Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የጾም ሕግጋት 1-3 By Ustaz Ahmed Adem




አሰላሙ አለይኩም
===የጾም ሕግጋት ክ ፩ ===
(ጾም አና መስፈርቶህቹ)
ጾም ማለት ጎህ ከቀደደበት ሰዓአት ጀምሮ ጸሓይ አስክትጠልቅ ድረስ (ከኒያ -እቅድ - ጋር ) ከምግብ ከመጠጥና ከግብረ -ስጋ ግንኙነት መታቀብ ማለት ነው 
ጾም ወደ አሏህ ከሚያቃርቡና እጅግ በጣም ተወዳጅ ከሆኑ ኢባዳዎች መካከል አንዱ ነው ጀነት ውስጥም ጾም ለሚያዘወትሩ ሰዎች ብቻ የተዘጋጀ በር አለ
ግዴታ -ዋጅብ- አና ግዴታ ያልሆነ ጾም አለ::
ግዴታ ጾም ማለት በአንደኛ ደረጃ የረመዷን ወር ጾም ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ የቀዷ የነዝር የከፋራ ወዘተ ግዴታ ጾሞች ሲሆኑ ሱና ወይም ግዴታ ያልሆኑ ሶሞች ደግሞ ሰኞና ሐሙስ የሹራ የአረፋ ወዘተ ጾሞች ይጠቀሳሉ
ሁሉም ኢባዳ መስፈርቶች አሉት ከጾም መስፈርቶች መካከል ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው
፩: ሙስሊም መሆን- ሙስሊም ያልሆነ ሰው ቢጾም ተቀባይነት አያገኝም (ቀድሞ መስለም ይጠበቅበታል )
፪ : አእምሮ ጤነኛ መሆን- እብድ ቢጾም ተቀባይነት አያገኝም
፫: ከወር-አበባ አና ከወሊድ ደም ንጹህ መሆን የወር-አበባ አና የወሊድ ደም ላይ ያለች ሴት ብትጾም ወንጀለኛ ትሆናለች
፬: ኒያ -እቅድ- መኖር ሳይነይቱ ከምግብ ታቅቦ መዋል ጾም አይባልም
፭: ከሰባት ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት ቢጾሙ ጾማቸው ተቀባይነት አይኖረውም ከሰባት በላይ የሆኑ ግን ለአካለ መጠን ያልደረሱ ህጻናት ጾም አነሱ ላይ ግዴታ አይደለም ቢጾም ተቀባይነት ያገኛል
===የጾም ሕግጋት ክ 2 ===
(ጾም አና ህጻናት)
ህጻናት ላይ ጾም ግዴታ የሚሆነው፥ ቀጥሎ ከሚዘረዘሩ ነገሮች መሀል አንዱ ተገኝቶ ለአካለ-መጠን ሲደርሱ ነው እነሱም፥
እድሜያቸው 15 ዓመት መሙላት ወይም ሀፍረተ-ገላቸው ላይ ጸጉር መብቀል ወይም የዘር ፈሳሽ ማየት ሲሆኑ ሴት ልጆች ደግሞ ከላይ ከተጠቀሱት በተጨማሪ የወር አበባ ደም ማይት ናቸው:: ከነዚህ መሀከል አንዱ ከተገኘ የረመዷንን ጾም ጨምሮ ሁሉም የዲንል-ኢስላም ህግጋት ይመለከቷቸዋል:: እድሜያቸው እዚህ ደረጃ ከመድረሱ በፊት ወላጆች ጾምን ሊያለማምዷቸውና እንዲጾሙም ሊያበረታቷቸው ይገባል ከልሆነ ግን ለአካለ-መጠን በሚደርሱበት ጊዜ ጾምን በአንዴ መልመድ ሊከብዳቸው ይችላል:: ብዙ ወላጆች ልጆቻቸውን መልካምን ነገር በለጋ እድሜያቸው ከማስለመድ ይልቅ ችላ ሲሏቸውና ገና ልጅ ናቸው እያሉ መጥፎ ባህሪይ ላይ እንዲያድጉ ሲያደርጓቸው ይታያል:: እንዲሁም ለአካለ-መጠን ደርሰው ሳለ ወላጆች የልጆቻቸውን ሁኔታ ባለ መከታተላቸውና ልጆችም (በተለይ ሴት ልጆች) አፍረው ዝም በማለታቸው ምክንያት ብዙ ሀይማኖታዊ ግዴታዎችን ከመወጣት ወደ ኋላ ሲሉ ይስተዋላል ይህ ወላጆችን አሏህ ዘንድ የሚያስጠይቅ ትልቅ ወንጀል ነው:: አሏህ በተከበረው ቃሉ የሚከተውን ብሏል
(يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آَمَنُوا قُوا أَنْفُسَكُمْ وَأَهْلِيكُمْ نَارًا وَقُودُهَا النَّاسُ وَالْحِجَارَةُ عَلَيْهَا مَلَائِكَةٌ غِلَاظٌ شِدَادٌ لَا يَعْصُونَ اللَّهَ مَا أَمَرَهُمْ وَيَفْعَلُونَ مَا يُؤْمَرُونَ)
( እናንተ ምእምናን ሆይ፥ እራሳችሁንም ቤተ-ሰቦቻችሁንም ማገዶዋ የሰው ልጅ እና ድንጋይ ከሆነችዋ የጀሀነም እሳት ጠብቁ -አድኑ- ከሷ ዙሪያም ጨካኝና ብርቱ የሆኑ አሏህ ያዘዛቸውን እምቢ የማይሉና የታዘዙትን በሙሉ የሚፈጽሙ መላይኮች አሉ ) አት-ተሕሪም 7
እራስንና ቤት-ሰብን ከጀሀነም እሳት ማዳን የሚቻለው አሏህ ያዘዘውን በመታዘዝና የከለከለውን በመከልከል ነው:: ህጻናት ከላይ ከተጠቀሱ ምልክቶች መካከል አንዱ እነሱላይ በመመገኘት ለአካለ-መጠን መድረሳቸው እንደተረጋገጠ አምስት ወቅት ሰላትን ቀጥ ብለው ሊሰግዱና ረመዷንንም ሊጾሙ እንዲሁም መላ የዲን ህግጋትን ሊጠብቁ ይገባል:: ይህን ግዴታ ያልተወጣ ወላጅም በሙሉ አሏህ ዘንድ ይጠየቃል

===የጾም ሕግጋት ክ 3 ===
(ጾምን የሚያፈርሱ ነገሮች )
ጾምን የሚያፈርሱ ነገሮች
ጾምን የሚያፈርሱ ነገሮችን ማወቅና መራቅ የሁሉ ሙስሊም ግዴታ ነው:: የዲን ሊቃውንት ጾም በአንዳንድ ነገሮች የሚፈርስ መሆኑ ላይ ከመስማማታቸውም ጋር ዝርዝር ሁኔታዎች ላይ ግን የተወሰኑ ልዩነቶች አሉ::
1ኛ: መብላትና መጠጣት እንዲሁም ምግብና መጠጥን የሚተኩ እንደ ጉሉኮስና የብርታት መርፌ ያሉ ነገሮች:: ጾመኛ መሆኑን ረስቶ የበላ ወይም የጠጣ ሰው እንዳስታወሰ በማቋረጥ ጾሙን መቀጠል ይችላል
2ኛ: የግብረ-ስጋ ግንኙነት መፈጸም እንዲሁም ሆን ብሎ በማነኛውም መልኩ የዘር ፈሳሽ እንዲወጣ ማድረግ፥ በረመዷን ጾም በቀኑ ክፍለ ጊዜ ጾም እንደሚያበላሽ እያወቁ ሆን ብሎ የግብረ-ስጋ ግንኙነት የፈጸም ሰው ጾሙ ከመበላሸቱም አልፎ ከባድ ወንጀል እንደተዳፈረ ይቆጠራል ተውበት ማድረግና ይህንን ቀን ቀዷ ከማውጣት በተጨማሪም በተከታታይ ( ያለምንም ማቋረጥ) 60 ቀን መጾም በበቂ ምክንያት ካልቻለም 60 ሚስኪን መመገብ ይጠበቅበታል:: ይህ ሁለቱንም ጾታዎች የሚመለከት ሲሆን ሴቷ ተገዳ ከሆነ ምንም አትወቀስም ጾሟንም መቀጠል ትችላለች:: በረመዷን ወር ሸይጧን ታስሮ ሳለ ስሜታቸውን ብቻ ማሸነፍ አቅቷቸው ይህን መሰል ወንጀል ላይ የሚወድቁ ሰዎች አሏህን ሊፈሩና የረመዷንን ወርም ክብር ሊጠብቁ ይገባል:: የበለጠ በጣም የሚያስጠላው ደግሞ ሚስቱ ካልሆነች ሴት ጋር ሲሆን ነው!!! አሏህን እንፍራ ቁጣውንና እርምጃውን አንቋቋምም እርሱ ቻይ እንጂ ቸልተኛ አይደለም!!! እንቅልፍ ላይ ሆኖ የዘር ፈሳሽ መውጣት ጾምን አያበላሽም::
3ኛ: በዋግምትና መሰል መንገዶች ደምን ከሰውነት ማስወጣት እና ትውከት፥እነዚህ ነጥቦች ላይ ኺላፍ ያለ ሲሆን መጠንቀቅና ከነዚህ ነገሮች መራቁ ይሻላል:: ለምርመራ ደም መስጠትና ጥርስን መንቀል ጾምን አያፈርስም::ሳይፈልጉት በሀይል የወጣ ትውከትም እንደዚሁ አያፈርስም::
ጾመኛ ሆኖ በየተኛውም ሰዓት መጉመጥመጥ፣ መፋቂያ መጠቀም፣ የአይን ጠብታ፣ መርፌ መወጋትና ምግብን ቀምሶ ከዛም መትፋት ይቻላል