Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

በመርካቶ በፒያሳ ተክለሀይማኖትን ጨምሮ እንዲሁም በቦሌ አካባቢ ማንኛውም ሱቆች ላይ የሚሰሩ ሙስሊም ሴቶች ወደ ምን እየሄዱ ነው ግን ?

‎تنبيهات على أحكام تختص بالمؤمنات    ተንቢሀት - ሙስሊም ሴቶችን የተመለከቱ ህግጋት‎'s photo.
ለሴቶች ሼር አድርጋችሁ አስነብቡልኝ ...
Kimiya Abdurezak
በመርካቶ በፒያሳ ተክለሀይማኖትን ጨምሮ እንዲሁም በቦሌ አካባቢ ማንኛውም ሱቆች ላይ የሚሰሩ ሙስሊም ሴቶች ወደ ምን እየሄዱ ነው ግን ? እራሳቸውን ማስዋባቸውና መጠበቃቸው መልካም ነው። ግን ወርቅ፣ ሽቶ እና ብን ያለች ሂጃብ ወይም ግማሽ ሂጃብ፣ ያለ እስቶኪንግ ወይም ያለ ካልሲ የሚለበሰው የተንጠለጠለው ቀሚስ ማድረጉ ካፊሮች "የሰለጠነች ዘመናዊ ናት" እንዲሉሽ ይሆን እረ ሲስ አላህን ፍሪ በልብስ፣ በጫማ፣ በሂጃብ መፎካከሩን ምን አመጣው ደግሞ ሚገርመው ያገቡትም እህቶቻችን እንዲህ መሆናቸው ነው አቤት ዘንድሮ ። ጅልባብና ኒቃብ የሚለብሱ ሴቶችም የዚሁ አባል ናቸው መከናነቢያቸውን ሴቶች በበዙባቸው ማንኛውም ቦታዎች ላይ በማውለቅ ጎልቶ ለመታየት የቻሉትን ሁላ ሲጥሩ ሲፎካከሩ ሲጨናነቁ ይታያሉ። በዚህ መሀል አይናቸውን የሚያንከራትቱ የሆኑ ያጡ የነጡ ሚስኪን እህቶችሽን ለቅፀበት እንኳን አያሳስቡሽም አዙሮ ማሰብ የለም ጭራሽ በጣም የሚገርመኝ ቤት ውስጥ ለባልሽ ልበሺው ብትባል የማትለብሰውን ውድ ልብስ ሴቶች ጋር ስትሄድ ለመፎካከር ትለብሰዋለች ወይም የባልዋ ወንድሞች ወይም ጓደኞች ሲመጡ ለበስ ታደርገዋለች እሱም ደዩስ ስለሆነ ግድ የለውም ሴቶቹ ትነሽ ሰብሰብ ካሉ ደግሞ " ይሄን በስንት ገዛሽው ? እስቲ ልለካው? በዚህ ያህል ብር ነው የገዛሁት እንዴት ነው አያምርብኝም ? የዚህ ብራንድ ካልሆነ ብዙም አይደላኝም ከዚህ አገር ነው ያመጣልኝ ምናምን" እያሉ በቃ መጎር መለፈፍ ነው።
የበታቻቸውን መመልከት የለ ፣ ሀያእ የለ ፣ አላህ ምን ይለኛል የለ እረ ሚገርም ነው ጌጦቻችሁን ሸፍኑ የሚለን ቁርአን ያለ ምንም ምክኒያት አይደለም። ወላሂ አንድ የገጠመኝን ላካፍላችሁ ሁለት ህፃናት መሀል ተቀምጨ የሰማሁትን ላካፍላችሁ ልጆች ሲያወሩ እንደምታያቸው ካወቁ እውነተኛ ማንነታቸውን አታገኙትም እየሰራችሁ እንደሆነ ካወቁ ምታዳምጧቸው አይመስላቸውም እና እኔም በዚህ ሁኔታ ውስጥሆኜ ስራዬን እየሰራሁ የ6 አመት እና የ 7 አመት ሙስሊም የሆኑ ሴት ህፃናት ያወራሉ አንደኛዋ ለሌላኛዋ "አዲስ ልብስ ተገዛልኝ" ትላታለች ሁለተኛዋም " የኔኮ ልብስ አባቢ ከዱባይ ነው የሚያመጣልኝ ያንቺ ልብስ እኮ የዚህ አገር ነው ደግሞ ዝም ብሎ ነው" አለቻት በዚህ ጊዜ የመጀመሪያዋ ልጅ ፊቷ ቀላ እንደተናደደች ያስታውቃል ወዲያው ከተቀመጠችበት ተነሰታ ሮጣ ከአጠገባችን ጠፋች ።
እንግዲ አስተውሉ እቺ ትንሽ ልጅ እንኳን እንዴት እንደተሰማት ...
አሁን ደግሞ የሚደረጉት አገር የሚያክሉ ጫማዎች ከዱባይ ስለ መጡ ብቻ ነው የምንለብሳቸው ነጮቹ እኮ ይህን ጫማ የሰሩት ከቤትዋ በመኪዋና ወደ መዝናኛ ከመዝናኛ በመኪናዋ ወደ ቤትዋ አምትሽከሰከር ስራ ፈት እንጂ ለኛ አገር በዚህ ላይ ተሰቅለን የወላለቀ መንገድ ይዘን በእግራችን እንድንኳትንበት አይደለም የተሰራው እድታቁት ያህል ነው። ስንቶቹን መንገድ ላይ ወለም እያላቸው እየወደቁ ነው።
አሁን ደግሞ የመጡ ሙሉ ቀሚስ ሆነው ከላይ እስከ ታች የተጣበቁ ልብሶች መተዋል አቤት ፈተና አንድ ጊዜ ሱቅ ላይ ምትሰራ ልጅ አለች ትንሽ አወራት ስለ ነበር እንዲህ አልኳት "እንደዚህ አይነት ልብስ እየለበሽ የምታገቢው ወንድ መጥፊያሽ እንጂ መልሚያሽ አይሆንም" ባልኳት ብዙም ሳይቆይ ደህና የሚባል ሰው አገባች። ከሁለት አመት በኋላ አገኘኋት ሆድ እየባሳት እስካሁን ልጅ አልወለድኩም እሱም ፍፁም መረን ለቋል በጣም እየተቀባባ ሲወጣ ጠረጠርኩት እና ተከተልኩት በተለያየ ጊዜ ዱባይ ሄጃለሁ ብሎኝ ከተለያዩ ሴቶች ጋር ሆቴል እያደረ አገኘሁት አለኝኝ። እረ ነገሩ እንዴት ነው???
የሠለመች እህት ከኛ ምን ትማር ? አላህ ያስተካክለን!!
መስጂድም ላይ በዚህ ዙሪያ ዳእዋ ቢሰጥ መልካም ነው።
ሴቱ እየጠፋ ነው! ፋክክሩም ተባብሷል!! አይኑን ከፍቶ በደንብ ነገሮችን እያስተዋለ የሚገስፅ የሚያስተምር
ዳኢም ጠፍቷል!!
ለእኔም ለናንተም አላህ ቀልብ ይስጠን......አሚን