Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ጥያቄ - በረመዳን ወር ቴልቪዥን እና ቪዲዮ መመልከት ፆምን ያጓድላልን? ሸይኽ ኢብኑ ኡሰይሚን

ጥያቄ - በረመዳን ወር ቴልቪዥን እና ቪዲዮ መመልከት ፆምን ያጓድላልን?
መልስ - አንድ ሠው የሚያዳምጠው ወይም የሚመለከተው ነገር ከተፈቀዱ ነገሮች (ሙባሀት)
ከሆነ ምንም ችግር የለውም ፆምመአ ላይ እንከን አይሆንም፡፡ ሆኖም ግን ፆመኛ ሰው ጊዜውን
ወደ አላህ ሊያቃርበው በሚችል ነገር ብቻ ነው ማሳለፍ ያለበት፡፡ ቁርዓንን ያነባል አላህን
ያወድሳል ወዘተ... አላህ ሀራም ያደረገውን ነገር ማዳመጥ ወይም መመልከት ግን
ፆምን እንደሚያጓድል ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ የዚህም ምክንያት ፆም የተደነገገበት አላማ
የአላህን ፍራቻ (ተቅዋን) መላበስ ነው፡፡ (እናንተ ያመናችሁ ሆይ ጾም በነዚያ ከናንተ በፊት
በነበሩት (ሕዝቦች) ላይ እንደ ተጻፈ በናንተም ላይ ተጻፈ (ተደነባ) ልትጠነቀቁ ይከጀላልና፡፡)
አልበቀራህ (183) አላህ በዚሃ አንቀፅ ፆም በግዴታነት የተደነገገበት አላማ ተቅዋ መሆኑን
ገልፆዋል፡፡ ነብዩ እንዲህ ብለዋል ‹‹መጥፎ ንግግርን ….. መሀይምነትን ያልተወ ሰው አላህ
ዘንድ ምግብና መጠጥ መተው ቦታ የለውም (ቡኻሪ ዘግበውታል) በዚህ መሠረት ማንኛውም
ፆመኛ የሚሠራው ሀጢዓት ፆሙ ላይ ተፅዕኖ አለው፡፡ ከዚህም ውስጥ አንዳንድ ሠዎች
እንደሚያደርጉት ከምግብ ከመጠጥና ከስጋዊ ተራክቦ ይቆጠቡና በአላህ ላይ ያምፃሉ፡፡
አንዳንዱ ሱሁር ከበላ በኋላ ይተኛና የፈጅርን ሠላት ያሣልፋል የሚነሣው ፀሃይ ከወጣች በኋላ
ነው፡፡ ሌላው ደግሞ የዓስርን ሠላት ሣይሰግድ ይተኛና በኢፍጣር ሰዓት ተነስቶ አራት ጊዜ ጎንበስ
ቀና ይላል፡፡ ጥቂትን እንዲ አላህን አያድስም፡፡ አንዳንድ ሠዎች ደግሞ ሠዎችን ያማሉ በንግድ
ወቅት ያጭበረብራሉ ብዙ ወንጀሎችንም ይፈፅማሉ፡፡ ይህን ሁሌ የሚያደርጉት ፆመኛ ሆነው
ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ የሚፈፅሙን ሀራም ተግባር የፆማቸውን ምንዳ እንደሚቀንሠው ጥርጥር
የለውም፡፡ ምናልባትም ምንዳውና ሀጢአቱ እኩል ይሆኑና የፆሙን ምንዳ ያጣሉ፡፡ ለሙስለሊም
ወንድሞች እና እህቶች የማስተላልፈው ምክር፤ አላህ በእነርሱ ላይ እርም ካደረጋቸው ነገሮች
እና ተግባሮች ፆማቸውን እንዲጠብቁ እና ይህን የተባረከ ወር አላህን በመታዘዝ እንዲያሳልፉት
ነው፡፡ እርም ነገሮችን ከመተው እና ግዴታዎችን ከመፈፀም ረገድ ራሳቸውን የሚያንፁበት ታላቅ
እድል ነው፡፡ ወቢላሂ ተውፊቅ ሸይኽ ኢብኑ ኡሰይሚን


ዝክረ ረመዳን مجالس شهر رمضان
 June 21, 2014

Post a Comment

0 Comments