የሰለፍያ ደዕዋ ከሽብርና ከአሸባሪዎች የፀዳ ነው!!
(ለዚህ ፅሁፍ መነሻ የሆነኝ ከሰሞኑ በኤፍ ኤሞቻችን የተለያዩ በቀቀኖች ሰለፍያን ከሽብር ጋር ሲያቆራኙ መስማቴ ነው፡፡)
የኸዋሪጅ ፍልፍሎች በተለያዩ አካላትና ተቋማት ላይ ሽብር በፈፀሙ ቁጥር ጣታቸውን ወደ ሰለፍያ አስተምሮ የሚቀስሩት ብዙ ናቸው፡፡ አንዳንዶቹ ባለማወቅ ሲሆን ሌሎች ግን ሆን ብለው ነው ይህን የሚያደርጉት፡፡ ነገር ግን ማንም ቢቀጥፍም ሰለፍያ ከየትኛውም የሽብር ድርጊት ንፁህ ነው፡፡ ለዚህም ማረጋገጫ የሚሆነን
1. የሰለፍያ ዑለማዎች ባንድ ድምፅ በንፁሃን ላይ የሚፈፀሙ የሽብር ድርጊቶችንና እነሱን በገንዘብ የሚያግዙ አካላትን ያወግዛሉ፡፡ የዑለማዎቹን ብይን በዚህ ሊንክ ገብተው ናሙና ይመልከቱ፡፡ http://www.alifta.net/BayanNew.aspx…
2. የሰለፍያ ዑለማዎች የአጥፍቶ መጥፋት ድርጊት ያወግዛሉ፡፡ ብይናቸውን በዚህ ሊንክ ገብተው ያረጋግጡ፡፡ http://www.sahab.net/forums/index.php?showtopic=114416
3. የሰለፍያ ዑለማዎች እንደ ኡሳማ ቢን ላደን፣ አልቃዒዳህ እና አይኤስ ያሉ የሽብር ሞተሮችን እና አንጃዎችን ያወግዛሉ፡፡ የዑለማዎቹን ብይን በዚህ ሊንክ ገብተው ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡
ስለ ቢንላደን http://www.alrbanyon.com/vb/showthread.php?t=3763
ስለአልቃኢዳህ http://www.ajurry.com/vb/showthread.php?t=35650
ስለ አይኤስ http://ajurry.com/…/%D8%AA%D8%AD%D8%B0%D9%8A%D8%B1-%D8%A7%…/
4. የሰለፍያ ዑለማዎች አሸባሪ ኸዋሪጆችን በተግባር የተቀላቀለ ብቻ ሳይሆን ለነሱ የሚሟገት በሀሳብ የሚጋራቸውም ከነሱው ከአጥፊዎቹ እንደሚቆጠር ተናግረዋል፡፡ ይህን ሊንክ ይመልከቱ፡፡ https://www.youtube.com/watch?v=tOXwGaL1c4I
5. የሰለፍያ ዑለማዎች በሙስሊም መሪዎች ላይ ማመፅን ያወግዛሉ፡፡ የአሸባሪዎቹ ዋና መገለጫና ዘመቻ ግን ከማንም በላይ በሙስሊም መሪዎች ላይ ጦር መስበቅ ነው፡፡ ስለዚህ ነጥብ የዑለማዎቹን አቋም በዚህ ገብተው ይመልከቱ፡፡ http://www.ajurry.com/vb/showthread.php?t=18162
6. የሰለፍያ ዑለማዎች በሀሳብ የማይጋሯቸውን ሙስሊሞች እንደ ከሃዲ መቁጠር (ማክፈርን) በፅኑ ያወግዛሉ፡፡ የኸዋሪጅ አስተሳሰብ ተከታዮች የሆኑት አሸባሪዎቹ ግን በአመለካከት የማይጋሯቸውን ሙስሊሞች ከመሪ እስከተመሪ፣ ከዑለማእ እስከ ተራው ህዝብ ያከፍራሉ፡፡ ከዚህም በመነሳት ሙስሊም ባልሆኑ አካላት ላይ ከሚፈፅሙት በላይ በሙስሊሞች ላይ የሚፈፅሙት አረመኔያዊ ድርጊት እጅጉን የከፋና የላቀ ነው፡፡ ሙስሊሞችን ያርዳሉ፣ ይጨፈጭፋሉ፣ ከመስጂድ ውስጥ ሳይቀር በማፈንዳት እልቂት ይፈፅማሉ፡፡ ይህን እንደ ናሙና ይመልከቱ፡፡ https://www.youtube.com/watch?v=n2_NQTrkOyU
7. የሰለፍያ ዑለማዎች እነዚህን በኢስላም ስም የሚነግዱ፣ ነገር ግን ኢስላምን ጥላሸት የሚቀቡ ፅንፈኞችን ለሚመለከተው አካል አሳልፎ መስጠት እንደሚገባ ይናገራሉ፡፡ በዚህ ሊንክ ይግቡና አንድ ናሙና ይመልከቱ፡፡ https://www.facebook.com/521762064636130/videos/629867173825618/
8. የሰለፍያ ዑለማዎች አይን ያወጣውን ሽብር ቀርቶ “ሰላማዊ” ሰልፍን እንኳን አይፈቅዱም፡፡ በዚህ ይግቡና አቋማቸውን ይመልከቱ፡፡ http://www.alrbanyon.com/vb/showthread.php?t=3339
9. የሰለፍያ ዑለማዎች አሸባሪዎች ከሚፈፅሙት በተለየ ሙስሊሞች እንኳን ባይሆኑ በህጋዊ መልኩ ወደ ሀገር የገቡ ሰራተኞችን፣ ጎብኚዎችን ወይም ዲፕሎማቶችን መግደል ከኢስላም አስተምሮ ያፈነገጠ እንደሆነ ያስተጋባሉ፡፡ አቋማቸውን በዚህ ገብተው ይመልከቱ፡፡ http://alhanbaly.blogspot.com/2012/09/blog-post_17.html
እንዲያውም እነዚህ አሸባሪዎች
1. የመጀመሪያ ጣታቸውን የሚቀስሩት በሰለፍያ አስተምሮ እና በሰለፍያ ዑለማዎች ላይ ነው፡፡ ለዚህም በሊብያ፣ በግብፅ፣ በአፍጋኒስታን እና በሌሎችም ሀገራት በርካታ የሰለፍያ ዑለማዎችንና ተማሪዎችን መግደላቸው፣ እነ ሸይኽ ሳሊሕ አልፈውዛንን ለመግደል መዛታቸው ዋቢ መሆን ይችላል፡፡
2. ይልቁንም እነዚህ የሽብር አጋፋሪዎች “የሙስሊም ወንድማማቾች” የሚባለው መሰረቱን ግብፅ ያደረገው አንጃ ተከታዮች ናቸው፡፡ ለዚህ ደግሞ ከራሳቸው ጭምር ምስክርነት አለ፡፡ ዝርዝሩን በዚህ ሊንክ ገብተው ማግኘት ይችላሉ፡፡ http://www.sahab.net/forums/index.php?showtopic=68486
በሰለፍያ አስተምሮ ላይ የሚቀጥፉት ብዙ አይነት ናቸው፡፡ ለምሳሌም
1. ኢስላምን መምታት የሚፈልጉ ጠላቶች በዋናነት ሰለፍያ ላይ ያነጣጥራሉ፡፡ ምክንያቱም የጥንቱን የነብዩን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አስተምሮ የሚወክለው ሰለፍያ እንደሆነ ስለሚያውቁ፡፡
2. ሌሎች ደግሞ አላማቸው በትክክልም ኢስላምን ሳይሆን ሽብርን መዋጋት ሆኖ ሳለ ነገር ግን የግንዛቤ እጥረት ስላለባቸው የሽብር ምንጩ በተሳሳተ መልኩ የሰለፍያ አስተምሮ እንደሆነ የሚገምቱ አሉ፡፡
3. አሸባሪዎቹ ደግሞ እራሳቸው ለሰለፍያ ደዕዋ እና ለሰለፍያ ዑለማዎች ጠላት ናቸው፡፡ ከየትኛውም ሀይል በላይ፣ ከየትኛውም ፀረ-ሽበር ህግና የተቀናጀ ስራ፣ የተደራጀ ጦር በላይ የሰለፍያ አስተምሮት ድራሻቸውን እንደሚያጠፋቸው፣ እርቃናቸውን እንደሚያስቀራቸው ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡ ስለሆነም የራሳቸውን ጥፋት ወደ ሰለፍያ በማስጠጋት ማስመታት ወይም ማጠልሸት ይሻሉ፡፡
ሼር በማድረግ የበኩላችንን እንወጣ፡፡ ሰለፍያን ከሴረኞች ማጠልሸት እንከላከል፡፡