ዚክር እና ጥቅሞቹ
አላህን ማሥታወሥ ያለዉ ጥቅም እና ትሩፋት = አላህን ማሥታወሥ ነፍሥያ እና ሸይጧን ላይ ድል መቀዳጃ ትልቅ በር ነዉ፡፡= ወደ አላህ ሡብሀነ ወተአላ መዳረሻ መንገድ ነዉ፡፡= አላህ ሡብሀነ ወተአላ የዚክርን በር የከፈተለት ሠዉ የሁሉንም የኸይር በሮች አግኝቷል፡፡= የዚክር በር የተዘጋበት ሠው የኸይር በሮች ተዘግተውበታል፡፡=ዚክርን አላህ ሡብሀነ ወተአላ ያገራለት ሠው ኢባዳዎች ሁሉ ይገሩለታል ፡፡= ዚክር የከበደው ሠው ከዚክር የሠነፈ ሠው ከኢባዳወችም ይሠንፋል፡፡= ዚክርን ማብዛት ሸይጧንን ከሠው ልጇች ያርቃል፡፡=አላህን ሡብሀነ ወተአላ ያሥደሥታልየአዱንያን ጭንቀት ያሥወግዳል፡፡=በልብ ውሥጥ ደሥታን ይፈጥራል፡፡=የደረቁ ቀልቦችን ያረጥባል፡፡=ብዙ ወንጀሎች ያራግፋል፡፡=ብቸኝነትን ያሥወግዳል ፡፡= ከአላህ ሡብሀነ ወተአላ ቅጣትም ይጠብቃል፡፡እንዲሁም ዚክር የሚያበዛ ሠው ከሙናፊቅነት ይድናል፡፡= ከቂያማ ቀን ከመፀፀት እና ከመቆጨት ያድናል፡፡= ጀነት ላይ የሠው ልጆች አትክልት እና ፍራፍሬ የሚያገኙትም በአዱንያ በማያደርጉት ዚክር ልክ ነው፡፡= የህሊና እረፍትን ይሠጣል፡፡= የአላህ ራህመት ይወርድበታል፡፡መላኢኮች ዙሪያውን ይከቡታል፡፡= በአዱኒያ ዚክር ለሚያበዛ ሠው አላህ ግንባሩ ላይ ኑርን ይሠጠዋል፡= ቀብር ጨለማ ቤት ላይ አላህ ብርሀንን ይፈጥርለታል፡፡= የቂያማ ቀንም በአዱኒያ ያደርገው የነበረው ዚክር ሢራጥን በሠላም እንዲሻገር ያደርገዋል፡፡ ፊቱምያበራል፡፡ለዚህም ነው አላህ ሡብሀነ ወተአላ የሠው ልጆች ዚክርን እንዲበዙ በተለያዩ የቁርአን አያዎች አዟል፡፡ ረሡል ሠለላሁ አለይሂ ወሠለም በብዙ ሀዲሶች ዚክርን ማብዛት እንዳለብን ገልፀዋል፡፡= ዚክር የሚያበዙ ሠወች የሚያገኙትን ትሩፋትም ጠቅሠዋል፡፡አላህ ሡብሀነ ወተአላ (ሡረቱል አህዛብ፡41-42) አያ ላይ = እናንተ ያመናችሁ ሠወች ሆይ= አላህን ሡብሀነ ወተአላ ብዙ ማሥታወሥን አሥታውሡት ጠዋትና ማታም አጥሩት ይላል አላህ ሡብሀነ ወተአላ ፡፡= በሌላው የቁርአን አያ የሡን ትክክለኛ ባሮችን መገለጫ ሢገልጵ= እነዚያ ያመኑ አላህን በማሥታወሣቸው ልባቸዉ ይረጋጋልየሠው ልጆች ሆይ አላህን በማሥታወሥ የልብ ሠላም እና እርጋታ ይገኛል፡፡ብሏል= በሌላኛው የቁርአን አያ አሥታውሡኝ አሥታዉሣችኃለሁ ብሏል፡፡ሐጅ ሥርአት ላይ ኢባዳችሁን ሥትጨርሡ አላህን ሡብሀነ ወተአላ አሥታውሡ፡፡ቤተሠቦቻችሁን እና ዘመዶቻችሁን ከምታሥታውሡት የበለጠ ይላላ፡፡== አላህን ሡብሀነ ወተአላ በብዛት አሥታውሡት ፡ እነሆ እሄን ያደረጋችሁ እንደሆነ ትድናላችሁ ይላል፡፡በተለያዩ የቁርአን አያዎች ላይ የዚክርን ጥቅሞች አላህ ገልጷል ፡፡=== ዐብዱሏህ ኢብኑ ዐባስ ረዲየሏሁ ዐንሁ የሚከተለውን ብለዋልአላህ ሡብሀነ ወተአላ ባሮቹ ላይ ማንኛውንም አይነት ኢባዳ አልደነገገም ኢባዳው በግልፅ በውል የሚታወቅ ገደብና መጠን ቢያደርግለት እንጂ፡፡ = ይህን ኢባዳ የታዘዙ እና የተደነገገላቸው ሠወችን ኡዝር ባላቸዉ ሠአት ይህን ኢባዳ ቢተዉት ምንም ችግር የለውም ብሎም ቢያሣውቅ እንጂ ፡፡ዚክር ሢቀር = ዚክርን በተመለከተ ይሄን ያክል ብቻ ዚክር አድርጉ ብሎ አላህ አልገደበውም፡፡= እንዲሁ ዚክርን መተውም አላህ ሡብሀነ ወተአላ ለማንም አልፈቀደም፡፡= አእምሮውን የሣተ ራሡን መቆጣጠር ያቃተው ሠው ካልሆነ በሥተቀር ዚክርን ለመተው አላህ ለማንም ኡዝር አልሠጠም፡፡ = እንደዚሁ ዚክርንም በዚህ ሠአት በሉ ብሎ አላህ አልገደባቸውም፡፡በወቅት የተገደቡ ዚክሮች ቢኖሩም በዛ ወቅት እነዚህ ዚክሮች መባል አለባቸው በዚህ ሠአት ቢባሉ ይመረጣል በማለት ነብያችን ሠለላሁ አለይሂ ወሠለም የተናገሩት ካልሆ ነበስተቀረ፡፡እንጂ ከዚህ ሠአት ውጭ አላህን ማሥታወሥ አይቻልም ማለት አይደለም፡፡ቆማችሁም አላህን አሥታውሡ ተቀምጣችሁም ተኝታችሁም አላህን አሥታውሡ፡፡== ቀንም ሌትም ባህርም ሆናችሁ የብሥ ላይ አላህን አሥታውሡ፡፡== ሀገርም ሆነ መንገድ ላይ በድንጋጤም ሆነ በደሥታ በህመምም ሆነ በጤንነት ጊዜም አላህን አሥታውሡ፡፡== በገሀድም በምሥጥርም በየትኛውም ቦታ እና ሁኔታ ላይ ብትሆኑ አላህን አሥታውሡት፡፡...ዚክር ከሚከለከልባቸው ቦታወች እንደ ሽንት ቤት አይነት ቦታወች ሢቀሩ ማለት ነው... = ጠዋት እና ማታም አላህን አጥሩት ብለው ከላይ የተጠቀሠውን ያደረጋችሁ እንደ ሆነ አላህና መላኢኮች በናንተ ላይ ሠለዋትን ያወርዳሉ፡፡አላህ ይቅር ይላቿሏመላኢኮችም ለናንተም ምህረትን ይጠይቃሉ፡፡የኢብኑ ዐባስ ንግግር እዚህ አበቃ በሌላም ንግግራቸው የሚከተለውን ብለዋል በብዛት አላህን የሚያሰታውሱ ወንዶች እና ሤቶች ማለት ከፈርድ ሠላት በኃላ አላህን የሚያሥታውሡ ጠዋትም ከሠአትም ማታም አላህን የሚያሥታውሡ ሢተኙም እንድሁም እንቅልፍ ላይ ሆኖም በባነኑ ቁጥር አላህን የሚያሥታውሡ ከቤትም በወጡ ቁጥር አላህን ያሥታውሡ፡፡ እሄን ያደረጉ እንደሆነ አላህን በብዛት ከሚያሥታውሡ ሠዎች ይመደባሉይህን ያደረጉ ሤቶች እና ወንዶች ምህረት እና ትልቅ አጂርን አዘጋጂቶላቸዋል ይላል፡፡ብለዋልነቢይ ሠለላሁ አለይሂ ወሠለም አቡ ሁረይራ በዘገቡት ሐዲሥ=,ሙፈሪዶች ቀደሙ ሲሉአንቱ የአላህ መልእክተኛ ሙፈሪዶች ማንናቸው ተብለው ሢጠየቁ?== በብዛት አላህን የሚያሥታውሡ ወንዶች እና ሤቶች ናቸው ብለዋል፡፡ዚክር በምላሥ ብቻ የሚባል አይደለም ፡፡በገሀድ ሠዎች ጋር በሚኮንበት ሠአት ብቻ የሚባል አይደለም፡፡ = እውነተኛ ዚክር የለመደ ሠው የዚክርን ጠአም ያወቀ ሠው ሁሌም አላህን ያሥታውሣል፡፡== በሌሊት ክፍለ ጊዜ አንድ ባል ተነሥቶ ሚሥቱን ቀሥቅሶ ወይም እሷ ተነሥታ ባሏን ቀሥቅሣ ቢያንሥ ሁለት ረካአ ሠላት የሠገዱ እንደሆን በብዛት አላህን ከሚያሥታዉሡት ሠዎች ይመደባሉ፡፡= እንደዚህ አይነት ሠዎችን አላህ ምህረት አዘጋጂቶላቸዋል፡፡ የነብዩ ሠለላሁ አለይሂ ወሠለም ሁኔታ ስንመለከት እናታችን አኢሻ ረደላሁ አንሃ ሁሌም አላህን በሁሉም ሁኔታ ላይ ያሥታውሱ ነበር ትላለች፡፡ አቡ ሁረይራ ባሥተላለፉት ሀድሥ= ሶሥት ሠዎችን አላህ ዱአቸዉን አይመልሥም ይላሉ፡፡ ከነዚህም መካከልአላህን በብዛት የሚያሥታውሡ ሠዎችን ጠቅሰዋል== የአላህ ባሪያ ሡብሀን አላህ አልሀምዱሊላህ ላኢላሀኢለሏህ ወሏሁ አክበር ያለ እንደሆነ አላህ ዱአውን እንደሚቀበለው ነብዩ ተናግረዋል፡፡ አንድ ግለ ሰብ አሥተምረኝ ጥሩ ነገር ንገረኝ ብሎ ወደ ነብዩ ዘንድ ሢመጣ ነብዩ ሠከላሁ አለይሂ ወሠለም ሡብሀን አላህ አልሀምዱሊላህ ላአኢላሀኢለሏህ ወላሁ አክበር በል አሉት፡፡ከዚያም የተወሠነ ብሎ ወደ ነብዩ ሠለላሁ አለይሂ ወሠለም መጥቶ እነዚህ ለጌታዬ ናቸዉ አላህን ማጥራት ነውለእኔሥ ብሏቸው ሢመጣ ነብዪ ሠለላሁ አለይሂ ወሠለም ሡብሀነ አላህ ሥትል አላህ እውነቱን ነዉ ይላልአልሀምዱሊላህ ሥትል እውነቱን ነው ይላል፡ላኢላሀኢለሏህ ሥትል እውነቱን ነው ይላል፡፡አላሁ አክበር ሥትል እውነቱን ነው ይላል፡፡ = እሄን ሁሉ አላህን አጥርተህ የለመንከው እንደሆነ የለመንከውን ነገር አያሣፍርህም ሁሌም እሡን እምታሞካሽ ከሆነ ያንተን ሀጃ ሥትጠይቀው መልሥ ይሠጠሀል በማለት ተናግረዋል፡፡== አቡ ደርዳር ባሥተላለፉት ሀድሥ ነብዪሠለላሁ አለይሂ ወሠለም ከሥራወች ሁሉ በላጭ የሆነ ሥራ በአላህ ዘንድ ማእረጋችሁን ከፍ የሚያደርግ ተወዳጅ የሆነ እንደዚሁ ወርቅ እና ብር ሠደቃ ከመሥጠት እና ከጠላታችሁ ጋር ፊት ለፊት ከመፋለም የሚበልጥ ሥራ ልንገራችሁን? አሉ አወን ሢሏቸው አላህን ሡብሀነ ወተአላማሥታወሥ ነው በማለት ነብዪ ሠለላሁ አለይሂ ወሠለም ተናግረዋል፡፡ == በሌላኛው ሀዲሥ ጌታዉን የሚያሥታውሥ እና የማያሥታውሥ ሠው መሳሌው እንደ ሞተ እና በህይወት እንዳለ ሠው ነው ይላሉ፡፡ = አላህን የሚያሥታውሥ በህይወት እንዳለ ሠው ነው፡፡= የሞተ ማለት ደግሞ አላህን የማያሥታውሥ ነው ብለዋል፡፡= ዚክር ማለት አላህን መፍራትና ማሥታወሥ ነዉ፡፡= ዚክር ከተውሂድ ይጀምራል፡፡አላህን የሚያሥታውሥ ሠው የአላህን ሡብሀነ ወተአላ ብቸኝነት ሊያወቅ እና ከሁሉም ጉድለት ሊያጠራው ይገባል፡፡= ሡብሀን አላህ ለላኢላሀኢለሏህ እያለ በአላህ ላይ ሚያጋራ ከሆነ ጥቅም የለውም፡፡= አላህን ማሥታወሥ በምላሥ ብቻ መሆን የለበትም፡፡በልብም በቀልብም ሊሆን ይገባል፡፡ አላህን ከሚፈሩ እና ከሚያሥታውሡት የአላህ ባሪያወች ያድርገን አሚን አህመድ አደም
0 Comments