ጥያቄ፡፦ የፆም ሥርዓቶች ምንድን ናቸው?
መልስ፦ ከፆም ሥርዓቶች አንዱ የታዘዙትን ነገሮች በመፈፀምና ከተከለከሉት ነገሮች በመራቅ በአላህ ተቅዋ ላይ መሆን ነው። አላህ እንዲህ ይላልና፦
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ كُتِبَ عَلَيْكُمُ ٱلصِّيَامُ كَمَا كُتِبَ عَلَى ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِكُمْ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ
<<እናንተ ያመናችሁ ሆይ ጾም በነዚያ ከናንተ በፊት በነበሩት (ሕዝቦች) ላይ እንደ ተጻፈ በናንተም ላይ ተጻፈ (ግዴታ ተደረገ) ልትጠነቀቁ ይከጀላልና፡፡>> (አል-በቀራ፡ 2፥183)

ነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) << የውሸት ንግግር፣ በውሸት መስራትንና፣ የመሐይምን ሥራ መስራት
ያልተወ ሰው ምግቡንና መጠጡን ከመተዉ አላህ ጉዳይ የለውም>>ብለዋል (ቡኻሪ ዘግበውታል)።
ሰደቃን፣ በጎ ተግባራትንና ለሰዎች በጎ መዋልን ማብዛትም ከፆም ሥርዓት (አደብ) አንዱ ነው። በተለይም በረመዳን ውስጥ። ነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እጅግ በጣም ለጋስ ነበሩ ይበልጥ ለጋስ የሚሆኑት ደግሞ በረመዳን ውስጥ ጅብሪል ተገናኝቷቸው ቁርአን በሚያስቀራቸው ጊዜ ነበር (ቡኻሪ ዘግበውታል)።
አላህ ሀራም ካደረጋቸው ነገሮች መራቅም ከፆም አደቦች አንዱ ነው። ከውሸት፣ ከመሳደብ፣ ከማታለል፣ ከመክዳት፣ ሐራምን ከማየትና ከማዳመጥ እና ከመሳሰሉት ሐራም ድርጊቶች ፆመኛም ሆነ የማይፆም ሰው መራቅ አለበት። ፆመኛ ግን ይበልጥ መራቅ ይጠበቅበታል።
ከአዳቦቹ አንዱ ሱሑርን መብላት ነው። ሱሑርን አዘይግቶ መብላት። ነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) << ሱሑርን ብሉ ሱሑር በረካ አለውና >> ብለዋል (ብኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)።
ከአዳቦቹ አንዱ በእሸት ቴምር ካላገኘ በደረቅ ቴምር ካላገኘ በውሃ ማፍጠር ነው። ፀሀይ መጥለቋ ከተረጋገጠ ለፍጡር መቻኮልም ከአዳቦቹ ነው። ነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) << ሰዎች ለፍጡር እስከተቻኮሉ ድረስ ኽይር ላይ ናቸው...>> ብለዋልና (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)።
( ሸይኽ መሐመድ ኢብኑ ሷሊህ አል-ዑሰይሚን ረሒመሁላህ )