Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የሸዕባን ወር ትሩፋቶች

°የሸዕባን ወር ትሩፋቶች
ምስጋና ለአለማት ጌታ ለአላህ ይሁን፤ ሰላትና ሰላም በመልክተኛውና በወደዳቸው ላይ ሁሉ ይውረድ።
የተከበረና የተባረከ ወር መምጫው ቀርቧል፤ በውስጣችን የኢማንና የሂዳያ (ቅናቻ) ስሜቶችን አነቃቅቷል፤ የኢባዳና የኸይር ስራ ፍላጎትን ቀስቅሷል፤ የሸዕባን ወር የረመዷን መሸጋገሪያና መግቢያ ወር ሲሆን ኡማው ወደ አላህ የመቃረብን ጣፍጭነትን የሚቀምስበትና የኢማንን ጣዕም በማጣጣም ለፆም፣ ለቂያምና ለበጎ ስራዎች ልምምድና ዝግጂት የሚያደርግበት ነው።
በዚህ ዝግጅት ታንፆ ወደ ረመዷን የገባ ወሩን በከፍተኛ ወኔና በጉጉት ይቀበላል፤ በኢባዳና በጣዓ (አላህን መታዘዝ) ላይም ይበረታል።
ለዚሁም ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ነጥቦች በአንክሮ ማየት ያሻል፡-
የሸዕባን ወር ትሩፋቶች
ነብያችን صلى الله عليه وسلم) በሸዕባን ወር ፆም የማብዛታቸው ሚስጠር
በተከበረው ወር (ረመዷን) መግቢያ ላይ ሆነን ልንመካከርባቸው የሚገቡ ነገሮች
ኢማም አህመድና ኢሚም አን-ነሳኢይ ከኡሳማ ቢን ዘይድ (رضي الله عنه) ጠቅሰው እንደዘገቡት“ነቢያችን (صلى الله عليه وسلم) ምንም ሳያቋርጡ አከታትለው ይፆሙ ነበር፤ በአንጻሩም አይፆሙም እስከምንል ድረስ ከሳምንቱ ሁለት ቀናትን እንጂ ሌላውን አይፆሙም ነበር፤ከወሮች ሁሉ (ከረመዷን ውጭ) በብዛት የሚፆሙት የሸዕባንን ወር ነበር፤ እኔም ‘የአላህ መልክተኛ ሆይ ምንግዜም አያፈጥሩም እሰከምንል ይፆማሉ፤ እንደዚሁም አይፆሙም እስከምንል ሁለት ቀናት ሲቀሩ ያፈጥራሉ፤ ሁለቱ ቀናት ፆመዎ ውስጥ ካልተጠቃለሉ ነጥለው ይፆሟቸዋል’ አልኳቸው፡፡ የአላህ መልክተኛም (صلى الله عليه وسلم) ‘ሁለቱ ቀኖች የትኞቹ ናቸው?’ ሲሉ ጠየቁኝ፤ ‘ሰኞና ሐሙስ’ አልኩኝ፣ የአላህ መልዕክተኛ (صلى الله عليه وسلم) ‘እነዚህ ሁለት ቀናት ሥራዎች ሁሉ ወደ አለህ የሚቀርቡባቸው ስለሆኑ እኔ ፆመኛ ሆኜ ስራዬ ወደ አላህ እንዲቀርብ ስለምፈልግ ነው’ ብለዋል።”
ከላይ በተጠቀሰው ሐዲስ ታለቁ ሰሐቢይ ኡሳማ ቢን ዘይድ (رضي الله عنه) የነቢያችንን (صلى الله عليه وسلم) የአመቱን እንቅስቃሴ ምን ይመስል እነደነበር ይገልፅልናል። ባልደረቦቻቸው አያፈጥሩም ብለው እስኪያስቡ ድረስ በተከታታይ መፆምና አይፆሙም ብለው እስኪያስቡ ድረስ በተከታተይ ማፍጥር የነብያችን (صلى الله عليه وسلم) መንገድ ነበር። ይህንን እናታችን ዓኢሻ (رضي الله عنها) እንዲህ በማለት ገልጸውታል“የአላህ መልክተኛ (صلى الله عليه وسلم) ምንግዜም አያፈጥሩም እስከምንል ድረስ ይፆሙ ነበር፤ አይፆሙም እስከምንል ድረስ ያፈጥሩ ነበር።”አነስ ቢን ማሊክ (رضي الله عنه) እነደተናገሩት ነቢያችን (صلى الله عليه وسلم) ሲፆሙ ፆም ጀመሩ ተብሎ ይነገር ነበር፤ ሲያፈጥሩም አፈጠሩ ተብሎ ይነገር ነበር።
ይህ የሚያሳየው የነቢያችንን (صلى الله عليه وسلم) ፆም ብዙሃኑ ባልደረባ ያውቀው እንደነበርና በሚጾሙባቸው ቀናት ያዩዋቸው ከፆማቸው ብዛት የተነሳ ሁል ጊዜ ይፆማሉ ይሉ እንደነበር፤ በአንፃሩ ደግሞ በፊጥራቸው ጊዜ (ሳይጾሙ) ያዩዋቸው በተከታታይ በዚህ ሁኔታ ሳይፆሙ ስለሚቆዩ አይፆሙም ይሉ ነበር። ይህ ሁኔታ የነቢያችን መንገድና መመሪያ ስለነበረ ነው።

Post a Comment

0 Comments