Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሸይኽ ኢብኑ ባዝ(ረሂመሁላህ) ስለ ሸዕባን 15 ለሊት ተጠይቀው የመለሱት ምላሽ እነሆ


እንደሚታወቀው ሸዕባን 15 ለሊት ላይ የተለያዩ ከሸሪአው መሰረት የሌላቸው ነገሮች ይፈፀማሉ።
ለምሳሌ የተለያዩ ምግቦችን ማዘጋጀት፣አዲስ አልባሳትን መልበስ ፣ለዱአ ብሎ መሰባሰብ ወዘተ …
ሸይኽ ኢብኑ ባዝ(ረሂመሁላህ) ስለ ሸዕባን 15 ለሊት ተጠይቀው የመለሱት ምላሽ እነሆ፦
«ሸዕባን ወርን አስመልክቶ አንድም ትክክለኛ ዘገባ ወይም መረጃ የለም። 
ይህንን ለሊት ከሌሎች ለሊቶች ልዩ የሚያደርገው ምንም ነገር የለም።በተጨማሪም ይህንን ለሊት አስመልክቶ በህብረት የሚቀራ ቁርአንም ሆነ ሰላት የለም።
የ ኢስላም ሊቃውንቶች እንዲህ ይላሉ፦
《ይህንን ቀን ከሌሎች ቀን ለተለየ ተግባር ለየት አድርጎ መያዝ አይቻልም። ቀኑን ልዩ ቀን አድርጎ መገመትም ደካማ አስተሳሰብ ነው ።》
በዚህ ጉዳይ ላይ ትክክለኛው እይታ ይሄ ነው።
አላህ የጥንካሬ ምንጭ ነው»