ተራዊሕ ሶላት ላይ የኢማሙን ቂራኣ ቁርኣን ይዘን የምንከታተል አለን። ነገር ግን ሳይታወቀን ብዙ ስህተቶች እየፈፀምን ነው።
➣ ሶላት ላይ እጅ የሚቀመጠው ደረት ላይ ነው፡፡ ቁርኣን በእጅ ሲያዝ ግን ይሄ ሱና ይቀራል።
➢ ለሶላት የቆመ ሰጋጅ እይታው የሱጁድ ቦታ ላይ መሆን
አለበት። ቁርኣን በእጅ ሲያዝ ግን እይታ ቁርኣን ላይ ስለሚሆን ይሄ ሱና ይቀራል።
➢ቁርኣን በእጃቸው የሚይዙ ሰዎች ኢማሙ በቂራኣ ሲሳሳት
ሁሉም ለማረም ስለሚሞክሩ አላስፈላጊ ጫጫታ ይፈጠራል።
➢ ሶላት ላይ ኹሹዕ ወሳኝ ነገር ነው። ቁርኣን ይዘን ስንከታተል ግን በርካታ አላስፈላጊ እንቅስቃሴዎች ይኖራሉ።
Ibnu Munewor