Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ረመዷን እና ቁርኣን ወይስ ረመዷን እና ነሺዳ??


አሰላሙ ዐለይኩም
ረመዷን እና ቁርኣን ወይስ ረመዷን እና ነሺዳ??
---በሰብርና እርጋታ ያንብቡት---
ከጥንት ጀምሮ ደጋግ ቀደምቶችና አሏህን ፈሪ ዑለማዎች ረመዳን ሲገባ ጥቅልል ብለው ወደ ቁርኣን ይዞሩ ነበር ኡመቱንም በዚሁ ይመክሩ ነበር
አሁን አሁን ግን በኢስላማዊ ነሺዳና ማንዙማ ስም ሰዎችን ከደጋግ ቀደምቶች ፈለግ ከሰላሙ የጀነት መንገድ የሚያፈናቅሉ የዓሊሞችን ልብስ የሚለብሱና ወደ ዲን ተጣሪ የሚመስሉ በረመዷን ስም እየነግዱ የምእምናንን ቀልብ የሚያደርቁ ሰዎች የበዙበት ዘመን ላይ ደርሰናል!!!
ረመዷን የቁርኣን ወር መሆኑን ከማወቃቸውና በተደጋጋሚም ከመስማታቸው ጋር አንዴ እንኳ የማያኸትሙ ነገር ግን አዳዲስ የሚታተሙ ነሺዳ ማንዙማና የሱዳን ሌላ ግዜ ደግሞ የሶማሌ ዘፈን እየገዙ የሚያደምጡ እጅግ በጣም ብዙ ናቸው
አሁን አሁን ጭራሽ ይባስ ብለው ታዳጊ ወጣቶችን በጉሩፕ እያደረጉ እስላማዊ ዘፈን (ነሺዳ ማለቴ ነው)በየመድረኩ ልክ ዘፋኞች እንደሚሆኑት እየሆኑ (ጺሙን ላጭቶ ሱሪውን ጎትቶ) የአሏህን እና የመልእክተኛውን ስም ወይም ቁርኣንና ሐዲስ እየጠቀሱ ሲዘፍኑ ማየትና መስማት ጀምረናል!!
ሴቷም ኢስላም በሐያእና ድምጽን መቀነስ እንዳላዘዛት ሁሉ ነሺዳና ግጥም እያለች ድምጿን እያስዋበችና እየተቅለሰለሰች የቤተ-ክርስቲያን አዝማሪ/ት ትመስል ድምጿን ለዓለም እየለቀቀች ጌታዋን ታምጻለች!!! ይህም አንሷት በዚህ ወንጀልን በተላመደ አንደበቷ የቁርኣንና ሐዲስ ጥቅሶችን እየቀነጭበች ትዘፍንባቸዋለች (ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን)
ይህ ተግባሯ አሏህን ከማስደሰት ይልቅ ሸይጧንን የሚያኮራ መሆኑን ዘንግታለች ወይም የጥመት ጎዳና ላይ በርቺ የሚሏት ከኢብሊስ ኮሌጅ ተመርቀው የወጡ ሀቅን እያወቁ በመደበቃቸውና የዚህችን ምድር ደስታና ተድላ ከጀነተል ፊርደውስ በማስበለጣቸው ምክንያት ለባጢል ዘበኛ የሆኑ ዓሊም እና ዳዒ ተብዬዎችን ተመክታለች::
ከመቼ ጀምሮ ነው ዘፈን ኢባዳና የደዕዋ ሲስተም የተደረገው? ለዚህስ ማነው እውቅና የሰጠው??
እናንተ ሙስሊሞች ሆይ፥ አሏህን ፍሩ ጭቃ ቤት ለማሰራት አናጺና ባለሙያ እንደምታማክሩት ሁሉ የጀነት ቤት ለማግኘት የሚያበቃችሁን እምነትና ዐቂዳችሁን በተመለከተ ሞኞችና ግዴለሾች አትሁኑ
አይን ጆሮ ልብ ወዘተ አሏህ እናንተ ጋር አደራ ያስቀመጣቸው ጊዜያዊ መጠቃቀሚያዎች ናቸው ነገ አሏህ ዘንድ የሚያስጠይቅን ነገር አትስሩባቸው
ነሺዳና መንዙማ ከስሜት ጋር ስለሚሄዱና የካፊሮችን ሙዚቃና ዘፈን ስለሚተኩ ጥሩ ነው እያልክ/ሽ አታድምጥ/ጪ ከቁርኣን የበለጠ ልብን የሚያረጥብ ነገር የለም
ከቁርኣንና ሐዲስ ውጪ ያሉ ነገሮች በሙሉ ጥመት ናቸው!!!
አሏሁመ ሀል በለግት አሏሁመ ፈሽሀድ!!
ረመዷን 18/1435
,,,,,,,አሕመድ አደም,,,,,,,,,



Post a Comment

0 Comments