በላጭ ናት። ይህም ማለት በሷ ውስጥ የሚሰራ ዒባዳ ከአንድ ሺ ወር በላይ የሚሰራ ዒባዳ ትበልጣለች።
4.መላኢካዎቹ እንደዚሁም "ሩሕ" ጂብሪል በጌታቸው ትእዛዝ ይወርዳሉ። እነሱ ደግሞ መልካም ነገርን ፣ በረካን እና እዝነትን እንጂ ይዘው አይወርዱም።
5.እሷም ሰላም ነች። ይህም የሆነው በዛች ሌሊት ውስጥ ባሪያው በሚሰራው መልካም ስራ ምክንያት አላህ ከእሳት እና ከቅጣት ነፃ የሚያወጣቸው ሰዎች ብዙ ስለሚሆኑ ነው። ጊዜዋም ፈጅር እስከሚወጣ ድረስ ነው።
6.አሏሁ - ተዓላ - እሷን ብቻ አስመልክቶ እስከ ቂያማ ቀን ድረስ የሚቀራ አንድ ሙሉ ምእራፍ አውርዷል።
7.ከትሩፋቶቿ ውስጥ ነብዩ - ﷺ - እንዲህ ይላሉ ፦ [ ለይለተል ቀድርን በአላህ አምኖ እንዲሁም ምንዳውን ከአላህ ፈልጎ የቆመ ሰው በፊት ያሳለፈው ወንጀሎቹ ይማሩለታል። ] (ሙተፈቁን ዓለይሂ ፤ ቡኻሪ ፥ 2017/ ሙስሊም ፥ 1169)
°
#ለይለተል_ቀድር_የምትገኘው_በረመዷን_ውስጥ_ነው። ምክንያቱም ቁርአን የወረደው በሷ ውስጥ መሆኑ እና አሏህ ደግሞ ቁርአንን በረመዷን ውስጥ እንዳወረደው እንዲህ በማለት መናገሩ ነው ፦
{ شَهْرُ رَمَضَانَ الَّذِي أُنزِلَ فِيهِ الْقُرْآنُ }
[| ቁርአን የወረደበትን ታላቁን የረመዷን ወርን ነው። .. |] (በቀራ ፥ 185)
°
በለይለተል ቀድር መውረዱን ሲናገር ደግሞ እንዲህ ይላል ፦
{ إِنَّا أَنزَلْنَاهُ فِي لَيْلَةِ الْقَدْرِ }
[| እኛ (ቁርኣኑን) በመወሰኛይቱ ሌሊት አወረድነው |] (ቀድር ፥ 1)
°
ነብዩም - ﷺ - ለይለተል ቀድር በረመዷን ነች ወይስ ከረመዷን ውጭ ነች ተብለው ሲጠየቁ [ በረመዷም ነች ] ብለዋል። ( ኢማሙ አሕመድ ፥ 5/171)
°
#ለይለተል_ቀድርም_የምትገኘው_በመጨረሻዎቹ_አስር_ቀናት_ውስጥ_ነው። ነብዩ - ﷺ - እንዲህ ይላሉ ፦ [ ለይለተል ቀድርን ከረመዷን በመጨረሻዎቹ አስር ቀናት ውስጥ ፈልጓት ] (ሙተፈቁን ዓለይሂ ፡ ቡኻሪ ፥ 1917 / ሙስሊም ፥ 1167)
°
ከጥንድ ቁጥሮች ይበልጥ ነጠላ ቁጥሮች ላይ መሆኗ የቀረበ ነው። ነብዩ - ﷺ - እንዲህ ይላሉ ፦ [ ለይለተል ቀድርን ከረመዷን ከመጨረሻዎቹ አስር ቀናት ውስጥ በነጠላዎቹ ላይ ፈልጓት ] (ቡኻሪ ፥ 1913)
°
ይበልጥ ደግሞ በመጨረሻዎቹ 7 ቀናቶች ላይ መሆኗ ይጠረጠራል። ማስረጃውም ዐብደሏህ ኢብኑ ዑመር - ረዲየሏሁ ዐንሁ - የነብዩ - ﷺ - ሶሐቦች ለይለተል ቀድርን በህልማቸው በመጨረሻዎቹ ሰባት ቀናት መሆኗን አሳያቸው ፤ ከዛም ነብዩ - ﷺ - እንዲህ አሉ ፦ [ ህልማችሁን በመጨረሻዎቹ ሰባት ቀናቶች ላይ የተገጣጠመች ሆና እያየሁ ነው ፤ የሚጠባበቃት ሰው በመጨረሻዎቹ ሰባት ቀናቶች ላይ ይጠባበቅ። ]
(ሙተፈቁን ዓለይሂ ፤ ቡኻሪ ፥ 1911 / ሙስሊም ፥ 1165) ይበልጥ ደግሞ በ27ኛው ሌሊት ላይ እንደሚጠረጠር የሚያመላክት (ሙስሊም ፥ 762) ላይ የተዘገበ ሐዲስ አለ።
°
#ለይለተል_ቀድር_በየአመቱ_በተነጠለች_ሌሊት_ላይ_ነች_ተብሎ_አይለይም። በአንዱ አመት ለምሳሌ በ27ኛው ሌሊት ልትሆን ትችላለች በሌላኛው አመት ላይ ደግሞ በ25ኛው ሌሊት ላይ ልትሆን ትችላለች። ይህም የአላህን ጥበብ እና ፍላጎት ተከትሎ ነው። ይህንንም የሚጠቁም ነብዩ - ﷺ - እንዲህ በማለት የተናገሩት ሐዲስ አለ ፦ [ ለይለተል ቀድርን በሚቀሩት ዘጠኞቹ ውስጥ ፣ በሚቀሩት ሰባቶቹ ውስጥ ፣ በሚቀሩት አምስቶቹ ውስጥ ፈልጓት። ] (ቡኻሪ ፥ 1917) ኢብኑ ሓጀር ፈትሑል ባሪ ላይ እንዲህ ብለዋል ፦ | ከተባሉት አባባሎች ውስጥ ከማስረጃ አንፃር ሚዛን የሚደፋው አባባል ለይለተል ቀድር ከመጨረሻዎቹ አስር ቀናቶች በዊትሮቹ ላይ መሆኗ እና መዘዋወሯ ነው። |
°
አላህ - ሱብሓነሁ ወተዓላ - ባሪያዎቹ ላይ ከማዘኑ የተነሳ ይህችን ሌሊት ደበቃት። የደበቀበት አንዱ ምክንያቱ እሷን ለመፈለግ ሲሉ ሶላት ፣ ዚክር ፣ ዱዓ እና የተለያዩ ዒባዳዎችን በማድረግ ወደ አላህ መቃረብን እንዲጨምሩ በማለት ነው። ሌላው የተደበቀችበት ምክንያት ደግሞ ለባሪያዎች
ፈተናም ጭምር ነው። በሷ ላይ ከልቡ ተነስቶ የጓጓ እና የጣረን ሰው ከሚሰላቸውን ሰው ለመለየት ማለት ነው።
°
በመሆኑም ይህችን ውድ ሌሊት በመፈለግ ላይ ተጣጣሩ ፤ ዝንጉነት እና ስልቹነትን ተጠንቀቁ። አላህ ሆይ ወሩን ከፆመ ለይለተል ቀድርን ካገኘና በሷም ውስጥ ባለው ትልቅ ምንዳ ከሚያገኙ ሰዎች አላህ ያድርገን።
_____________________________
***በጥቅሉ ሲታይ የቁርአን አወራረድ ሁኔታ ሁለት አይነት ነው። አንደኛው አወራረድ ሙሉው በአንድ ጊዜ በለይለተል ቀድር ላይ መውረዱ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ እንደ አስፈላጊነቱ በ23አመት ውስጥ መውረዱ ነው።
______________________________ ምንጭ ፦ "መጃሊሱ ሸህሩ ረመዷን" ሊብኒ ኡሰይሚን ከገፅ 123 - 128
(ግንቦት 5 /2010)
✍ኢብን ያህያ አህመድ @ Ibn yahya Ahmed
መጃሊሱ_ሸህሩ_ረመዷን
መጅሊስ 22 #ለይለተል_ቀድር
በነዚህ በተከበሩ የመጨረሻዎቹ አስር ቀናት ውስጥ አሏሁ - ሱብሓነሁ ወተዓላ - ከሌሎቹ ሌሊቶች ያላቃት እና በዚህ ህዝብ ላይ ትልቅ ችሮታውን የቸረባት የሆነችው ለይለተል ቀድር ትገኛለች። የሷን ትሩፋት አስመልክቶ አሏሁ - ተዓላ - እንዲህ ይላል ፦
{ إِنَّا أَنزَلْنَاهُ فِي لَيْلَةٍ مُّبَارَكَةٍ ۚ إِنَّا كُنَّا مُنذِرِينَ * فِيهَا يُفْرَقُ كُلُّ أَمْرٍ حَكِيمٍ * أَمْرًا مِّنْ عِندِنَا ۚ إِنَّا كُنَّا مُرْسِلِينَ * رَحْمَةً مِّن رَّبِّكَ ۚ إِنَّهُ هُوَ السَّمِيعُ الْعَلِيمُ * رَبِّ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَمَا بَيْنَهُمَا ۖ إِن كُنتُم مُّوقِنِينَ }
°
[| እኛ (ቁርኣኑን) በተባረከች ሌሊት ውስጥ አወረድነው፡፡ * እኛ አስፈራሪዎች ነበርንና፡፡ በውስጧ የተወሰነው ነገር ሁሉ ይልለያል፡፡ * ከእኛ ዘንድ የኾነ ትእዛዝ ሲኾን (አወረድነው)፡፡ * እኛ (መልክተኞችን) ላኪዎች ነበርን፡፡ከጌታህ በኾነው ችሮታ (ተላኩ)፡፡ እነሆ እርሱ ሰሚው ዐዋቂው ነውና፡፡ * የሰማያትና የምድር በመካከላቸውም ያለው ነገር ሁሉ ጌታ ከኾነው (ተላኩ)፡፡ የምታረጋግጡ እንደኾናችሁ (ነገሩ እንዳልነው መኾኑን እወቁ)፡፡ |] (ዱኻን ፥ 3 -7)
አላህ የተባረከ በማለት ገለፃት። ምክንያቱም በውስጧ ብዙ መልካም ነገር ፣ በረካ እና ትሩፋት ስላላት ነው። ከበረካዎቿ ውስጥ ደግሞ ቁርአን በሷ ውስጥ መውረዱ ነው። እንደዚሁ በውስጧ በአመስ ውስጥ የሚከሰተው ነገር በሙሉ ይፈረድባታል።
በሌላም አንቀጽም ላይ እንዲህ ይላል ፦
{ إِنَّا أَنزَلْنَاهُ فِي لَيْلَةِ الْقَدْرِ * وَمَا أَدْرَاكَ مَا لَيْلَةُ الْقَدْر * لَيْلَةُ الْقَدْرِ خَيْرٌ مِّنْ أَلْفِ شَهْرٍ * تَنَزَّلُ الْمَلَائِكَةُ وَالرُّوحُ فِيهَا بِإِذْنِ رَبِّهِم مِّن كُلِّ أَمْرٍ * سَلَامٌ هِيَ حَتَّىٰ مَطْلَعِ الْفَجْرِ }

0 Comments