Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ቁርኣንና የተከበረው የረመዷን ወር


ቁርኣንና የተከበረው የረመዷን ወር
ቁርኣንና ረመዷን የጠበቀ ግንኙነትና ትስስር አላቸው ለዚህም ነው {ረመዷን ሸህሩል ቁርኣን} የሚባለው ይህንንም የተረዱ ደጋግ ቀደምቶች ረመዳን ላይ ከሌላው ግዜ በበለጠ ቁርኣን ለመቅራት ትልቅ ትኩረት ይሰጡ ነበር ታላቁ አርኣያችንም ነቢዩ ሙሀመድ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ረመዷን ላይ በየሌሊቱ ከመላእክቶች ሁሉ ታላቅ ከሆነው ጅብሪል ጋር ቁርኣንን ይማማሩ ነበር::
ታላቁ ሰሃቢ ኡስማን ኢብኑ አፋን ደግሞ ረመዷን ላይ በየሌሊቱ ቁርኣንን አንዴ ያከትሙ ነበር
ኢማሙ ሻፊኢ ደግሞ በረመዷን ውስጥ 60 ጊዜ ያከትሙ ነበር: ቀታዳ ሚባሉት ሊቅ ደግሞ በየሶስት ቀኑ ያከትሙ ነበር: ኢማሙ አዝዙህሪም በበኩላቸው ረመዷን ሲመጣ ይሰጧቸው የነበሩ የዲን ትምህርቶችን በሙሉ በማቆምና ከሰዎችም በመራቅ ቁርኣን ይዘው ያነቡ ነበር::
እኛስ ረመዷን ላይ ምንድን ነው ምንቀራው??!! አላህ ያዘነለት በስተቀር ያብዛኞቻችን ሁኔታ በጣም ያሳዝናል:: ከፊሉ ሀራም የሆነውን ዘፈን ከፊሉ በቢድኣና ሽርክ የተሞላውን መንዙማ ከፊሉ የቁርኣን ጸር የሆነውን ዘመናዊ ነሺዳ በመስማት ስያሳልፉት ሌሎችም ደግሞ ቴሌቭዥን ላይ እና ኮምፕዩተር ላይ አይናቸውን ተክለው ውድና ድንቅ የሆነውን የረመዷን ወር ጊዜያቸውን ያባክናሉ: በዚህም ሸይጣንን እያስደሰቱ ረህማንን ያስቀይማሉ: ሙእሚኖች ለጀነት ስንቅ እያዘጋጁም እነሱ ወደ ጀሀነም በር ይጠጋጋሉ: አላህ ሁላችንንም ወደሱ ያማረ መመለስን ይመልሰን: እነሆ ውድ ወንድሞችና እህቶች በተቻለን ያክል ቁረኣንን ደጋግመን ለማክተም እንሞክር ሌላ ወር ላይ ከሚገኘው አጅር እጥፍ ድርብ የሆነ አጅር ነውና የሚገኝበት:


by Ahmed Adem

Post a Comment

0 Comments