==የረጀብ ወር ማስታወሻ== ክ/1
( ጊዜ መጀመሪያ አሏህ ሰማይና ምድርን ሲፈጥር ወደነበረበት ስራዓቱ ተመልሷል ዓመት 12 ወር ነው ከነዚህ ወራት ውስጥም አራቱ ልዩ ክብር ያላቸው ናቸው ሶስቱም ተከታታይ ናቸው ዙልቀዕዳ ዙልሒጃ ሙሐረም እና በጁማደል ኣኺራና ሸዕባን መሀል ያለው ረጅብ ናቸው) -ነቢዩ ሙሐመድ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም-
የረጀብ ወረ ከተከበሩ ወራት አንዱ በመሆኑ በሱ ውስጥ ወንጀሎችን ከመዳፈር ከሌላ ጊዜ በበለጠ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል:: ታላቁ ታቢዒ ቀታዳ አሏህ ይዘንላቸውና በዚህ ዙሪያ የሚከተለውን ብለዋል " በተከበሩ ወራት ውስጥ እራስንም ይሁን ሰዎችን መበደል ከሌሎች ወራት የበለጠ ይከለከላል ወንጀል ምንግዜም ከባድ ቢሆንም በነዚህ ወራት በሚሰሩ ወንጀሎች ግን አሏህ ከባድ ቅጣትን ይቀጣል" በነዚህ ወራት ውስጥ ወንጀሎች ልዩ ቅጣት እንደሚያስቀጡት ሁሉ መልካም ስራዎችም ልዩ አጅር ያሰጣሉ::
==የረጀብ ወር ማስታወሻ== ክ/2
መልካም ስራ ከቦታዎች -እንደ መካና መዲና- እንዲሁም ከወቅቶች -እንደ ረመዷንና የሐጅ ቀናት- አንጻር የሚበላለጥ መሆኑ በቁርኣን አና በነቢዩ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ንግግር ተረጋግጧል ስለሆነም ዘውትር የምንፈጽማቸው እንደ ሷላት ዚክር ሰደቃ ጾም ዱዓና ለሰዎች በጎ መዋል ወዘተ የረጀብን ወር ጨምሮ በተከበሩ ወራት ውስጥ ልዩ አጅር ያሰጣሉ:: ነገር ግን አንዳንድ አላዋቂዎች ከነዚህ ከተከበሩ አራቱ ወሮች ውስጥ ልዩ ክብርና ትኩረት የሚሰጡት ለረጀብ ብቻ ነው ይህ ማስረጃ አልባና ከጊዜ በኋላ የተፈጠረ መጤ አመለካከት ነው
ኢብኑ ከሢር የተፍሲር መጽሃፋቸው ላይ ከላይ የተጠቀሰውን የሱረቱ አትተውባ 36ኛውን ኣያ አስመልክተው ከታላቁ ሰሓቢይ ዐብዱሏሁ ኢብኑ ዐባስ ረዲየሏሁ ዐነሁ የሚከተለውን ዘግበዋል "" አሏህ በ12ቱም ወራት ውስጥ የከለከላቸው ነገሮችን በመዳፈር ያዘዛቸውን ነገሮችንም ባለመፈጸም እራስን ከመበደል ከከለከለ በኋላ አራቱን የተከበሩ ወራት ለይቶ በመጥቀስ ልዩ ትኩረት እንዲሰጣቸውና በነሱ ውስጥም የሚሰራ ወንጀል ከሌላው ይልቅ ከባድ እንደሚሆን እንዲሁም መልካም ስራዎችም ተጨማሪ ምንዳ እንደሚያሰጡ ገለጸ"" ብለዋል
==የረጀብ ወር ማስታወሻ== ክ/3
የረጀብ ወር ከተቀሩት የተከበሩ ወራት የሚለይበት ምንም ነገር ስለመኖሩ ከነቢዩ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም የተነገረ ነገር የለም:: በረጅብ ወር የሚሰሩ አንዳንድ ተግባራትን የሚጠቅሱ ሐዲሦች በሙሉ የሐዲስ ምሁራን ዘንድ ዷዒፍ -ደካማ- ናቸው
ማንኛውም ከዲን ጋር ተያያዥ የሆነ ስራ ነቢዩ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እራሳቸው ካልሰሩት ወይም ስሩት ብለው ካላዘዙ ወይም ደግሞ በዘመናቸው ሲሰራ አይተው ዝም ካላሉ ዒባዳ ነው ማለት አይቻልም:: በዘመናችን በሰፊው ከሚታዩ በድዓዎች -የዲን ላይ ፈጠራዎች- መሀከል አንዱ በረጀብ ወር ምክንያት የሚከሰቱ የተለያዩ አይነት ቢድዓዎ ይጠቀሳሉ: ቢድዓ ማለት በዲን ላይ መሰረት ያሌለውን ነገር መጨመር ወይም በመሰረቱ ዲን ላይ የሚታወቅን ነገር አፈጻጸሙን መቀየር ማለት ነው:: ቢድዓ በሙሉ ጥመት ነው የቢድዓ ጥሩ አለ ማለት ነቢዩ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ዲኑን ሙሉ በሙሉ አላደረሱም እንደ ማለት ይቆጠራል "" ዛሬ ሀይማኖታችሁን ሞላሁላችሁ"" ከሚለው የቁርኣን መመሪያም ይጻረራል
ነቢዩ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ግልጽ በሆነ አነጋገር፥
…وكل بدعة ضلالة ) رواه مسلم
""ቢድዓ በሙሉ ጥመት ነው""
ካሉት ንግግራቸው ጋርም ይጋጫል

==የረጀብ ወር ማስታወሻ== ክ/4
* የኢስራዕ እና ሚዕራጅን በዓል ማክበር *
በዲን ላይ አድስ ንነገር መለጠፍ ስራዬ ብለው የያዙ ሰዎች በየዓመቱ ረጀብ ወር 27ኛው ምሽት ላይ ነቢዩ ወደ ሰማይ የወጡበት ዕለት ነው በሚል ተሰብስበው ምግብ በማዘጋጀት የተወሰኑትም እንስሳትን በማረድ እንዲሁም ማንዙማበማቅረብና መሰልነገሮችንበማድረግ ዕለቱን ያከብራሉ, ይህ ተግባር ከሸሪዓ አንጻር ምንም ማስረጃ ያሌለው በመሆኑ ከቢድዓ ይቆጠራል:: ምክንያቱም ይህንን ተግባር ነቢዩም ይሁ ንሰሃቦቻቸው እንዲሁም የነሱን ፈለግ ተከታይ የነበሩ ደጋግ ቀደምቶች በሙሉ አላደረጉትም:: ከዚህም አልፎ የዲን ሊቃውንት ይህንን የፈጠራ ተግባር ተቃውመዋል ኢብኑሐጀርአል-ዓስቀላኒይ አሏህ ይዘንላቸውና በዚህ ዙሪያ የሚከተለውን ብለዋል" በረጀብ ትሩፋት ዙሪያና እሱንም ሙሉበሙሉም ይሁን ከፊሉን መጾምን አስመልክቶ እንዲሁም የረጀብ ወር ውስጥ በልዩ ሁኔታ የተወሰኑ ሌሊቶችን መስገድ አስመልክቶ አንድም ከነቢዩ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም የተዘገበ ማስረጃ ሊሆን የሚችል ሰሒሕ ሐዲሥ የለም ይህንንም ከኔ በፊት ሸይኹል
ኢስላም አል ሀረዊ ገልጸውታል""
በረጀብ ወር ላይ እነዚህና መስል ተግባራትን የጀመሩት ከነቢዩ ሱና የራቀ አካሄድ የሚሄዱት ራፊዷዎች (ሺዓዎች) እና ሶፊዮች ናቸው:: በአሏህና በምልዕክተኛው የሚያምን ሰው ስራውን በቁርኣንና ሐዲስ መመዘን ይኖርበታል ካልሆነ ግን ኢማኑ አይስተካከልም

==የረጀብ ወር ማስታወሻ== ክ/5
*ሰላት አርረጋኢብ *
ከቁርኣንና ሐዲስ የመነጨ እውቀት ያሌላቸውና በደመ-ነፍስ (በነሻጣ) ዒባዳ የሚያደርጉ ሰዎች ነቢዩን ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እየተከተሉ ከመሄድ ይልቅ እሳቸውን አስከትሎ መሄድ ያምራቸዋል:: እንደሚታወቀው ሰላት ከታላላቅ ዒባዳዎች መሀከል አንዱ ነው ነገር ግን ሰላት ምንም ታላቅ ዒባዳ ቢሆን ነቢዩ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ያልሰገዱትን አይነት ሰላት መስገድ በፍጹም አይቻልም:: ረጅብ ላይ ከሚከሰቱ ቢድዓዎች መሀከል አንዱ ከወሩ የመጀመሪያው ጁምዓ ምሽት ላይ ከመግሪብ እስከ ዒሻ ባለው ጊዜ 12 ረክዓ ሰላት መስገድ ይገኝበታል, እንደው ሌላ ጊዜ ፈርድ አስተካክለው የማይሰግዱ እንዲሁም ከፈርድ ሰላት ፊትና ኋላ ያሉ ሱናዎችን ጠብቀው የማይሰጉ ሁሉ ይህ መጤ ተግባር ላይ ሲሳተፉ ይታያል! እንዲህ አይነቱ ሰላት ከላይ እንደተጠቀሰው ነቢዩም ይሁን ሰሃቦቻቸው እንዲሁም የነሱን ፈለግ ተከታይ የነበሩ ደጋግ ቀደምቶች በሙሉ ያላደረጉት በመሆኑ ከፈጠራ -ቢድዓ- ይቆጠራል ከቢድዓ መራቅ ብልህነት ነው!

==የረጀብ ወር ማስታወሻ== ክ/6
*ወሩን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል መጾም*
ብዙ ሰዎች ረጀብን ሲጾሙ ይታያል ይህም ልዩ አጅር አለው ብለው ስለሚያምኑ ነው, ይሁን እንጂ ነቢዩ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ረጅብን ሙሉ በሙሉም ይሁን በከፊል መጾማቸውን የሚገልጽ አንድም ሰሒሕ ሐዲሥ የለም:: ይህንንም አስመልክተው ኢብኑ ተይሚያ የሚከተለውን ብለዋል: "ረጀብን ለይቶ መጽም በተመለከተ የሚጠቀሱ ሐዲሶች በሙሉ ዷዒፍ ከመሆን አልፎም ነቢዩ ላይ የተቀጠፉ ውሸቶች ናቸው" ኢብኑል ቀይምም እንዲህ ይላሉ ""ረጀብን መጾምና ከሱ ውስጥም በተወሰኑ ሌሊቶች ልዩ ሰላት መስገድን በተመለከተ የሚጠቀሱ ሐዲሶች በሙሉ ነቢዩ ላይ የተቀጠፉ ውሸቶች ናቸው""
ይህንን ጾም ደጋግ ቀደምቶች በጥብቅ ይቃወሙት ነበር ኸርሸህ ኢብኑ አል-ሑር በመባል የሚታወቀው ታቢዒ እንዲህ ይላል " ዑመር ኢብኑል ኸጣብ ረጀብን የጾሙ ሰዎችን ካየ እጃቸውን የምግብ ገበታ ውስጥ እስኪከቱ ድረስ ብሉ ረጀብ እኮ የጃሂሊያ -ከነቢዩ መላክ በፊት የነበሩ ህዝቦች- ያከብሩት የነበረ ወር ነው እያለ ጾመኞችን ሲመታ አይቻለሁ""በመሆኑም ሱና ነው በሚል ረጀብን ብቻ ነጥሎ ወሩን በሙሉ ወይም ከሱ ውስጥ የተወሰኑ ቀናትን መጾም ቢድዓ መሆኑን ልናውቅና ልንጠነቀቅ ይገባል ነገር ግን ዘውትር ሰኞ እና ሐሙስ እንዲሁም አያመልቢድ -በዓረብኛወርአቆጣጠር 13/14/15ኛ ቀናትን መጾም- ልምድ ያለው ሰው ያስለመደውን ጾም መጾም ይችላል

አሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱሏህ
==የረጀብ ወር ማስታወሻ== ክ/7
*ሚስኩል ኺታም*
በመጨረሻም፥ ኢማሙ አሕመድና ቲርሚዚይ ከዒርባድ ኢብኑ ሳሪያ ረዲየሏሁ ዐንሁ በዘገቡት ሐዲስ ነቢዩ ሰለሏሁ ዐለይሂወሰለም የሚከተለውን ብለዋል
" አሏህን በመፍራትና መሪዎቻችሁን በመታዘዝ አደራ! ከእኔ በኋላ ትልቅ ልዩነትን ታያላችሁ የኔን ሱና አጥብቃችሁ ያዙ! -የቅን ተተኪ መሪዎችንም ፈለገ- በኋላ ጥርሳችሁ ነክሳቹ ያዙ አድስ መጤ ነገሮችን ተጠንቀቁ የዲን ላይ ፈጠራ በሙሉ ጥመት ነው"