ረመዷንን እንዴት እንቀበል???
አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ፈቃዱ ከሆነ ከቀናቶች በውሃላ ታላቁና ውዱ እንግዳችን ረመዷንን እንቀበላለን።ግና እንዴት???
= አላህን በማመስገን።አዎ ብዙዎች አጊንተውት የእድሉ ተቋዳሽ ለመሆን ሲመኙና ሲጓጉ ቢቆዩም በድንገት ሞት የተባለው አይቀሬ ጠልፏቸዋል።ዳሩ እኔና እናንተም ለመድረሳችን ዋስትና ባይኖረንም።ግና በጌታችን ላይ ሙሉ ተስፋ አለን ። ኢንሻ አላህ እንደርሳለን። {ጌታችሁም ብታመሰግኑ በእርግጥ እጨምርላቹሃለው} ኢብራሂም 7
= በመደሰት። ምን ጥርጥር አለው። የያዘው መልካም ነገር እንዲህ አንድ ሁለት ተብሎ የሚዘለቅ አይደለም። ከአቡ ሁረይራ በተዋራውና አህመድና ነሳኢ በዘገቡት ሃዲስ ላይ የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ይህን ደስታና ብስራት እንዲህ ሲሉ ነበር ለባልደረቦቻቸው የሚነግሩት። "ያ የተባረከ የሆነው የረመዷን ወር መጣላችሁ። እርሱን መፆሙ በእናንተ ላይ ግዴታ ሆኗል። በእርሱ ውስጥ የጀነት በሮች ይከፈታሉ። የጀሃነም በሮች ይዘጋሉ። ሰይጣናት ይታሰራሉ። በውስጡ ከሺህ ወር የምትበልጥ ሌሊት አለችበት። የእርሷን መልካም ነገር የተከለከለ በእርግጥም መልካምን ተከለከለ።"
= ተውባ (ወደ አላህ መመልስ)። እንዴታ ተውበት ከታላላቅ አላማዎቹ ውስጥ አንዱ ነው እንጂ። ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዓንሁ) እንደተወራው የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል። " የረመዷንን ወር አምኖና ምንዳውን ከአላህ አስቦ የፆመ ያለፈ ወንጀሉ ይማርለታል።" ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። በእርግጥም ረመዷን ታላቁ የተውበት አጋጣሚና እድላችን ነው። አዎ። ለኡማው ታላቅ ፈረጃ ነው። በሽርክ የጨለመ በተውሂድ ወጋገን የሚበራበት ፤ በቢድዓ የዋዠቀ በሱና ጮራ የሚፈነጥቅበት ፤ በወንጀል የዘቀጠ አላህን በመታዘዝ ከፍ የሚልበት ታላቅ አጋጣሚ።
= እንግዲህ እንደ ናሙና ጥቂትን ነገር ለማለት ያህል ነው እንጂ ረመዷንን መቀበል ሲባል በማንኛውም ወደ አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ በሚያቃርቡ መልካም ነገሮች ሁሉ መዘጋጀትን ያካትታል።አቦ አደራ ግን እርሱን ለመቀበል ብሎ የቤትን ውስጥ ላይ ፍተጋን፤ ታይተው ተሰምተው ያልታወቁ የምግብና መጠጥ አይነቶች ጋጋታን እዚህ ውስጥ እንዳትጨምሩብኝ አደራ አደራ። አበቃሁ። አላህን ሱብሃነሁ ወተዓላ ባማሩት ስምና በሃሪዎቹ እለምነዋለው። ይህን ረመዷን ለኡማው መልካም ነገር ሁሉ ማግኚያ ከመጥፎ ነገር ሁሉ መጠበቂያ ሰበብ ያድርገው። እንዲሁም ኡማውን ወደ መሰረቱ (ተውሂድ) ለመመለስ ባላቸው አቅም ደፋ ቀና የሚሉ እህት ወንድሞችን ሁሉ ድልና የበላይነትን ያጎናፅፋቸው።አላሁመ አሚን።

0 Comments